በሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ዋንጫ ኢትዮጵያ ቡና በቲፒ ማዜንቤ 3-1 በተረታበት ጨዋታ ባሳየው ያልተገባ ባህርይ ከደጋፊዎችና አሰልጣኝ ስታፉ ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ ገብቶ የነበረው እና ላልተወሰነ ጊዜ ታግዶ የቆየው አጥቂው ሙሉአለም ጥላሁን ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያለውን ውል አፍርሶ ለመከላከያ መፈረሙን ፕላኔት ስፖርት ዘግቧል፡፡  ሙሉአለም ውሉን ማፍረሱን ተከትሎ የቀድሞ ክለቡ ኢትዮጵያ መድንንRead More →

እስካሁን በተካሄዱት የ9 ሳምንት ጨዋታዎች ላይ ተሞርኩዞ የቅዱስ ጊዮርጊስን የበላይነት ፣ የክልል ክለቦችን እንቆቅልሽ ፣ የደደቢትን ፈተና ፣ የግብ ድርቅን እና የፀጋዬ/ንግድ ባንክን ጥምረት በማንሳት አብርሃም ገ/ማርያም የፕሪምየር ሊጉ የ9 ሳምንታት ጉዞ ምን እንደሚመስል ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡ ደደቢት የአምና ክብሩን የማስጠበቅ ፈተና በሊጉ እስካሁን 6 ጨዋታ ብቻ ያደረገን ክለብ ካሁኑ ከዋንጫRead More →

የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ ፍፁም ገ/ማርያም ለተጨማሪ ህክምና አሜሪካ ተጉዞ ከ26 ቀናት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ወደ ክለቡ ተመልሶ ልምምድ መጀመሩ ተነግሯል፡፡  በከባድ ጉዳት ከሜዳ ርቆ የሰነበተው የቀድሞ የሙገር ሲሚንቶ አጥቂ መመለስ በኡመድ ኡኩሪ ላይ ጥገኛ ለሆነው የአሰልጣኝ ማርቲን ኑይ የአጥቂ ክፍል አማራጭ ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በተመሳሳይ ለረጅም ጊዜያት ጉዳት ላይ የነበረውRead More →

የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የ2014 የውድድር ዘመን ድልድል ይፋ ሲሆን ደደቢት ተጋጣሚውን አውቋል። የአምናው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮን በቅድመ ማጣርያው ከዛንዚባሩ ሻምፒዮን ኬ ኤም ኤም ኬ ጋር ተደልድሏል፡፡ የመጀመርያው ጨዋታን ከሜዳው ውጪ የሚያደርገው ደደቢት የመልሱን በሜዳው የሚያከናውን መሆኑ ወደ ተከታዩ ዙር ለማለፍ ምቹ አጋጣሚ ይፈጥረለታል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ድልድል በፅፅር ቀለልRead More →

የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የ2014 የውድድር ዘመን ድልድል ይፋ ሲሆን መከላከያም ተጋጣሚውን አውቋል። ቅዱስ ጊዮርጊስን በመላያ ምቶች አሸንፎ የ2005 የኢትዮጵያ ዋንጫ (ጥሎማለፍ) ቻምፒዮን የሆነው መከላከያ የ2014 የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመርያ ጨዋታውን ከኬንያው ሊዮፓርድስ ጋር ያደርጋል፡፡ ሰኞ ከቀትር በኋላ በወጣው ድልድል መሰረት መከላከያ የመጀመርያ ጨዋታውን ኬንያ ላይ ሲያደርግ የመልሱን ጨዋታ አአ ላይ ያደርጋል፡፡ Read More →

ከ10 ቀናት በኃላ በደቡብ አፍሪካ አዘጋጅነት ለሚደረገው የሃገር ውስጥ ሊግ ውስጥ የሚገኙ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት ቻን ውድድር እየተዘጋጀች የምትገኘው ኢትዮጵያ የመጨረሻ 23 ተጫዋቾችን አሳውቃለች ፡፡ በመጀመርያው የ27 ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ ያልነበረው አበባው ቡታቆ በስብስቡ ውስጥ ውስጥ ሲካተት ግብ ጠባቂው ሲሳይ ባንጫ ከምርጫው ተዘሏል፡፡ ግልፅ ምክንያት ባይቀርብም የደደቢቱ ግብ ጠባቂ ራሱንRead More →

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለወትሮው ለትልልቅ ውድድሮች ቢያንስ አንድ ወር ዝግጀት የማድረግ ልማድ ቢኖረውም በ2014 መጀመርያ በሀገር ውስጥ ሊግ ውስጥ በሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ በሚዋቀር ስብስብ ለሚደረገው ውድድር (ቻን) እስካሁን ዝግጅት አልጀመረም፡፡ ውድድሩ ሊጀመር የ23 ቀናት እድሜ የቀሩት ቢሆንም ኢትዮጵያ እስካሁን ተጫዋቾቿን አላሳወቀችም (በምድባችን የምትገኘው ጋና ከወዲሁ 23 ተጫዋቿን አሳውቃለች)፡፡ አሰልጣኝ ሰውነትRead More →

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ትናንት እና ዛሬ ተካሂዶ ለቀጣዮቹ 40 ቀናት ተቋርጧል፡፡ ቅዳሜ እለት በተካሄደው ብቸኛ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኤልያስ ማሞ ብቸኛ ግብ ኢትዮጵያ መድንን 1-0 አሸንፎ ነጥቡን 18 አድርሷል፡፡ ጨዋታው ብዙም ሳቢ ያልነበረ እና በሙከራዎች ያልታጀበ ሲሆን ኤልያስ ማሞ ግብ ከማስቆጠሩ በፊት ፊሊፕ ዳውዚ ከርቀት አክርሮ የመታውናRead More →

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የብሔራዊ ቡድኑ አባላት በሆኑት አበባው ቡጣቆ እና ሲሳይ ባንጫ ላይ ቅጣት ማስተላለፉን ዛሬ በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ በአለም ዋንጫ ማጣርያ የመጨረሻ ጨዋታ የመልስ ግጥሚያ ላይ የተሰለፉት ሁለቱ ተጫዋቾች በናይጄሪያ ካላበር በነበሩበት ወቅት ሁለቱ ተጫዋቾች መጣላታቸውን መሰረት በማድረግ ነው ቅጣት የተላለፈባቸው፡፡ የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ ክፍል 3Read More →

በናይጀሪያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዋና ከተማዋ አቡጃ የፊታችን ታህሳስ 27 ቀን እንዲከናወን የታሰበው ጨዋታ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኩል ተቀባይነት አግኝቷል። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወደ አቡጃ ለሚያደርገው ጉዞ የትራንስፖርት ወጭ ብቻ የሚሸፍን ሲሆን ፥ ሌሎች ወጭዎች በናይጀሪያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አማካኝት የሚሟሉ ይሆናል። ጨዋታው የሚከናወነው የሃገር ውስጥRead More →