ብሔራዊ ቡድን (Page 2)

የ55 ዓመቱ የዚምባብዌ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ዝድራቭኮ ሎጋሩሲች በነገው ዕለት ቡድናቸውን የኢትዮጵያ አቻውን ከመግጠሙ በፊት ለጋዜጠኞች አስተያየት ሰጥተዋል። ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ የተደለደለው የዚምባቡዌ ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን ለማከናወን በትናንትናው ዕለት ባህር ዳር እንደደረሰ ይታወቃል። ብሔራዊ ቡድኑን የሚያሰለጥኑን ክሮሺያዊው የ55 ዓመት አሠልጣኝ ዝድራቭኮ ሎጋሩሲችዝርዝር

👉”በጋናው ጨዋታ በመሸነፋችን ተጫዋቾቹም ሆነ የአሠልጣኝ ቡድን አባላቱ ቅር ተሰኝተናል” ውበቱ አባተ 👉”በተክለማርያም ምክንያት አይደለም የተሸነፍነው። በጨዋታው የተሸነፍነው ጎል ማግባት ስላልቻልን ነው” ውበቱ አባተ 👉”ተጫዋቾቹ በጥሩ የራስ መተማመን ላይ ነው የሚገኙት” ጌታነህ ከበደ 👉”ነገ የሜዳችን ጨዋታ ስለሆነ አሸንፈን ለመውጣት የማጥቃት ሀይላችንን አሻሽለን እንገባለን” ውበቱ አባተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝዝርዝር

በነገው ዕለት በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የሚያደርጉት የኢትዮጵያ እና ዚምባቡዌ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከጨዋታው በፊት የመጨረሻ ልምምዳቸውን አከናውነዋል። ኳታር ለምታስተናግደው የ2022 የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታዎችን ከደቡብ አፍሪካ፣ ዚምባቡዌ እና ጋና ጋር ተደልድሎ እያከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሦስት ቀናት በፊት ወደዝርዝር

በነገው ዕለት ከሴራሊዮን ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ አመሻሽ ሰርቷል። በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ዓመት ለሚከናወነው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከደቡብ አፍሪካ፣ ጋና እና ዚምባቡዌ ጋር እንደተደለደለ ይታወቃል። የአፍሪካ ተወካይ ቡድኖችን የሚለዩት የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ከአንድ ሳምንት በኋላ ሲጀምሩ ዋልያውም ወደዝርዝር

የፊታችን ሀሙስ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ የሚያደርገው የሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድን ዋልያውን የሚገጥምበትን ስብስብ ይፋ ሲያደርግ አዲስ አበባ የሚገባበትም ሰዓት ታውቋል። በአሠልጣኝ ጆን ኬይስተር የሚመራው የሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድን በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አስተናጋጅነት ለሦስት ቀናት በሚከናወነው ውድድር ላይ ተሳታፊ እንደሚሆን ይታወቃል። ብሔራዊ ቡድኑ ከፊቱ ላለበት ንዑስ ውድድር አቋሙን ለመፈተሽዝርዝር

ባሳለፍነው ሳምንት የወጣውን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድልን በተመለከተ አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ገለፃ አድርገዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ቡድኑ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች እያደረገ ያለውን ዝግጅት አስመልክቶ ዛሬ ከሰዓት በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ መግለጫ ሰጥተዋል። ዝግጅታቸውን በተመለከተ የተነሳውን ሀሳብ ከደቂቃዎች በፊት ያስነበብን ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንትዝርዝር

👉”እኔ ወደ ቡድኑ ከመጣው ጀምሮ ለመገንባት የምንፈልገው ነገር አለ” 👉”የቡድኑ 70 እና 75 በመቶ የሚሰለፉ ተጫዋቾች ስለሚታወቁ ያን ያህል ጫና አይፈጠርም” በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኳታር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2022 ዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከደቡብ አፍሪካ፣ ጋና እና ዚምባቡዌ ጋር እንደተደለደለ ይታወቃል። ብሔራዊ ቡድኑ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በውድድሩ ለመሳተፍምዝርዝር

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅት አካል የሆኑ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን እንደሚያደርግ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነሐሴ 28 ከጋና (ከሜዳው ውጪ) እንዲሁም ጳጉሜ 2 ከዚምባብዌ (በሜዳው) በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የ2022 የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጉዞውን የሚጀምር ሲሆን ለእነዚህ የማጣርያ ጨዋታዎችም በአዳማ ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ። በቀጣይ ሳምንት ደግሞ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችንዝርዝር

ለካታሩ የ2022 ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመርያ ሁለት ጨዋታዎቿን በዓመቱ መጨረሻ የምታከናውነው ኢትዮጵያ ጨዋታ የምታደርግባቸው ቀናትን አውቃለች። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው በምድብ 7 ከጋና፣ ዚምባብዌ እና ደቡብ አፍሪካ ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ የመጀመርያ ጨዋታዋን ነሐሴ 28 ወደ ጋና አምርታ የምታከናውን ሲሆን ቀጣዩን ጨዋታ ጳጉሜ 2 ላይ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ዚምባብዌንዝርዝር

በቀን ሁለት ጊዜ ዝግጅታቸውን እያደረጉ የሚገኙት ዋልያዎቹ ዛሬም መደበኛ ልምምዳቸውን ሲሰሩ ተመልክተናል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ለሚያከናውናቸው ሁለት የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች መቀመጫውን ከአዲስ አበባ 90 ኪሎ ሜትር ዕርቃ በምትገኘው አዳማ ከተማ በማድረግ ዝግጅት ከጀመረ ቀናቶች ተቆጥረዋል። ዛሬ ከ10:00 ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የቡድኑ አባላት በተሟላ ሁኔታዝርዝር