ባሳለፍነው የጨዋታ ሳምንት ሁለት ግቦች ከአንድ ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ተቆጥረዋል ፤ እኛም እነዚህን ግቦች መነሻ በማድረግ የተወሰኑ ሀሳቦችን ለማንሳት ወደናል። ሊጉ ከመቋረጡ በፊት በተደረገው የመጨረሻው 13ኛ የጨዋታ ሳምንት በተደረጉ ስምንት ጨዋታዎች በአጠቃላይ ሃያ ግቦች የተቆጠሩ ሲሆን ግቦቹ የተቆጠሩበትን ደቂቃዎች ከተመለከትን አንዳች የሚነግሩን ነገር አለ። አንድን የጨዋታ አጋማሽ በሦስት አስራ አምስትRead More →

በመጀመሪያው ሳምንት በክለቡ ታሪክ እጅግ አስከፊ ከሆኑ ውጤቶች አንዱን በማስመዝገብ የጀመሩት ኢትዮጵያ መድኖች በመጨረሻ ሦስት ጨዋታዎች ግን ከአስከፊው ሽንፈት ቀና ያሉባቸውን ተከታታይ ድሎች አሳክተዋል። ገና ብዙ መንገድ ቢቀርም ብዙዎች የሰጉለት ቡድን ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ፤ እኛም ስለቡድኑ የአራት ጨዋታ ጉዞ ተከታዩን አሰናድተናል። ከስምንት ዓመታት በኋላ ዳግም ወደ ፕሪምየር ሊጉRead More →

14 ጨዋታዎች በድምሩ 41 ጎሎች ፣ በርከት ያሉ ድንቅ ጎሎች እንዲሁም የመጨረሻ ደቂቃዎች ድራማዎችን በማስመልከት የጀመረው የ2015 የውድድር ዘመን አጀማመሩ አስገራሚ ሆኗል። በተከታዩ ፅሁፋችን በጥቂቱ በሁለቱ ሳምንታት ስለተመለከትናቸው ጎሎች የተወሰኑ ሀሳቦችን ለማንሳት ወደናል። እግርኳስ ለተወሰኑ ዕድለኞች ስራ ለተቀረው ብዙሀኑ ደግሞ መዝናኛ ነው። በእግርኳስ ለመዝናናት ደግሞ ጎሎች እና የመጨረሻ ደቂቃዎች ድራማዊRead More →

አዲሱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ባሳለፍነው ሳምንት ዓርብ ጅማሮውን አድርጓል። እኛም አዲሱን የውድድር ዘመን መጀመር አስመልክቶ በየዓመቱ ከቡድን ግንባታ መርህ በተፃረረ መልኩ ባለ ሁለት አሀዝ ብዛት ያላቸውን ተጫዋቾች ማዘዋወር መደበኛ ነገር ስለሆነበት ሊጋችን ጥቂት ነጥቦችን ለማንሳት ወደናል። አዲስ ዓመት እና አዳዲስ ነገሮች የተዛመዱ ናቸው። እርግጥ ስለ አዲስ ነገር ለማሰብRead More →

የመጨረሻው ፅሁፋችን ደግሞ በዚህኛው ሳምንት ያስተዋልናቸው ሌሎች ትኩረት የሚስቡ ጉዳዮች የቀረቡበት ነው። 👉 የተሳታፊ ክለቦች ቁጥር ይጨመር ይሆን ? ካለፉት ጥቂት ቀናት አንስቶ በሊጉ ከቀጣይ ዓመት አንስቶ የተሳታፊ ክለቦች ቁጥር ሊጨምር ይችላል የሚለው ጉዳይ በስፋት በእግርኳሱ ዙርያ ባሉ አካላት መካከል እየተንሸራሸረ ይገኛል። ከዚህ ጋርም በተያያዘ ከሊጉ መውረዱን ያረጋገጠው የሰበታ ከተማውRead More →

ሦስተኛው የትኩረታችን ክፍል ደግሞ አሰልጣኞችን የተመለከተ ይሆናል። 👉 አነጋጋሪው የፀጋዬ ኪዳነማርያም አስተያየት እርግጥ አሁን ላይ የሚታዩ መሻሻሎች ቢኖሩም በሊጉ ወጣት ተጫዋቾች በቂ ዕድል ካለማግኘታቸው በስተጀርባ የሚነሳው አንደኛው ጉዳይ በሊጉ በወጣቶች ላይ ዕምነት አሳድረው ለማጫወት ድፍረት ያላቸው አሰልጣኞች ቁጥር አነስተኛ የመሆኑ ጉዳይ ነው። አብዛኞቹ የሊጉ አሰልጣኞች በሚያስብል መልኩ የቡድናቸውን ነገ ዛሬRead More →

ቀጣዩ ትኩረታችን ደግሞ በጨዋታ ሳምንቱ ትኩረት የሳቡ ተጫዋቾች ላይ ያተኮሩ ሀሳቦች የተዳሰሱበት ነው። 👉 ቀጣዩ የሊጉ አብሪ ኮከብ – ብሩክ በየነ 13 ግቦች ላይ የደረሰው ብሩክ በየነ በሰሞነኛ የግብ ማስቆጠር ግስጋሴው ቀጥሎ በመጨረሻው ጨዋታ የሊጉ ከፍተኛ አስቆጣሪ ይሆን ወይ? የሚለው ጉዳይ በጉጉት ይጠበቃል። በውድድር ዘመኑ ከአንድ ጨዋታ ውጭ በተቀሩት በሙሉRead More →

ሊጠናቀቅ የአንድ ጨዋታ ሳምንት ዕድሜ በቀረው የዘንድሮው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሳምንት የተመለከትናቸው ትኩረት የሳቡ ክለብ ነክ ጉዳዮች በተከታዩ ፅሁፋችን ቀርበዋል። 👉 የዋንጫው ፉክክር ወደ መጨረሻው ዕለት አምርቷል አሸናፊው እስካሁን ባለየለበት የዘንድሮው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አንገት ለአንገት ተናንንቀዋል። በጨዋታ ሳምንቱ ሁለቱም ቡድኖች ነጥብRead More →

የመጨረሻው የትኩረታችን ክፍል ደግሞ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ያተኩራል። 👉 የመጨረሻዎቹ ጨዋታዎች እና ዳኝነት ባህር ዳር ከተማ እና ድሬዳማ ከተማ ያደረጉት የ28ኛ የጨዋታ ሳምንት መርሃግብር እጅግ አወዛጋቢ የነበረ የዳኝነት ውሳኔን የተመለከትንበት ጨዋታ ነበር። በጨዋታው በ89ኛው ደቂቃ ላይ ድሬዳዋ ከተማዎች ያገኙትን የማዕዘን ምት አብዱለጢፍ መሀመድ ያሻማውን ኳስ አቡበከር ኑራ መቆጣጠር አለመቻሉን ተከትሎRead More →

ሦስተኛው የትኩረታችን ክፍል ደግሞ አሰልጣኞች ላይ ያተኮረ ነው። 👉 የደረጀ መንግሥቱ አስተዋፅዖ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የነበሩት ባህር ዳር ከተማዎች በዚህኛው የጨዋታ ሳምንት ድሬዳዋ ከተማ ላይ ወሳኝ ድል ማሳካት ችለዋል። በጨዋታው የቀድሞው የቡድኑ አምበል ቡድኑን በሜዳ ጠርዝ ሆኖ ሲመራ ተመልክተነዋል። አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ቡድኑን ክረምት ላይ ከተረከቡ ወዲህ ባለፉት ዓመታት የባህርRead More →