ከዚህ ቀደም ወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ በሚል ስያሜ ይታወቅ የነበረው ክለብ ከዚህ በኋላ “ድቻ ስፖርት ክለብ” በሚል እንደሚጠራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በቅርቡ እንዳስታወቀው የብሔር እና ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ስያሜዎችን የሚጠቀሙ ክለቦች ስያሜያቸውን እንዲያስተካክሉ ባወጣው መመሪያ መሰረት ወላይታ ድቻ ቀዳሚው ማስተካከያ ያደረገው ክለብ ሆኗል። በዚህምRead More →

ያጋሩ

ኢትዮጵያ ቡና የግብ ጠባቂ ኮታውን በቦትስዋናዊ የግብ ዘብ ማሟላቱ ታውቋል። ኢትዮጵያ ቡና በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና መሪነት በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም የ2015 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታውን በነገው ዕለት ወላይታ ድቻን በመግጠም ይጀምራል። ክለቡ የመጨረሻው ሊሆን በሚችል ቅጥር ከሳምንት በፊት የኬኒያ ዜግነት ያለውን ግብ ጠባቂ ጃኮብ ሆሳኖን ለማስፈረም ተቃርቦ በልምምድ ወቅትRead More →

ያጋሩ

ኢትዮጵያ ብቸኛ የአፍሪካ ዋንጫ ድሏን ካጣጣመች እነሆ 60 ዓመታት ያህል ተቆጠሩ። አገሪቱ ወርቃማ የእግርኳስ ዘመኗን የሚደግምላት ትውልድ ሳታገኝ ፣ ጀብድ የፈጸሙላት ጀግኖቿንም በወጉ ሳታከብር ግማሽ ክፍለ ዘመን ተሻገረች። በኢትዮጵያ እግርኳስ ኗሪ ታሪክ ሰርተው የመረሳት ሰለባ ከሆኑ ባለውለተኞች መካከል ሉቺያኖ ቫሳሎ ቀዳሚው ነው። ዳሚያኖ ቤንዞኒ በሉቺያኖ ቫሳሎ ግለ-ታሪክ ዙሪያ ከተጻፈውና  “Read More →

ያጋሩ

አዲስ አዳጊው ክለብ ኢትዮጵያ መድን የሦስት የውጪ ዜጋ ተጫዋቾችን ዝውውር ፈፅሟል፡፡ በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከስምንት ዓመታት በኋላ ብቅ ብሎ በዛሬው ዕለት ቅዱስ ጊዮርጊስ በመግጠም የውድድር ዘመኑን የሚጀመረው የአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌው ኢትዮጵያ መድን በርካታ የሀገር ውስጥ አዳዲስ ተጫዋቾችን ካስፈረመ በኋላ ፊቱን ወደ ውጪ ሀገር በማዞር ዝውውሩ ከመጠናቀቁ በፊት በኢትዮጵያ እግርRead More →

ያጋሩ

ዛሬ የተጀመረው የዘንድሮው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ነገ በሁለት ጨዋታዎች ሲቀጥል የተጋጣሚ ቡድኖችን የተመለከቱ መረጃዎችን እንደሚከተለው አሰናድተናል። ኢትዮጵያ መድን ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ መድን ከከፍተኛ ሊግ ማደጉን ተከትሎ በፕሪምየር ሊጉ ከስምንት ዓመታት በኋላ በሚያደርገው የመጀመሪያ ጨዋታ ከቻምፒዮኖቹ ጋር ይገናኛል። አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌን በመቅጠር ከነባር ስብስቡ ብዙሀኑን አስቀርቶና ተጨማሪ ዝውውሮችን ፈፅሞRead More →

ያጋሩ

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ የሆኑት ንግድ ባንኮች የወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ውል ሲያድሱ አንድ ተጫዋቾችም ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል። በአሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመራው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2014 የሴቶች ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ከሆነ በኋላ በሴካፋ የቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ውድድር ላይ ከመካፈሉ በፊት ናርዶስ ጌትነት፣ ብርቄ አማረ፣ መሳይ ተመስገን እና አርየት ኦዶንግ ያስፈረመ ሲሆን በዛሬው ዕለትRead More →

ያጋሩ

የጦና ንቦቹ በዘንድሮው ውድድር የዓምናው ቡድናቸው ላይ መጠነኛ ለውጦችን በማድረግ ቀርበዋል። በየዓመቱ በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ከሚታዩ ቡድኖች መካከል የሆነው ወላይታ ድቻ ዘጠነኛ የውድድር ዓመቱን ለመጀመር በዝግጅት ላይ ይገኛል። ዓምና የነበረው የድቻ ጉዞ 5ኛ ደረጃን ይዞ በመጨረስ የተደመደመ ቢሆንም በሁለቱ ዙሮች ፍፁም የተለያየ መልክን አሳይቷል። በመጀመሪያው ዙር 9 ድሎችን በማስመዝገብRead More →

ያጋሩ

ከደቂቃ በፊት አማኑኤል ገብረሚካኤልን በቡድናቸው ያቆዩት ፈረሰኞቹ የሌላኛውን አጥቂያቸውን ውል ማራዘማቸውም ታውቋል። ለ2015 የውድድር ዘመን ዛሬ ወደ ባህር ዳር ያቀኑት ቅዱስ ጊዮርጊሶች የወሳኝ አጥቂያቸውን አማኑኤል ገብረሚካኤልን ውል ካካዘሙ በኋላ አሁን ደግሞ የአዲስ ግደይን ውል ማራዘማቸውን አውቀናል። በሲዳማ ቡና ለአራት ዓመታት ቆይታ አድርጎ በ2013 የፈረሰኞቹ ቤት የተቀላቀለው አዲስ ግደይ ከጉዳት ጋርRead More →

ያጋሩ

በግብፅ ሊግ ያመራል ተብሎ በስፋት ይነገር የነበረው አማኑኤል ገብረሚካኤል በፈረሰኞቹ ቤት የሚያቆየውን ውል አራዝሟል። ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከፈረሰኞቹ ጋር መልካም ጊዜን በማሳለፍ የ2014 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ማንሳት የቻለው አማኑኤል ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለአንድ ዓመት ለመቆየት መስማማቱን ክለቡ ይፋ አድርጓል። በዳሽን ቢራ ቢ ቡድን የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው አማኑኤል በመቐሌRead More →

ያጋሩ

የመሀል ተከላካዩ ምንተስኖት ከበደ ከሲዳማ ቡና ጋር በስምምነት ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እየቀረው ተለያይቷል፡፡ በያዝነው ዓመት ከሲዳማ ቡና ጋር ቀሪ የአንድ ዓመት ውል በመኖሩ የቅድመ ውድድር ዝግጅትን በሀዋሳ ከተማ ከክለቡ ጋር ሲሰራ የነበረው የመሀል ተከላካዩ ምንተስኖት ከበደ በጋራ ስምምነት ከክለቡ ጋር ተለያይቷል፡፡ የቀድሞው የመከላከያ ፣ መቀለ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያRead More →

ያጋሩ