ብሔራዊ ቡድን

በሀገራችን የሚካሄደው የሴካፋ ውድድር ሙሉ መርሐ-ግብርን እንደሚከተለው አዘጋጅተነዋል። 41ኛው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከሦስት ቀናት በኋላ በባህር ዳር ከተማ መደረግ ይጀምራል። በውድድሩ ላይ ስምንት የቀጠናው እና አንድ ተጋባዥ ሀገር ተሳታፊ እንደሆኑ የተገለፀ ሲሆን የእጣ ማውጣት መርሐ-ግብሩም በበይነ መረብ አማካኝነት በትናንትናው ዕለት ተከናውኗል። በዚህም ዘጠኙ ብሔራዊ ቡድኖች በሦስት ምድብዝርዝር

በዛሬው ዕለት የምድብ ድልድሉ የወጣው የሴካፋ ውድድር የምድብ ጨዋታዎች የቀን እና ሰዓት መርሐ-ግበር ታውቋል። ዘጠኝ ሀገራትን በሦሰት ምድብ ከፋፍሎ የሚደረገው የሴካፋ ውድድር ከሐምሌ 10 ጀምሮ በባህር ዳር ከተማ መደረግ ይጀምራል። የምድብ ድልድሉ እኩለ ቀን አካባቢ የወጣ ሲሆን አሁን ደግሞ የምድብ ጨዋታዎች ቀን እና ሰዓት ታውቋል። በዚህም መሠረት የውድድሩ የመክፈቻ መርሐ-ግብርዝርዝር

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ የብሔራዊ ቡድኑ ደጋፊዎች ማሊያን በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከወራት በፊት የብሔራዊ ቡድኖቹን ትጥቅ ከሚያቀርበው አምብሮ ጋር ስምምነቱን ማራዘሙ ይታወቃል። ለቡድኖቹ ከሚቀርበው የትጥቅ ስምምነት ጎን ለጎን ፌዴሬሽኑ የደጋፊዎችን መለያ ራሱ አስመጥቶ ለማከፋፈል መወሰኑ ሲገለፅ ነበር። ይህንን ተከትሎ ጉዳዩ ምን ደረጃ ላይ ደረሰዝርዝር

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስፖንሰር የሆነው ዋልያ ቢራ ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት ለመሥራት ከፌዴሬሽኑ ጋር ስምምነት ፈፅሟል። ራሱን በፋይናንስ ለማጠናከር የተለያዩ ስራዎችን እየከወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በዛሬው ዕለት ከሀይኒከን ኢትዮጵያ ጋር በዋልያ ቢራ ምርት በቀጣዮቹ አራት ዓመታት አብሮ ለመስራት ስምምነት ፈፅሟል። ከ11 ሰዓት ጀምሮ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተከናወነው ሥነ-ስርዓት ላይ የኢትዮጵያዝርዝር

ትናንት በአዲስ አበባ የነበራቸውን ዝግጅት ጨርሰው ወደ ባህር ዳር የተጓዙት የኢትዮጵያ ከ 23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አባላት ዛሬ ልምምድ አከናውነዋል። በአቫንቲ ሆቴል መቀመጫውን ያደረገው ብሔራዊ ቡድኑ ከቀኑ 9 ሰዓት በቀዝቃዛማ የአየር ሁኔታ ላይ ልምምዱን የሰራ ሲሆን ቀለል ያለ ልምምድ እንዲሁም ከሁለት ተከፍለው በግማሽ ሜዳ ጨዋታ በማድረግ አከናውነዋል። በዛሬው ልምምድዝርዝር

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከእስራኤል ጋር ባደረገው መልካም ግንኙነት በቅርቡ ወደ ሀገሪቱ ተጉዞ የወዳጅነት ጨዋታ አድርጎ ለተመለሰው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም የኢትዮጵያ እና የእስራኤል ግንኙነት በተመለከተ ዛሬ ከሰዓት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ግብዣን አድርገዋል፡፡ በተጠናቀቀው ወር ላይ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከእስራኤል አቻው ጋር በትምህርት፣ ስልጠና፣ ስፖርት ማኔጅመንት፣ የወዳጅነት ጨዋታዎችንዝርዝር

የፊታችን ቅዳሜ ለሚጀመረው የሴካፋ ውድድር በአዲስ አበባ ሲዘጋጅ የከረመው ብሔራዊ ቡድኑ አንድ ተጫዋች ቀንሶ በምትኩ ለአንድ ተጫዋች ጥሪ በማድረግ አመሻሽ ባህር ዳር ደርሷል። ለ41ኛው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከሰኔ የመጀመሪያ ቀናት አንስቶ ሲዘጋጅ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አመሻሽ ላይ ውድድሩ ወደሚደረግበት ባህር ዳር ከተማ አቅንቷል። እርግጥ ብሔራዊ ቡድኑዝርዝር

ዛሬ ረፋድ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ያደረገው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ነገ ወደ ባህር ዳር ከማምራቱ በፊት ምሽት ላይ አሸኛኘት ተደርጎለታል። በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በሚደረገው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ ጠንካራ ሆኖ ለመቅረብ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል። በሳምንቱ አጋማሽ ከኢትዮጵያ መድህንዝርዝር

በግል ምክንያታቸው ከብሔራዊ ቡድኑ የተገለሉትን ሁለት እንዲሁም በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ የወጡትን ሦስት ተጫዋቾች ለመተካት አሠልጣኝ ውበቱ አባተ አዲስ ጥሪ ለሦስት ተጫዋቾች አቅርበዋል። ከቀናት በኋላ በባህር ዳር ከተማ በሚደረገው የሴካፋ ውድድር ላይ የሚካፈለው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን በካፍ የልዕቀት ማዕከል እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ እያደረገ ይገኛል። በትናንትናውዝርዝር

የኢትዮጵያ እና እስራኤል ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች ሁለተኛ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ዛሬ ተደርጎ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። በኢትዮጵያ እና እስራኤል እግርኳስ ፌዴሬሽኖች እግርኳሳዊ ግንኙነት የተገኘው ሁለት የ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የአቋም መለኪያ ጨዋታ ማክሰኞ እና ዛሬ ተደርጓል። ማክሰኞ አመሻሽ በተደረገው ጨዋታ ላይ ቡድኖቹ ያለ ጎል ነጥብ ተጋርተው መውጣታቸው ሲታወስዝርዝር