የአርባምንጭ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ደጋፊዎች በፈፀሙት ያልተገባ ድርጊት ቅጣት ሲተላለፍባቸው የሳምንቱ ውሳኔዎችም ተያይዘው ወጥተዋል። የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር እና ሥነ ስርዓት ኮሚቴ በሊጉ የ25ኛ ሳምንት ጨዋታዎችን ተንተርሶ ከዳኞች እና ከጨዋታ ታዛቢዎች የደረሰውን መረጃ ዋቢ በማድረግ በታዩ የዲሲፕሊን ግድፈቶች ላይ በክለቦች እና ተጫዋቾች ላይ ቅጣትን ጥሏል። ድሬደዋ ከተማ ወልቂጤንRead More →

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት መርሐግብሮች መካከል የአንድ ጨዋታ ውጤት በጊዜያዊነት እንዳይፀድቅ ሲወሰን ሁለት ክለቦች ቅጣት አስተናግደዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ቅዳሜ ግንቦት 05 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል። በተጫዋቾች ደረጃRead More →

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከማላዊ ጋር የሚያደርገው የሜዳው ጨዋታን የሚያደርግበት ሀገር ታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምስተኛውን የምድብ ጨዋታ ሰኔ 13 (June 20) ለማከናወን ሞዛምቢክን ምርጫው ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለካፍ አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ ይፋ እንዳደረገው በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በሚገኙ ስታዲየሞች ላይ ለማከናወን ጥረት ቢያደርግም ሩዋንዳ ከዚህ በፊት ተፈቅዶላትRead More →

በአዳማ ከተማ በተካሄዱ የ17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መነሻነት በሊጉ አስተዳዳሪ በተወሰዱ የዲስፕሊን እርምጃዎች ሁለት ተጫዋቾች እና አንድ ክለብ ተቀጥተዋል። በድሬዳዋ አንድ ጨዋታ ብቻ የተደረገበት የፕሪምየር ሊጉ 17ኛ ሳምንት በአዳማ ቀጥለው በተደረጉ ጨዋታዎች መጠናቀቁ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎም በሰባቱ ጨዋታዎች ላይ የታዩ የዲሲፕሊን ጥሰቶችን ከዳኞች እና ኮሚሽነሮች የደረሰውን ሪፖርት ተከትሎ የሊጉ የውድድር እናRead More →

በ16ኛው ሳምንት የተደረጉ ጨዋታዎችን ተከትሎ የሊጉ አወዳዳሪ አካል ባስተላለፋቸው ውሳኔዎች ሱራፌል ዳኛቸው እንዲሁም የሲዳማ ቡና እና ወላይታ ድቻ አሰልጣኝ ቡድን አባላት ጠንከር ያለ ቅጣት አግኝቷቸዋል። የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና እና ስነ ሥርዐት ኮሚቴ በያዝነው ሳምንት ተደርገው በተጠናቀቀቁ የ16ኛ ሳምንት የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች ላይ ግድፈት በታየባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የቅጣትRead More →

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ትናንት እና ዛሬ የተራዘሙት አራት ጨዋታዎች የሚደረጉበት ቀን እና ሰዓት በይፋ ተገልጿል። ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ15ኛ ሳምንት መርሐግብር የመጨረሻ ሁለት ቀናት እንዲደረጉ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩት አራት ጨዋታዎች በድሬዳዋ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት መራዘማቸው ይታወሳል። የሊጉ አክሲዮን ማህበር ውድድር እና ሥነስርዓት ኮሚቴ እነዚህን ጨዋታዎች አስመልክቶ ስብስባRead More →

ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ሆነዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ለመቅጠር የስራ ማስታወቂያ ማውጣቱ የሚታወስ ሲሆን መስፈርቱን ያሟሉ አምስት ተወዳዳሪዎችም ባለፈው ሳምንት በጁፒተር ሆቴል ለውድድር የቀረበውን የአንድ ዓመት የእግር ኳስ ልማት እቅድ አዘጋጅተው ገለፃ አድርገው ነበር። የፊፋ የቴክኒክ አማካሪ ዶሚኒክ ኒዮንዚማ በተገኙበት የተደረገውን ገለፃRead More →

የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌድሬሽን በዘንድሮው ዓመት በርካታ ሥራዎችን ለመስራት ማሰቡን ዛሬ በተከናወነ ሥነስርዓት ላይ ገልጿል። ከተመሠረተ ጥቂት ዓመታትን ያስቆጠረው የሲዳማ ክልል እግርኳስ ፌድሬሽን ከምስረታው ጀምሮ ፌድሬሽኑን ከማጠናከር ጀምሮ ከታዳጊ እስከ አዋቂዎች ድረስ በሁለቱም ፆታ የተለያዩ የውስጥ ውድድሮችን ጨምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን የሚዘጋጁ ውድድሮችን እያስተናገደ ዘልቋል። ዘንድሮምRead More →

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቻን ለሚያደርገው ተሳትፎ ፌዴሬሽኑ ከመንግሥት ምን ያህል የፋይናንስ ድጋፍ እንደጠየቀ ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው ጥር በአልጄሪያ አስተናጋጅነት የሚከናወነው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ላይ እንደሚሳተፍ ይጠበቃል። ከውድድሩ ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስተዳደራዊ ዝግጅት እያደረገ ስለመሆኑ ከደቂቃዎች በፊት በድረ ገፁ አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ እንዳስነበበው ብሔራዊ ቡድኑ በውድድሩRead More →

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በ11ኛው የጨዋታ ሳምንት በታዩ የዲስፕሊን ግድፈቶች ላይ በመመስረት የቅጣት ውሳኔዎች ሲያስተላልፍ ድሬዳዋ ከተማ የሳምንቱ ከፍተኛው ቅጣት ተጥሎበታል። 11ኛው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ ሳምንት ሰባት ፍልሚያዎችን አስተናግዶ ትናንት ተፈፅሟል። ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ሥነስርዓት ኮሚቴ ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርቶች ከመረመረRead More →