ኢእፌ (Page 18)

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ትግራይ ስታድየም ላይ በደደቢት እና ኢትዮጵያ ቡና መካከል የተካሄደው ጨዋታ “ያለ ክለባችን ፍቃድና እውቅና ውጭ የቀጥታ የሬዲዮ ስርጭት ተካሂዷል።” ሲል ለፌዴሬሽኑ አቤቱታውን አቀረበ። ” የደደቢት እግርኳስ ክለብ ጥቅምት 25 ቀን 2011 ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ባከናወነው ጨዋታ ላይ የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሀን (ኤፍኤም 96, 3) የሬዲዮዝርዝር

በ2010 ፌዴሬሽኑ ያወዳደራቸው ሰባት ሊጎች ኮከቦችን ሽልማት ኅዳር መጀመርያ ላይ ይደረጋል ቢባልም ስለመካሄዱ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም። ለሁለተኛ ጊዜ በሚዘጋጀው በዚህ የኮከቦች ሽልማት ከአምናው ልምድ በመውሰድ ዘንድሮ በተሻለ ሁኔታ ይደረጋል ቢባልም እስካሁን ሳይደረግ መቆየቱ እንዳለ ሆኖ በአንዳንድ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ አባላት ዘንድ ቢቀር የሚል ሀሳብ ተነስቶ የነበረ ቢሆንም “ከአምናው የተሻለ መርሀግብርዝርዝር

የኢትዮጵያ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታን በቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍን አስመልክቶ የፌዴሬሽኑ መተዳደርያ ደንብን መሠረት ባደረገ መልኩ እንዲሆን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለክለቦች በላከው ደብዳቤ አሳሰበ። በአዲስ መልክ መካሄድ ከጀመረ 21ኛ ዓመቱን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2011 የውድድር ዘመን ሊጀመር ዋዜማ ላይ በምንገኝበት ወቅት ሚዲያዎች ጨዋታዎችን ከፌዴሬሽኑ ፈቃድ ውጭ ማስተላለፍ እንደማይቻል በደብዳቤ ትዕዛዝ አስተላልፏል።ዝርዝር

ኢትዮጵያ ቡና በትኬት ሽያጭ ገቢ ላቀረበው ጥያቄ ፌዴሬሽኑ ምላሽ  ለመስጠት ቀጠሮ ይዟል። ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የ2010 የአዲስ አበባ ስታድየም ገቢ ድርሻ እንዲሰጠው እና የዘንድሮው የውድድር ዘመን የስታድየም ትኬት ሽያጭ በክለቡ አማካኝነት እንዲከናወን ፤ ይህ በአስቸኳይ ካልተፈጸመም ውድድር እንደማያደርግ የሚገልጽ ደብዳቤ ለፌዴሬሽኑ ማስገባቱን በዛሬው ዕለት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ደብዳቤውን የተመለከተውዝርዝር

በ2010 የውድድር ዘመን ወልዋሎን ሲያገለግሉ የነበሩት ወግደረስ ታዬ ፣ መኩርያ ደሱ ፣ ከድር ሳህሊ እና አታክልቲ ፀጋዬ ክለቡ በቅድመ ውድድር ዝግጅት ነሐሴ 19 ወደ ካምፕ እንዲገቡ የሰጠሁትን ትዕዛዝ ሌሎች የቡድኑ ተጫዋቾች ጥሪውን አክብረው ሲገኙ እነርሱ ግን በተደጋጋሚ ጥሪ ቢደረግላቸውም ሊገቡ አልቻሉም ። ሆኖም ከድር ሳሊህ እና አታክልቲ ፀጋዬ ጋር ጉዳዩዝርዝር

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ አዲሱ የውድድር ዓመት እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት እና ያለፈው ዓመት አፈፃፀም  ሪፖርት የሚቀርብበት ቀን ላይ መሸጋሸግ ተደርጎበታል። ኅዳር 15 እንደሚጀመር የሚጠበቀው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ጥቅምት 15 እንደሚደረግ መርሐ ግብር ተይዞለት የነበረ ቢሆንም በሴቶች ፕሪምየር ሊግ ስብሰባ ምክንያት ወደ ፊት ተገፍቶ ጥቅምት 20 በኢትዮጵያ ሆቴልዝርዝር

በተሻሻሉ ህጎች ላይ ለዳኞች ፤ ለኮሚሽነሮች እንዲሁም ለክለብ አመራሮች እና ለተጫዋቾች ስልጠና ሊሰጥ ነው። የ2010 የውድድር ዓመት በርካታ የውዝግብ መነሻ የሆኑ ነገሮችን አሳይቶን ያለፈ ነበር። በተለይም ከዳኝነት ጋር ተያይዘው የተፈጠሩ ጉዳዮች የስፖርቱን ወቅታዊ ህግጋት ካለመረዳትም ጭምር እንደሚከሰቱ የብዙዎች ዕምነት ነው። ይህን ከግምት በማስገባትም ይመስላል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ ዳኞችዝርዝር

በፌዴሬሽኑ መመዘኛ መሰረት አቶ መኮንን ኩሩ ተቋሙ የቴክኒክ ዳሬክተር ለመሆን የሚያበቃቸውን ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ በኢትዮጵያ እግርኳሳዊ ልማት ላይ በርካታ ስራዎች ይሰራል ተብሎ የሚታመንበት የቴክኒክ ዳይሬክተር ቦታ ያለፈውን አንድ ዓመት ያለ ኃላፊነት ክፍት ሆኖ በመቅረቱ በርካታ መሰራት የሚገባቸው ስራዎች ተዘንግተው ቆይተዋል። አዲሱ የፌዴሬሽን በቦታው ሰው ለመቅጠር ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መስፈርት መሰረትም የተወዳደሩዝርዝር