ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ (Page 2)

በሊጉ ለመቆየት እየታተሩ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ለመሳተፍ እየተፋለሙ ከሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚያደርጉትን የነገ ከሰዓት ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል። ከሁለት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ድል ያገኙት ሲዳማ ቡናዎች በመጨረሻ ጨዋታቸው ነጥብ ጥለዋል። ቡድኑም በሊጉ የሚያቆየውን ውጤት ለማስመዝገብ እና ወደ አሸናፊነት ለመመለስ በነገው ጨዋታ ሦስት ነጥብን እያሰበ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ይገመታም።ዝርዝር

የ23ኛውን ሳምንት ቀዳሚ ጨዋታ የተመለከቱ ነጥቦችን እንዲህ አንስተናል። የውድድር ሳምንቱ በመልካም ቁመና ላይ የሚገኘው ወላይታ ድቻን በሊጉ የመቆየት ተስፋው ከተመናመነው ጅማ አባ ጅፋር ጋር ያገናኛል። ካለፉት ሦስት ጨዋታዎች አምስት ነጥቦችን የሰበሰቡት ወላይታ ድቻዎች በሰንጠረዡ አጋማሽ ቢገኙም ቀሪዎቹ ጨዋታዎች ደረጃቸውን ይበልጥ አሻሽለው ለመጨረስ ስለሚረዷቸው ካለብዙ ጨዋታ ሙሉ ነጥብ ለማሳካት ወደ ሜዳዝርዝር

ጥሩ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ የሚጠበቀውን የኢትዮጵያ ቡና እና ወላይታ ድቻን ጨዋታ እንደሚከተለው ተመልክተነዋል። ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች ድል ማድረግ ያልቻለው ኢትዮጵያ ቡና ወደ አሸናፊነት ለመመለስ እና የአፍሪካ የክለቦች የውድድር መድረክ (የኮንፌዴሬሽን ካፕ) ላይ ተሳታፊ የሚያደርገውን የሁለተኛ ደረጃ አጥብቆ ለመያዝ ሦስት ነጥብን አልሞ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ይታሰባል። የድሬዳዋ ቆይታውን በጥሩ አፈፃፀም ያገባደደውዝርዝር

በሀዋሳ የሚደረገውን የመጀመሪያ የሊጉ ጨዋታ የተመለከቱ ነጥቦችን እንዲህ አንስተናል። በታችኛው የሰጠረዡ ክፍል ፉክክር ውስጥ ያሉትን ቡድኖች የሚያገናኘው ጨዋታ ለአንዳቸው ተስፋን ለሌላኛቸው ደግሞ የመጨረሻ ዕድልን ይዞ የሚመጣ ነው። በሊጉ የመቆየት ተስፋው በእጁ ያለው ድሬዳዋ ከተማ ሙሉ ነጥቦችን ካሳካ በጊዚያዊነትም ቢሆን ከአደጋው ቀጠና በአራት ነጥቦች መራቅ ይችላል። እስካሁን ዘጠኝ ነጥብ ላይ የቆሙትዝርዝር

በነገ ምሽቱ ጨዋታ ዙሪያ የሚያተኩረው ዳሰሳችን ይህንን ይመስላል። በነገው ዕለት የሚከናወነው የሮድዋ ደርቢ ጠንከር ያለ ፉክክርን እንደሚያስተናግድ ይጠበቃል። ድሬዳዋ ላይ ሁለት ድል እና ሁለት ሽንፈትን ያስመዘገቡት ሲዳማዎች ዛሬ አንድ ነጥብ ያገኘው ተፎካካሪያቸው ድሬዳዋ ከተማን ለመጠጋት ነገ አሸንፈው መውጣት የግድ ይላቸዋል። ባለፉት አራት ጨዋታዎች ከ12 ነጥቦች አስሩን ማሳካት የቻለው ሀዋሳ ከተማዝርዝር

