የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከማላዊ ጋር የሚያደርገው የሜዳው ጨዋታን የሚያደርግበት ሀገር ታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምስተኛውን የምድብ ጨዋታ ሰኔ 13 (June 20) ለማከናወን ሞዛምቢክን ምርጫው ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለካፍ አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ ይፋ እንዳደረገው በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በሚገኙ ስታዲየሞች ላይ ለማከናወን ጥረት ቢያደርግም ሩዋንዳ ከዚህ በፊት ተፈቅዶላትRead More →

ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ሆነዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ለመቅጠር የስራ ማስታወቂያ ማውጣቱ የሚታወስ ሲሆን መስፈርቱን ያሟሉ አምስት ተወዳዳሪዎችም ባለፈው ሳምንት በጁፒተር ሆቴል ለውድድር የቀረበውን የአንድ ዓመት የእግር ኳስ ልማት እቅድ አዘጋጅተው ገለፃ አድርገው ነበር። የፊፋ የቴክኒክ አማካሪ ዶሚኒክ ኒዮንዚማ በተገኙበት የተደረገውን ገለፃRead More →

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቻን ለሚያደርገው ተሳትፎ ፌዴሬሽኑ ከመንግሥት ምን ያህል የፋይናንስ ድጋፍ እንደጠየቀ ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው ጥር በአልጄሪያ አስተናጋጅነት የሚከናወነው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ላይ እንደሚሳተፍ ይጠበቃል። ከውድድሩ ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስተዳደራዊ ዝግጅት እያደረገ ስለመሆኑ ከደቂቃዎች በፊት በድረ ገፁ አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ እንዳስነበበው ብሔራዊ ቡድኑ በውድድሩRead More →

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ዛሬ ከከፍተኛ ሊግ ክለቦች ጋር ባደረገው ውይይት በውድድሩ መጀመሪያ ቀን ፣ በተሳታፊዎች ብዛት እንዲሁም ሊጉ ስለሚያገኘው የቀጥታ ስርጭት ሽፋን አዳዲስ መረጃዎች ይፋ አድርጓል። የ2015 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር በተጠናቀቀው ዓመት ተሳታፊ ያልሆኑ የአማራ ክልል ክለቦችን ጨምሮ በድምሩ 42 ክለቦች በሦስት ምድብ ተከፍለው ይወዳደራሉ፡፡ አስቀድሞ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽንRead More →

ዱላ ሙላቱ ጅማ አባ ጅፋር ‘ደመወዜን አልከፈለኝም’ በማለት ያቀረበው አቤቱታ በፌደሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ አግኝቷል። ዱላ ሙላቱ ከመስከረም 1 2013 አንስቶ እስከ ሰኔ 30 2015 የሚያቆየው የሁለት ዓመት ውል ከጅማ አባ ጅፋር ጋር የነበረው ቢሆንም ከሚያዝያ 1 2014 ጀምሮ ግን ክለቡ ደመወዙን እየከፈለው እንደማይገኝ በመጥቀስ ለፌደሬሽኑ አቤቱታውን ማስገባቱ ይታወሳል። ጉዳዩንRead More →

👉”በስምምነቱ ላይ በግዴታነት የተቀመጡ ጉዳዮች አሉ…….” – አቶ ባህሩ ጥላሁን 👉”እኛ የምንከፍለው ከሌሎች ሀገራት አንፃር ዝቅተኛ ነው ነገርግን ሀገራችን ካለችበት ሁኔታ አንፃር ከፍተኛ ነው።” – አቶ ባህሩ ጥላሁን 👉”ውጣ ውረዶች ቢኖሩም ጥሩ ነገር ሰርተናል ብዬ አስባለሁ”- አሰልጣኝ ውበቱ አባተ 👉”ከሀገር ውጭ ያለውን ነገር ትተን በሀገር ውስጥ አንድ ክለብ ብይዝ የማገኘውRead More →

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ኮንትራት መራዘሙ ተረጋግጧል። መስከረም 18 2013 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ተደርገው ተሹመው የነበሩት አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ቡድኑን ይዘው ዘልቀዋል። በቆይታቸው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎን ያሳኩት አሰልጣኝ አሁን ደግሞ ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣዩ የቻን ውድድር ላይ የሚያሳትፈውን ውጤት እንዲያስመዘግብ አድርገዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ውላቸውRead More →

👉 “ምርጫው በዚህ መልኩ መጠናቀቁ ትልቅ ድል እና እፎይታ ነው የፈጠረው ፤ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ እና ምንም አይነት እንከን የሌለው ነበር ” አቶ በለጠ 👉 “የምርጫ ቦታ መቀየሩን ስናውቅ የወቅቱን ፕሬዝዳንት እና የጽሕፈት ቤት ሀላፊውን አስጠርተን ምክንያታቸውን እንዲያስረዱን አድርገናል” አቶ ኃይሉ 👉 “ይህን አስፈፃሚነት ለቀን እንድንወጣ እና ራሳችንን እንድናገል ከውጭRead More →

👉”ደጋፊዎቼን እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለው” 👉”ጉባኤው ትንሽ ለሰራነው ነገር በዚህ ደረጃ እውቅና መስጠቱ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል” 👉”የጉባኤው አባላት ራሳቸውን ነፃ ያወጡበት ነገር ነው…የእኔ መመረጥ ብቻ ሳይሆን የራሳቸውንም ነፃነት ያወጁበት ነው” 👉”ጉባኤያችን ኢ ሲ ኤ አዳራሽ ተጀምሮ ኢ ሲ ኤ አዳራሽ አልቋል” ስለ ተሰማቸው ስሜት እና ስለ ተዘጋጀው ሰነድ…?Read More →

በቀጣይ ሁለት ቀናት የሚደረገውን የምርጫ ጠቅላላ ጉባዔ የተመለከተ መግለጫ ተሰጥቷል። መጪውን አራት ዓመታት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት እና ሥራ አስፈፃሚ የሚሆኑ ግለሰቦችን ለመለየት የሚደረገው የምርጫ ጠቅላላ ጉባዔ ነገ እና ከነገ በስትያ በኢሲኤ አዳራሽ ይከናወናል። የዚህን የምርጫ ሂደት በተመለከተ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፅህፈት ቤት የከወናቸውን ተግባራት አስመልክቶም ዋና ፀሀፊው አቶ ባህሩRead More →