ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት የቻን ውድድር የምድብ እጣ ማውጣት መርሐ-ግብር የሚከናወንበት ቀን ተገልጿል። በ2023 በአልጄሪ አስተናጋጅነት የሚከናወነው የቻን ውድድር ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳታፊዎችን ቁጥር አሳድጎ በ18 ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ከጥር 5 -27 ድረስ እንደሚከናወን ይታወቃል። በየቀጠናው በተከናወኑ የማጣሪያ ውድድሮች ሞሮኮ፣ ሊቢያ፣ ሴኔጋል፣ ሞሪታኒያ፣ ማሊ፣ ኒጀር፣ ጋና፣ አይቮሪኮስት፣ ኮንጎ፣ ዲ አር ኮንጎ፣Read More →

ያጋሩ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዩጋንዳ ጋር ባደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ጉዳት የገጠመው ተከላካዩን በሌላ ተጫዋች ተክቷል። በአልጄርያ አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የቻን ውድድር የመጨረሻ የማጣርያ ጨዋታው ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ አቻው ጋር ነሐሴ 20 እና 29 ለሚኖረው ወሳኝ ጨዋታ ይረዳው ዘንድ ባሳለፍነው ሳምንት ሁለት የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችን ከዩጋንዳ አቻው ጋር ማድረጉRead More →

ያጋሩ

ታንዛኒያ ላይ የቻን የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአዳማ ከተማ ልምምድ ማድረግ ከጀመረ ሁለተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል፡፡ በአልጄሪያ አዘጋጅነት ለሚደረገው የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳታፊ ለመሆን የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከደቡብ ሱዳን ጋር የደርሶ መልስ መርሃግብሩን በታንዛኒያ የሚያከናውነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን እየከወነ ነው። የብሔራዊRead More →

ያጋሩ

ሐምሌ 15 እና 21 በቻን ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የሚገጥሙት ደቡብ ሱዳኖች የመጨረሻ ስብስባቸውን ይፋ አድርገዋል። በአልጄሪያ አስተናጋጅነት በሚከናወነው የቻን ውድድር ላይ የሚሳተፉ ብሔራዊ ቡድኖችን ለመለየት የማጣሪያ ጨዋታዎች ከቀናት በኋላ መደረግ ይጀምራሉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ለሁለቱ ጨዋታዎች ይህንን ዘገባ በምንሰራበት ሰዓት የመስክ ላይ ልምምዱን ማድረግ ጀምሯል። ተጋጣሚው ደቡብ ሱዳን በበኩሏRead More →

ያጋሩ

በቻን ማጣሪያ ከኢትዮጵያ ጋር የምትፋለመው ደቡብ ሱዳን በትናንትናው ዕለት ዝግጅቷን ጀምራለች። በሀገር ውስጥ ሊግ ብቻ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት የቻን ውድድር በቀጣዩ ዓመት በአልጄሪያ እንደሚከናወን ይታወቃል። በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ብሔራዊ ቡድኖችን ለመለየት ደግሞ ከቀናት በኋላ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች የሚጀምሩ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም የመጀመሪያ ማጣሪያዋን ከደቡብ ሱዳን ጋር ታከናውናለች። ሐምሌ 14Read More →

ያጋሩ

ከደቡብ ሱዳን ጋር የቻን ማጣሪያ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስቡን ይፋ አድርጓል። በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የቻን የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን ጋር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ እንደሚጠብቀው ይታወቃል። ሐምሌ 15 እና 24 ለሚደረጉት እነዚህ ሁለት ጨዋታዎች የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጨዋቾች ጥሪ ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋRead More →

ያጋሩ

የካፍ የስታዲየም መመዘኛ መስፈርት አለማሟላቱን ተከትሎ የሜዳ ላይ ጨዋታዎቹን ከሀገር ውጪ እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን ጋር የቻን ማጣሪያ ጨዋታውን የሚያደርግበት ሀገር ይፋ ሆኗል፡፡ በሀገር ውስጥ ተጫዋቾች ብቻ በካፍ አዘጋጅነት በየሁለት አመቱ የሚደረገው የቻን የአፍሪካ ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች በያዝነው ዐመት ነሀሴ ወር ላይ ይከውናሉ፡፡ በማጣሪያው ከደቡብ ሱዳንRead More →

ያጋሩ

በካሜሩን አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የቻን ውድድር ነገ የሚካሄደውን ጨዋታ ኢትዮጵያዊቷ ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በመሐል ዳኝነት ትመራዋለች።  ባሳለፍነው ቅዳሜ የተጀመረው የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ውድድር የምድብ ጨዋታዎች እየተካሄዱበት ሲሆን ቅዳሜ በሚደረገው የናሚቢያ እና ታንዛንያ ግጥሚያ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታዎች ይጠናቀቃሉ። ምሽት 4:00 ላይ በሊምቤ ስታዲየም የሚደረገውን ይህን ጨዋታም ብቸኛዋ የውድድሩ ሴትRead More →

ያጋሩ

በካሜሮን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የቻን ውድድር እና ተዛማጅ ጉዳዮች የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ ለሳምንታት ቆይታ ወደ ካሜሩን አቅንተዋል። በሀገር ውስጥ ሊጎች ተጫዋቾች ብቻ የሚካሄደው የቻን ውድድር በኮሮና ሻይረስ ምክንያት በ2020 መካሄድ ሲገባው ተገፍቶ ከቀናት በኋላ በካሜሩን አስተናጋጅነት እንደሚካሄድ ይታወቃል። በዚህ ውድድር በክብር እንግድነት ተጋብዘው ፕሬዝደንት ኢሳያስ ጅራ በትናትናው ዕለት ወደRead More →

ያጋሩ

ኢትዮጵያዊቷ ጠንካራ ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በ2021 ለሚደረገው የቻን ውድድር ላይ ከሚመሩ 19 ዳኖች ውስጥ ብቸኛዋ ሴት የመሐል ዳኛ ሆና ተካታለች።  ካፍ ከወራት በፊት በካሜሩን አስተናጋጅነት ሊካሄድ በነበረው የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ውድድር ላይ ጨዋታዎችን እንዲመሩ ለቅድመ ስልጠና ከመረጣቸው ዳኞች መካከል ሊዲያ አንዷ የነበረች ሲሆን በመጨረሻው ዝርዝር ውስጥ ከተመረጡ 19 የመሐልRead More →

ያጋሩ