የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ በሴካፋ በምክትል ፕሬዝዳንትነት በድጋሜ መመረጣቸው ታውቋል። በምስራቅ እና መካከለኛው ቀጠና የሚገኙ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች የተዋቀረው ሴካፋ በዛሬው ዕለት የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤውን ዛንዚባር ላይ አከናውኗል። በዚህ ጉባኤ ላይም የቀጠናው ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ፕሬዝዳንቶች እና ዋና ፀሐፊዎች የተገኙ ሲሆን ሀገራችንን በመወከልም አቶ ኢሳይያስ ጅራ እና አቶ ባህሩRead More →

በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታውን ያደረገው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዩጋንዳን 1-0 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜው አምርቷል። ሱዳን ላይ እየተደረገ ባለው የሴካፋ ዞን ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ ከዩጋንዳ ጋር ሲያደርግ አሰልጣኝ ዕድሉ ደረጄ ከመጀመሪያው የታንዛኒያ ጨዋታ አንፃር በአሰላለፋቸው ላይ ባደረጉት ለውጥRead More →

በሱዳን አስተናጋጅነት በሚደረገው የሴካፋ ከ20 ዓመት ዋንጫ ጨዋታ ላይ በዳኝነት ግልጋሎት ለመስጠት ሁለት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ወደ ስፍራው አምርተዋል፡፡ በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግርኳስ ተቋም በሆነው (ሴካፋ) አዘጋጅነት ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ በሱዳን አስተናጋጅነት ካርቱም ላይ ይከናወናል፡፡ ሰባት ሀገራትን በተሳታፊነት የሚያቅፈው ውድድሩ ቀደም ብሎ ከተቀመጠለት ቀን በአንድ ሳምንት ተራዝሞ የፊታችን ዕርብRead More →

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች አሠልጣኝ የሆኑት እድሉ ደረጄ ከፊታቸው ላለባቸው የሴካፋ ውድድር ለ48 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል። ግብፅ በምታስተናግደው የ2023 ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሚሆነውን የሴካፋ ዞን ተወካይ ለመለየት እንደ ማጣሪያ የሚያገለግለው የቀጠናው ውድድር በሱዳን አስተናጋጅነት ከጥቅምት 12 እስከ 23 እንደሚደረግ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በምድብ 2Read More →

በመዲናችን አዲስ አበባ በሚከናወነው የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ውድድር ላይ ለሚሳተፈው ብሔራዊ ቡድን የአሠልጣኝ ቅጥር መከናወኑ ይፋ ሆነ። በአልጄርያ አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ለማለፍ ሀገራት የቀጠናቸው ተከፋፍለው የማጣርያ ውድድር የሚያከናውኑ ሲሆን የዚህ አካል የሆነው የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ውድድር በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከመስከረም 20 ጀምሮ ይከናወናል። በዚህ ውድድርRead More →

የቀጠናው ክለቦችን የሚያሳትፈው የሴካፋ ካጋሜ ካፕ የዘንድሮ ውድድር እንደማይደረግ የውድድሩ የበላይ አካል አስታውቋል። 1974 በይፋ እንደተጀመረ የሚነገረው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ የክለቦች ውድድር ከ2002 ጀምሮ በሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ስፖንሰር አድራጊነት ካጋሜ ካፕ በሚል ስያሜ እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል። በዞኑ የሚገኙ የሊግ አሸናፊዎችን ነገርግን እንደየሀገራቱ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች የውስጥ አሰራር የጥሎ ማለፍRead More →

ለተከታታይ አስር ቀናት ሲደረግ የነበረው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ በአስተናጋጇ ሀገር ዩጋንዳ ቻምፒዮንነት ተጠናቋል፡፡ በስምንት የቀጠናው ሀገራት መካከል በሁለት ምድብ ተከፍሎ ለአስር ተከታታይ ቀናት ሲደረግ የነበረው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ በአስተናጋጇ ሀገር ዩጋንዳ አሸናፊነት ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ በምድብ አንድ ላይ ተደልድለው የነበሩትን ዩጋንዳን እና ብሩንዲን ዳግም ያገናኘውን የዛሬውን ጨዋታ ለመታደም የዩጋንዳ ከፍተኛ የመንግሥትRead More →

በሴቶች የሴካፋ ዋንጫ ኢትዮጵያ ታንዛኒያን 2ለ1 በመርታት የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች፡፡ የሉሲዎቹ አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል በ4-3-3 የተጫዋች አደራደር ቅርፅ በዩጋንዳ 1ለ0 ከተረቱበት ቋሚ አሰላለፍ ረድኤት አስረሳኸኝን ወደ ተጠባባቂ በማውረድ በምትኩ ቱሪስት ለማን በቀዳሚው አሰላለፍ ተጠቅመዋል፡፡ በምድብ ጨዋታ ተገናኝተው 2ለ2 በሆነ ውጤት ተለያይተው የነበሩት ታንዛኒያ እና ኢትዮጵያ በዛሬው ጨዋታቸው የመጀመሪያው አጋማሽRead More →

መቶ ሀያ ደቂቃዎችን የፈጀው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዩጋንዳን አሸናፊ በማድረግ ተጠናቋል። ለፍፃሜ የሚያልፈውን ቡድን ለመለየት ስድስት ሰዓት ሲል የዩጋንዳ እና ኢትዮጵያ ጨዋታ ጅምሩን አድርጓል፡፡ ሉሲዎቹ በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታቸው ከደቡብ ሱዳን ጋር ተገናኝተው ድል ሲያደርጉ ከተጠቀመው ቋሚ አሰላለፍ ግብ ጠባቂዋ እምወድሽ ይርጋሸዋን በታሪኳ በርገና እንዲሁም ናርዶስ ጌትነትን በኝቦኝRead More →

በሴካፋ ውድድር ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የምድቡ ሁለተኛ ሆኖ ወደ ግማሽ ፍፃሜው አልፏል። በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ስምንት ብሔራዊ ቡድኖችን ተሳታፊ በማድረግ ካሳለፍነው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ እየተከናወነ የሚገኘው የሴቶች የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ትናንት እና ዛሬ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎቹን አከናውኖ ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉ 4 ቡድኖችን ለይቷል።Read More →