ጠንካራ ፉክክርን ያስመለከተን የባህርዳር ከተማ እና መቻል ጨዋታ በመጨረሻም በባህርዳር ከተማ 3ለ2 አሸናፊነት ተጠናቋል። መቻሎች በመጨረሻ ደቂቃ ጎል ከሀዋሳ ጋር ነጥብ በተጋሩበት ጨዋታ ከተጠቀሙት አሰላለፍ በሁለቱ ላይ ለውጥ አድርገዋል። ሳሙኤል ሳሊሶ እና ግርማ ዲሳሳን በበረከት ደስታ እና ከነዐን ማርክነህ ሲተኳቸው በ25ኛው ሳምንት ጨዋታ ባህርዳሮች በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ከገጠመው ስብስባቸው አደምRead More →

ሀድያ ሆሳዕና ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2ለ1 በመርታት በደረጃ ሰንጠረዡ አራተኛ ላይ ተቀምጦ የሀዋሳ ቆይታውን አጠናቋል። ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮጵያ ቡናው ሽንፈቱ በሦስት ተጫዋች ላይ ለውጥ አድርጎ ገብቷል። ፔፕ ሰይዶን በያሬድ በቀለ ፣ዳግም በቀለን በሔኖክ አርፊጮ ፣ ዘካሪያስ ፍቅሬን በባዬ ገዛኸኝ ሲተካ በአርባምንጭ ከተርታው ስብስባቸው ኤሌክትሪኮች ደግሞ ዮናስ ሰለሞንን በሚኪያስ መኮንን በብቸኝነት የተኩበትRead More →

የወልቂጤ እና ፋሲል የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ 0ለ0 በሆነ ውጤት ፍፃሜን አግኝቷል። ወልቂጤ ከተማ ድል ካደረጉበት የመድኑ ጨዋታቸው ቅያሪ ሳያደርጉ ሲገቡ በአንፃሩ ከድሬዳዋው ሽንፈታቸው ፋሲሎች የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገዋል። በለውጡም አስቻለው ታመነን በዓለምብርሀን ይግዛው ፣ ሀብታሙ ገዛኸኝን በዱላ ሙላቱ ተክተዋል። ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት የዕለቱ ዋና ዳኛ ተካልኝ ለማ ፋሲሎች ያደረጉት መለያRead More →

ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ቡናን 2-1 በመርታት የሀዋሳ ቆይታውን በድል ዘግቷል። ኢትዮጵያ መድን ከወልቂጤው ሽንፈት በሦስት ተጫዋች ላይ ቅያሪ አስፈልጎታል። ሐቢብ መሐመድ ፣ ዮናስ ገረመው እና ሀብታሙ ሸዋለምን በፀጋሰው ድማሙ ፣ አሚር ሙደሲር እና ወገኔ ገዛኸኝ ሲተኩ ሀድያ ላይ ኢትዮጵያ ቡና ድል ካደረገው ስብስቡ ጉዳት በገጠመው ሬድዋን ናስር ምትክ ጫላ ተሺታንRead More →

አዳማ ከተማ በሁለተኛው አጋማሽ ከጥሩ እንቅስቃሴ ጋር ታግዞ ከመመራት ተነስቶ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ድሬዳዋ ከተማን አሸንፏል። ድሬዳዋ በፋሲሉ ድል ላይ ይዞት የገባውን አሰላለፍ ሳይለውጥ ለጨዋታው ሲቀርብ በአንፃሩ በለገጣፎ ሽንፈት ያስተናገዱት አዳማዎች የአምስት ተጫዋቾችን ቅያሪ አድርገዋል። እዮብ ማቲዮስ ፣ ዳንኤል ደምሱ ፣ አማኑኤል ጎበና ፣ ቦና ዓሊ እና ቢኒያም አይተንን በአዲሱRead More →

ሀዋሳ ከተማ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት የመጀመሪያ ሦስት ነጥቡን ወላይታ ድቻን 3ለ1 በመርታት አስመዝግቧል። ሀዋሳ ከተማ በመጨረሻ ደቂቃ ግብ ተቆጥሮበት ነጥብ ከተጋራው የመቻሉ ጨዋታ የአንድ ተጫዋች ለውጥ አድርጎ ጀምሯል። በለውጡም በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቶ በነበረው ግብ ጠባቂው መሐመድ ሙንታሪ ምትክ አላዛር ማርቆስን በብቸኝነት ሲለውጡ ከሲዳማ ቡና ጋር ያለ ጎል አጠናቀውRead More →

የተቀዛቀዘ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ በተበራከተበት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለገጣፎ ለገዳዲን 2ለ1 በመርታት የሊጉን መሪነት አጠናክሯል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ድቻን ከረታበት ስብስቡ ቅጣት ባስተናገዱት ፍሪምፓንግ ሜንሱ እና ረመዳን የሱፍ ምትክ ምኞች ደበበ እና ሱለይማን ሀሚድን ሲጠቀሙ ከአዳማው ድል አንፃር ለገጣፎ ለገዳዲዎች ታምራት አየለን በበረከት ተሰማ የተኩበት ብቸኛ ለወሰጣቸው ሆኗል። አሰልቺ የሜዳRead More →

በበርካታ ደጋፊዎች ታጅቦ የተደረገው የሲዳማ ቡና እና የአርባምንጭ ከተማ ጨዋታ 1ለ1 በሆነ የአቻ ውጤት ተጠናቋል። ቡድኖቹ በተመሳሳይ የሁለት ተጫዋቾችን ለውጥ ባደረጉበት ለውጦቻቸው ሲዳማ ቡና ከድቻው የአቻ ውጤቱ አማኑኤል እንዳለን በደግፌ ዓለሙ እና እንዳለ ከበደን በይስሐቅ ከኖ ሲተኩ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ላይ ድልን ያሳኩት አርባምንጮች በበኩላቸው ወርቅይታደስ አበበን በአካሉ አትሞ እንዲሁም ቡጣቃRead More →

ኢትዮጵያ ቡና በአማኑኤል ዮሐንስ እና መስፍን ታፈሰ ጎሎች ሀድያ ሆሳዕናን 2-1 በማሸነፍ ደረጃውን ከፍ አድርጓል። ሀድያ ሆሳዕና የባህር ዳር ድሉ ላይ የተጠቀመበትን አሰላለፍ ሳይቀይር ለጨዋታው ሲቀርብ ከለገጣፎ ነጥብ የተጋሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በአንፃሩ ራምኬል ጀምስን በክዋኩ ዱሀ ፣ መሐመድ ኑርናስርን አብዱልከሪም ወርቁ ተክተው ቀርበዋል። ቀዝቀዝ ባለ ዐየር ጅምሩን ያደረገው የሁለቱ ቡድኖችRead More →

ወልቂጤ ከተማ ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት እና በጨዋታ ባስቆጠራቸው ግቦች ኢትዮጵያ መድንን 2ለ0 በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠናው ከፍ ያለበትን ውጤት አሳክቷል። ሁለቱ ቡድኖች ካለፈው ሳምንት ጨዋታቸው በሦስቱ ላይ ለውጥ ማድረግ አስፈልጓቸዋል። መድኖች ከሀዋሳው የአቻ ውጤታቸው ጀማል ጣሰው ፣ ማቲያስ ወልደ አረጋይ እና ኤፍሬም ዘካሪያስን በፋሪስ ዕላዊ ፣ ብዙአየው ስይፉ እናRead More →