የነገውን ቀዳሚ ጨዋታ በዳሰሳችን ለመመልከት ሞክረናል። በሰንጠረዡ አናት እና ግርጌ የሚገኙት ቡድኖችን የሚያገናኛው ጨዋታ ውጤት ለሁለቱም የተለያየ ትርጉም ይኖረዋል። ለፋሲል ከነማ ከተከታዩ ጋር ያለውን ልዩነት ይበልጥ አስፍቶ በጊዜ ዋንጫውን በእጁ ለማስገባት የሚያደርገው ጥረት ውስጥ የሚከወን ጨዋታ ነው። በተቃራኒው አዳማ ከተማ ቢያንስ ከበላዩ ያለው ጅማ አባ ጅፋር ጋር በነጥብ ለመስተካከል እናዝርዝር

የቀጣዩ ዳሰሳችን ትኩረት የነገ ምሽቱ ጨዋታ ይሆናል። በመካከላቸው በባህር ዳር የበላይነት የሰባት ነጥቦች እና የአራት ደረጃዎች ልዩነት ይኑር እንጂ ይህ ጨዋታ ጥሩ ፉክክር እንደሚኖርበት መናገር ይቻላል። የጣና ሞገዶቹ ማሸነፍ ከቻሉ በዚህ ሳምንት አራፊ ከሆነው ኢትዮጵያ ቡና ሁለተኛነቱን የመረከብ ዕድል በመኖሩ ውጤቱ አብዝቶ ያስፈልጋቸዋል። ኃይቆቹም የሚያስከፋ ሁኔታ ላይ ባይገኙም የታችኛውን የሰንጠረዥዝርዝር

በ20ኛው ሳምንት ቀዳሚ ጨዋታ ዙሪያ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተናል። አሁን ላይ የከፋ ስጋት የሌለባቸው ሁለቱ ቡድኖች በሰንጠረዡ አጋማሽ አካባቢ ላይ ሆነው ይበልጥ ራሳቸውን የሚያደላድሉባቸውን ነጥቦች ፍለጋ ይገናኛሉ። ድሬዳዋ ላይ የመጀመሪያ ሦስት ነጥባቸውን ጅማ አባ ጅፋርን በመርታት ያሳኩት ሰበታዎች አሸነፊነታቸውን ካስቀጠሉ የነገ ተጋጣሚያቸውንም በነጥብ በልጠው ከፍ ማለት ይችላሉ። የኮቪድ በትር አብዝቶ ያረፈበትዝርዝር

ነገ ምሽት የሚደረገውን ተጠባቂው የሸገር ደርቢን ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል። የውድድር ዓመቱን አራተኛ ሽንፈት በሀዋሳ ከተማ ካስተናገዱ በኋላ ሰበታን በመርታት ዳግም ወደ አሸናፊነት የተመለሱት ኢትዮጵያ ቡናዎች የድል ጉዞዋቸውን ለማስቀጠል፣ ከመሪው ፋሲል ከነማ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ እንዲሁም ተጋጣሚያቸው ቅዱስ ጊዮርጊስን ጨምሮ ከሚከተሏቸው ብድኖች ለመራቅ በነገው ጨዋታ ሦስት ነጥብ ያስፈልጋቸዋል። ድልዝርዝር

የ19ኛው ሳምንት የማሳረጊያ ቀን ቀዳሚ በሆነው ጨዋታ ዙሪያ እነዚህን ነጥቦች አንስተናል። በሰንጠረዡ የታች እና የላይኛው ፉክክር ውስጥ ይገኙ እንጂ የቡድኖቹ የነገው ጨዋታ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ፋሲል ከነማ የአምስት ተከታታይ የድል ጉዞው በባህር ዳር ቢቋረጥም ከተከታዩ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት እምብዛም የሚያሰጋው አይደለም። ያም ቢሆን ግን በቶሎ ወደ አሸናፊነት በመመለስ ልዩነቱንዝርዝር