ኮሮና

ዛሬ እየተደረገ ባለው የሼር ካምፓኒው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ፕሪምየር ሊጉ እንደሚመለስ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ዛሬ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስብሰባ እያደረገ ይገኛል፡፡ በዛሬው የውይይት መድረክ ላይ የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር፣ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ እና የአክሲዮን ማኅበሩ የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደዝርዝር

በሃገራችን የተለያዩ የሊግ እርከኖች እየተጫወቱ የሚገኙ እና ለሙከራ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ጋናዊያን እግርኳስ ተጫዋቾች ትላንት በአዲስ አበባ ወደሚገኘው ጋና ኢምባሲ በመሄድ ለመንግስታቸውን ምሬት የተቀላቀለበት ጥያቄ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሼር ኩባንያ እና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን በጋራ በመመካከር በዓለማችን ብሎም በሃገራችን እየተስፋፋ ባለው ኮቪድ 19 ምክንያት የእግርኳስ ውድድሮችን በኢትዮጵያ መሰረዛቸው ይታወቃል።ዝርዝር

ሱፐር ስፖርት ከኮሮና ወረርሺኝ ጋር በተያያዘ የአፍሪካ የሊግ ውድድሮችን አስመልክቶ ይዞት በወጣው መረጃ ኢትዮጵያ ብቸኛዋ ሃገር እንደሆነች ተመላክቷል። በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ዓለም ላይ የሚደረጉ የእግርኳስ የሊግ ውድድሮች ዘለግ ላለ ጊዜ ተቋርጠው እንደነበር ይታወቃል። ምንም እንኳን ወረርሽኙ ከዓለም ሙሉ ለሙሉ ባይጠፋም የአውሮፓ ሃገራት ሊጎቻቸውን በጥብቅ የጤና ህጎች አጥረው ውድድሮችን ከቆሙበትዝርዝር

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቀውስ እያስከተለ የሚገኘውን የኮሮና ቫይረስ ሀገራችንም እያስከተለ የሚገኘውን ተፅዕኖ ለመቀነስ በስፖርቱ ዘርፉ ያሉ ግለሰቦች እና ተቋማት ድጋፋቸውን እያደረጉ ሲሆን አሁን ደግሞ የኮምቦልቻ ዳኞች እና ታዛቢዎች ሙያ ማህበርም በቀደሙት ጊዜያት በወሎ እና አካባቢዋ በዳኝነቱ ሆነ በስፖርቱ ጉልህ አስተዋፅኦ ላደረጉት ባለውለተኞች እና ቤተሰቦቻቸው ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉን አስመልክቶ የማኅበሩዝርዝር

ሰበታ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከቡድኑ አጠቃላይ አባላት በተሰበሰበ 453 ሺህ ብር እህል በመግዛት ለከተማ አስተዳደሩ አስረከበ፡፡ በኮሮና ወረርሺኝ ምክንያት በርካቶች በሀገራችን በስራ እጦት ለችግር እየተዳረጉ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህ ረገድ ችግር ያጋጠማቸውን ግለሰቦች፣ አቅመ ደካሞች እና ድርጅቶችን በእግርኳሱ ውስጥ ያሉ በአጠቃላይ የራሳቸውን ድርሻ እስከ አሁኗ ጊዜ ድረስ እየተወጡ ሲገኝ አሁንዝርዝር

የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ደቡብ ፖሊስ ለሁለተኛ ጊዜ የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲሁም የደም ልገሳን አከናውኗዋል፡፡ ከወራት በፊት የቁሳቁስ ድጋፍን ከሀዋሳ ከተማ ክለብ ጋር በአንድ በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ለግሶ የነበረው የከፍተኛ ሊግ ተወዳዳሪው ደቡብ ፖሊስ አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ የክለቡ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች፣ የክለቡ ሰራተኞች በጠቅላላው ከደመወዛቸው ላይ 10% በመቁረጥ የተለያዩ የእህል ምግቦችን እናዝርዝር

(መረጃው የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ነው።) የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ሀላፊዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል ውይይት አደረገ። በዚህ ውይይት ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶች እና ወጣቶች ማህበራዊ ዘርፍ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወይዘሮ ሂሩት አፅብሀ ፣ የአዲስ አበባዝርዝር

ከዚህ ቀደም ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ እንዲውል የገንዘብ ድጋፍን አበርክቶ የነበረው የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ቡታጅራ ከተማ አሁን ደግሞ የቁሳቁስ ድጋፍን ዛሬ አበርክቷል። ከአንድ ወር በፊት ከተጫዋቾቹ፣ ከአሰልጣኝ ቡድን አባላት እና ከክለቡ የቢሮ ሰራተኞች ከሀምሳ አንድ ሺህ ብር በላይ ለግሶ የነበረው የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ቡታጅራ ከተማ አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ በዛሬው ዕለትዝርዝር

በቅርቡ የተቋቋመው የትግራይ አሰልጣኞች ማሕበር በለይቶ ማቆያ ውስጥ ላሉ የጎዳና ተዳዳሪዎች ድጋፍ አደረገ። በቅርቡ የተቋቋመው የትግራይ አሰልጣኞች ማኅበር በመቐለ ለይቶ ማቆያ ለተጠለሉት የጎዳና ተዳዳሪዎች የምግብ እና ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶች ድጋፍ አደረገ። ከስድስት ወራት በፊት የተመሰረተው ይህ ማኅበር ቀደም ብሎ ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጉ ሲታወስ አሁን ደግሞ በከተማው የሚገኙትን ባለ ሀብቶች አስተባብሮዝርዝር

ክለቦች ለሴት ተጫዋቾች መክፈል የነበረባቸውን የወር ደመወዝ በአግባቡ እየፈፀሙ ባለመሆኑ በተጫዋቾቹ ዘንድ ቅሬታን አስነስቷል፡፡ በ2012 በኢትዮጵያ በሁለቱም ፆታ ሲደረጉ የነበሩ የእግር ኳስ የሊግ ውድድሮች ከወራት በፊት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ከቆሙ በኃላ በቅርቡ ደግሞ በይፋ ሙሉ ለሙሉ መሰረዛቸው ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውድድሮቹ ቢሰረዙም ክለቦች ከተጫዋቾች ጋር በገቡት ውል መሠረትዝርዝር