ከጊኒ ጋር ሁለት ጨዋታዎች የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከፍልሚያዎቹ በፊት ሀገሩ ላይ የአቋም መለኪያ ጨዋታ እንደሚያደርግ ተገልጿል። በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጋቢት 15 እና 18 ከጊኒ ጋር ወሳኝ ሦስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎች ይጠብቀዋል። ለእነዚህ ፍልሚያ የቡድኑ አሠልጣኝ ውበቱ አባተRead More →

ከቀናት በኋላ ከሱዳን ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ የሚያደርገውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ለይተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊፋ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ወቅትን በመጠቀም ከሱዳን ብሄራዊ ቡድን ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ለማድረግ ከጫፍ እንደደረሰ ሶከር ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት ዘገባ ሰርታ ነበር። ከሱዳን ብሔራዊ ፌዴሬሽን ባገኘነው መረጃም ብሔራዊ ቡድኑ ለ24 ተጫዋቾችRead More →

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሁለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ለማድረግ ቀጠሮ የያዘችው ሱዳን ለፍልሚያዎቹ ስብስቧን ለይታለች። የሀገራት ይፋዊ ጨዋታዎች ከቀጣዩ ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ የሚከናወኑ ሲሆን የነጥብ ጨዋታዎች የሌለባቸው ብሔራዊ ቡድኖችም የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማድረግ እየተሰናዱ ይገኛሉ። ሶከር ኢትዮጵያም ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዚህ የቀን ሰሌዳ ከሱዳን ጋር ጨዋታ ለማድረግ እየተነጋገረ እንደሆነናRead More →

በመጪው የዓለም አቀፍ ጨዋታዎች የጊዜ ሰሌዳ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአቋም መለኪያ ጨዋታ እንዲያገኝ የተጀመረው ንግግር ለመሳካት ከጫፍ ደርሷል። የዓለም አቀፍ የብሔራዊ ቡድኖች አህጉራዊ ጨዋታዎች እና የአቋም መፈተሻ ፍልሚያዎች ከቀጣዩ ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ እንደሚከናወን ይታወቃል። በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የነጥብ ጨዋታ የሚያደርግበት መርሐ-ግብር ባይኖረውም ወቅታዊ አቋሙን እንዲገመግም የኢትዮጵያRead More →

በሁለት ቀናት ልዩነት ዋልያዎቹን በአቋም መፈተሻ ጨዋታ የገጠመው የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ሰርዲዮቪች ሚሉቲን “ሚቾ” ከዛሬው ፍልሚያ በኋላ አስተያየት ሰጥተዋል። ጨዋታው እንዴት ነበር..? “በቅድሚያ ይህን ከአፍሪካ ዋንጫ እና ዓለም ዋንጫ ማጣርያው ስብስብ አቡበከር ናስር እና ሽመልስ በቀለ የጎደሉትን ቡድን መግጠም ቀላል አይደለም ፤ ቡድኑ ግብፅን ማሸነፉ በራሱ ብዙ የሚናገረው ነገርRead More →

አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ቡድናቸው ከዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሁለተኛ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ አከናውኖ 0ለ0 ከተለያየ በኋላ ተከታዩን የድህረ-ጨዋታ አስተያየት ሰጥተዋል። ጨዋታው እንዴት ነበር? “ይህ ጨዋታ በሁለት ቀን ልዩነት ያደረግነው ነው። ቢሆንም ለቀጣይ ጨዋታ ቡድናችንን በደንብ እንድናይበት ረድቶናል። በሁለት ቀን መካከል ሪከቨር ማድረግ ትንሽ ከባድ ነው። ይህ ቢሆንም ግን ከሜዳው አንፃርRead More →

አመሻሽ ላይ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ያከናወነው የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ሰርዲዮቪች ሚሉቲን ተከታዩን የድህረ-ጨዋታ አስተያየት ሰጥተዋል። ጨዋታው እንዴት ነበር? “በመጀመሪያ የዛሬውን እና የእሁዱን ጨዋታ እንድናደርግ ቀድመው ሀሳቡን ያመጡትን አቶ ኢሳይያስ ጂራ እና ውበቱ አባተን ማመስገን እፈልጋለው። ይሄ ለእኛ ብዙ ማለት ነው። እኔ በግሌ የማስበው በእግር ኳስRead More →

👉”በሁለቱም ጨዋታዎች ለቀዳሚ አሰላለፍ የተጠጋውን ስብስብ በማሰለፍ ማሸነፍ ይቻላል ፤ ግን… 👉”በጨዋታው ከውጤት ይልቅ ተጫዋቾቹን ለማየት ነው የሞከርነው 👉”ስህተቶች በእንደዚህ አይነት ጨዋታዎች ነው እየፀዱ የሚሄዱት 👉”ከሌሶቶ ጋር ያለን አቀራረብ ከግብፅ ወይም ከማላዊ ጋር ይኖረናል ማለት አይደለም ጨዋታው እንዴት ነበር ? “ከውጤት አንፃር ከታየ ጨዋታው አንድ ለአንድ ነው የተጠናቀቀው። ይሄ ብቻRead More →

አዳማ ላይ ከሌሶቶ አቻው ጋር ሁለተኛ የአቋም መፈተሻ ጨዋታውን ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አንድ አቻ ተለያይቷል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በሁለቱ አጋማሾች ሁለት መልክ የነበረው ነበር። በመጀመሪያው አጋማሽ የአሠልጣኝ ውበቱ አባተ ተጫዋቾች ብልጫ ወስደው ለመንቀሳቀስ ሲሞክሩ ቢታይም በ3ኛው ደቂቃ ግብ ሊያስተናግዱ ነበር። በዚህም በ3ኛው ደቂቃ ጊትጋት ኩት ለግብ ጠባቂው በረከት አማረRead More →

በነገው ዕለት ከዋልያው ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ የሚያደርገው የሌሶቶ ብሔራዊ ቡድን ከደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ ደርሷል። የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ከቀናት በኋላ እንደሚጀምሩ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ከማላዊ እና ግብፅ ጋር ላሉበት ጨዋታዎች ዝግጅቱን ከትናንት በስትያ የጀመረ ሲሆን ከፍልሚያቹ በፊት ያለበትን አሁናዊ አቋም ለማወቅ ነገ እና ሰኞ ከሌሶቶRead More →