በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ በተከታታይ የተቀመጡትን ክለቦች የሚያገናኘውን ጨዋታ እንደሚከተለው ቃኝተነዋል። በሁለት ነጥብ እና በአንድ ደረጃ ብቻ ተለያይተው በደረጃ ሰንጠረዡ አንደኛ እና ሁለተኛ ቦታ ላይ የተቀመጡት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ መድን በዋንጫ ፉክክር ውስጥ ትልቅ ተፅዕኖ ሊያመጣ የሚችለውን የእርስ በእርስ ፍልሚያ ነገ ምሽት 1 ሰዓት ያከናውናሉ። ቅዱስ ጊዮርጊሶች ይህንን ጨዋታRead More →

ነገ በተስተካካይነት የሚደረገው የወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡናን ጨዋታ የተመለከቱ መረጃዎችን እንደሚከተለው አሰናድተናል። 13 የጨዋታ ሳምንታትን በተጓዘው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በብቸኝነት የቀረው የወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና ተስተካካይ ጨዋታ ነገ ይደረጋል። የ11ኛ ሳምንት መርሐግብር የነበረው ይህ ጨዋታ ሊጉ ከአዳማ ወደ ድሬዳዋ መመለሱን ተከትሎ ቀድሞ እንዲደረግ በታሰበበት የድሬዳዋ ስታዲየም 11:00 ላይRead More →

የሊጉን መመለስ የሚያበስረው 45ኛው የመዲናይቱን ትልቅ ደርቢ የተመለከተ ቅድመ ዳሰሳ በሚከተለው መልኩ አሰናድተናል። የሀገራችን ከፍተኛው የሊግ እርከን ውድድር የሆነው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በብሔራዊ ቡድናችን የቻን ዝግጅት እና ውድድር ምክንያት ታኅሣሥ 16 ከ13ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በኋላ የተደረጉትን ተስተካካይ ጨዋታዎች አከናውኖ መቋረጡ ይታወቃል። ከአንድ ወር በኋላ ደግሞ ነገ ሲመለስ ብዙዎች በጉጉት በሚጠብቁትRead More →

የወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታ ወደ አዳማ መዘዋወሩን ተከትሎ ነገ በሊጉ የሚደረገውን ብቸኛ ጨዋታ የተመለከቱ መረጃዎችን እንደሚከተለው አሰናድተናል። 11ኛው የጨዋታ ሳምንት ድሬዳዋ ላይ በሚኖረው ቆይታ ነገ ምሽት ፋሲል ከነማን ከድሬዳዋ ከተማ በሚያገናኘው ጨዋታ ይቋጫል። ለሦስት ጨዋታዎች ድል ርቆት የነበረው ፋሲል ከነማ ተከታታይ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ቢችልም ወደ ሰንጠረዡ አናት ፉክክርRead More →

በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ የተቀመጡ ክለቦችን የሚያገናኘው የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታን የተመለከተ ዳሰሳ እንደሚከተለው አሰናድተናል። በአንድ ነጥብ እና አንድ ደረጃ ብቻ ተበላልጠው የሊጉን ፉክክር በበላይነት እየመሩ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባህር ዳር ከተማ ነገ ምሽት 1 ሰዓት የሚያደርጉት ጨዋታ የብዙዎችን ቀልብ በመያዝ ትልቅ ግምት ተሰጥቶታል። በጨዋታው ባህር ዳር ከተማ ባገኘው የአሸናፊነትRead More →

የሊጉ የባህር ዳር ከተማ ቆይታ ነገ መቋጫውን ሲያገኝ ዐፄዎቹን ከጣና ሞገዶቹ የሚያገናኘውን ተጠባቂ ጨዋታ በሚከተለው መልኩ ዳሰነዋል። ለፕሪምየር ሊጉ ተጨማሪ ድምቀትን እየፈጠረ የሚገኘው ይህ መርሐግብር እጅግ ከፍ ባለ የመሸናነፍ ስሜት እና በከፍተኛ የደጋፊዎች ቁጥር ታጅቦ ይደረጋል። ካርዶች እና አነጋጋሪ የዳኝነት ውሳኔዎች የማያጡት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በፕሪምየር ሊጉ ለሰባተኛ ጊዜ ነገRead More →

ያለፉት ሁለት ዓመታት የሊጉ አሸናፊዎችን የሚያገናኘውን የነገውን ተጠባቂ ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል። ፋሲል ከነማ ወደ ፕሪምየር ሊጉ መድረክ ከመጣበት የ2009 የውድድር ዓመት ጀምሮ በሁለቱ ቡድኖች መካከል የሚደረጉ ጨዋታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ የትኩረት ደረጃቸው ከፍ እያለ መጥቷል። በተለይም ፋሲል ከነማ ዋንጫውን ባነሳበት 2013 እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉን ክብር ከቆይታ በኋላ ባስመለሰበት 2014Read More →

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ነገ ከቀትር በኋላ የሚደረጉ የሦስተኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎችን የተመለከቱ መረጃዎች እንደሚከተለው አጠናክረናል። ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በመጀመሪያው የጨዋታ ሳምንት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ተጫውተው ነጥብ የተጋሩት ወላይታ ድቻዎች የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ድል ለማግኘት ነገ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ይጠበቃል። በባህር ዳሩም ሆነ በቅዱስ ጊዮርጊሱ ጨዋታ ባለቀ ሰዓትRead More →

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሦስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ ጅማሯቸውን ሲያደርጉ የጨዋታ ሳምንቱ የመክፈቻ ጨዋታ የሆነው የመቻል እና አርባምንጭ ከተማን የተመለከቱ መረጃዎችን አሰናድተናል። አርባምንጭ ከተማ ከ መቻል ፍፁም በተለያየ መንገድ ክረምቱን ያሳለፉት ሁለቱ ቡድኖች የሊጉ አጀማመራቸው በተጠበቀው ልክ አልሆነላቸውም። ጥቂት ተጫዋቾችን በማስፈረም የውድድር ዘመኑን የጀመሩት አርባምንጭ ከተማዎች በመጀመሪያዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ሽንፈትንRead More →

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ሁለት ጨዋታዎች ዙሪያ ተከታዮቹን መረጃዎች አሰባስበናል። ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጀመሪያው ሳምንት በቅደም ተከተል ሽንፈት እና ድል ያገኙት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች እና ቅዱስ ጊዮርጊሶች ነገ 7 ሰዓት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። ሊጉ በአዲስ መልክ 1990 ላይ ሲመሰረት ሻምፒዮን የሆነው ኤልፓ ከወቅቱ የሊጉ ባለድልRead More →