U-20 (Page 2)

በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሚመራው የኢትዮጵያ ከ20ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የመጀመርያ ተመራጭ ሠላሳ ተጫዋቾቹን አሳውቋል። ከህዳር 22-ታኅሣሥ 6 በታንዛኒያ አስተናጋጅነት የሚደረገው ከ20 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆነውና ከኬንያ እና ሱዳን ጋር የተደለደው ቡድኑ በዛሬው ዕለት ለሠላሳ ተጫዋቾች ጥሪ አቅርቧል። ይህን ተከትሎም ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በመገኘት የኮቪድ ምርመራ ያካሄዱዝርዝር

ከዚህ ቀደም ብለን በተለያዩ የዕድሜ እርከኖች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ያገለገለው እና በክለብ ደረጃ ጉና ንግድ፣ ኢትዮጵያ መድን፣ ሐራር ቢራ እና ሜታ ቢራ የተጫወተው የአጥቂ አማካዩ እና ጨዋታ አዋቂው ሚካኤል አብርሀ የወጣቶች አፍሪካ ዋንጫ ትውስታውን ወደ እናንተ ማቅረባችን ይታወሳል አሁን ደግሞ ከውድድሩ በፊት በኬንያ ያጋጠመውን አቅርበንላችኃል። ኢትዮጵያ ካዘጋጀችው የወጣቶች አፍሪካ ዋንጫዝርዝር

በልዩ የኳስ አገፋፍ ብቃቱ ይታወቃል። በእግርኳስ ሕይወቱ ለወጣት እና ለዋናው ብሄራዊ ቡድን ተጫውቷል። በክለብ ደረጃ ለጉና ንግድ፣ መድን፣ ባንኮች፣ ሐረር ቢራ፣ እና ሜታ ቢራ የተጫወተው ይህ ተጫዋች በኢትዮጵያ በተዘጋጀው የወጣቶች አፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ የነበረው ስብስብ አካል ነበር። ኢትዮጵያ በካሜሩን በተሸነፈችበት የመክፈቻ ጨዋታም በመጨረሻው ደቂቃ ላይ ተከላካይ እና ግብ ጠባቂ በአስደናቂዝርዝር

* የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች እሁድ ይደረጋሉ ከአንድ ሳምንት በፊት የተጀመረው እና በሰፊ ውጤት በተጠናቀቁ ጨዋታዎች ዛሬ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች ያስተናገደው የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ወደ ሩብ ፍፃሜ ያለፉ ሀገራትን ለይቷል። ጠባብ የማለፍ ዕድል በመያዝ ወደ ጨዋታው ያመራችው ሃገራችን ኢትዮጵያ በኬንያ 4-0 ተሸንፋ ካለ ምንም ነጥብ ከውድድሩ ውጭ ሆናለች። የኬንያዝርዝር

*ኢትዮጵያ ነገ የመጨረሻ ዕድሏን ትሞክራለች የሴካፋ ከ20 ዓመት ዋንጫ ዛሬም በአምስተኛ ቀን ጨዋታ ሲቀጥል ሦስት ጨዋታዎች ተካሂደው ኤርትራና ደቡብ ሱዳን ድል ሲያደርጉ ወደ ሩብ ፍፃሜ ያለፉ ተጨማሪ ሀገራት ታውቀዋል። በኤርትራ ዋናው ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዓለምሰገድ ኤፍሬም እየተመሩ ላለፉት ስምንት ወራት ዝግጅት ያደረጉት የቀይ ባሕር ግመሎች ጅቡቲን 7-0 በማሸነፍ ወደ ሩብዝርዝር

የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ በዩጋንዳ አስተናጋጅነት እየተደረገ ሲገኝ ኢትዮጵያም ከምድብ ሁለት ባደረገቻቸው ሁሀለቱም ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዳ ወደ ሩብ ፍፃሜ የመግባቷ ሁኔታ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። በምድብ ሁለት ከዛንዚባር ታንዛኒያ እና ኬንያ ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ በታንዛኒያ 4-0 ትላንት ደግሞ በዛንዚባር 2-1 በመሸነፍ ከኬንያ ጋር የምታደርገው የመጨረሻ ጨዋታ እየቀራት ከውድድሩ መሰናበቷን መመረጋገጧንዝርዝር

የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ አራተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ሲካሄዱ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ሽንፈቷን አስተናግዳለች። ኬንያ እና ታንዛንያም ነጥብ ተጋተርዋል። አስቀድሞ የተከናወነው የኢትዮጵያ እና ዛንዚባር ጨዋታ በዛንዚባር 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ኢትዮጵያ ከመጀመርያው ጨዋታ ለውጦችን በማድረግ በተለይም በቻን ማጣርያ ሩዋንዳን በገጠመው ስብስብ የመጀመርያ ተሰላፊ የነበረው መስፍን ታፈሰን ብትጠቀምም በደካማዋ የእግርኳስ ሀገር ሽንፈትዝርዝር

ከነሀሴ 27 ጀምሮ በአዳማ ከተማ ዝግጅቱን ሲያደርግ የቆየው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ላይ ለመካፈል 26 የልዑካን አባላትን በመያዝ ወደ ዩጋንዳ አምርቷል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የምስራቅ አፍሪካን የእግር ኳስ ደረጃ ከፍ ያደርጋል የተባለለት ይህ የታዳጊዎች ውድድር ነገ በአስተናጋጇ ከተማ ካምፓላ ይጀመራል፡፡ በአሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ እየተመራዝርዝር

በዩጋንዳ አስተናጋጅነት የፊታችን ዕሁድ በካምፓላ በሚጀመረው የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ላይ ተካፋይ የሆነው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአዳማ ከተማ ዝግጅቱን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ አስራ አንድ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በሚሳተፉበት በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከኬንያ፣ ዛንዚባር እና ታንዛኒያ ጋር ከቀናት በፊት በወጣው ዕጣ መሠረት የተደለደለች ሲሆንዝርዝር

ዩጋንዳ ለምታዘጋጀው የሴካፋ ከ 20 ዓመት በታች የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል። በውድድሩ ተሳታፊ ለመሆን በዝግጅት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከኬንያ ፣ ታንዛንያ እና ዛንዚባር የተመደበች ሲሆን በአሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ እየተመራ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው ቡድኑ ከሰባት ቀናት በኋላ በሚጀምረው ውድድር ላይ ለመሳተፍ ከቀናት በኃላ ወደ ዩጋንዳ ያመራል። ባለፈው ማክሰኞ ኒኮላስዝርዝር