ኢእፌ (Page 2)

በትግራይ ክልል ክለቦች አለመሳተፍ ምክንያት በ13 ክለቦች የተካሄደው የዘንድሮ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በቀጣዩ ዓመት በ16 ክለቦች መካከል እንደሚካሄድ መገለፁ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ የሊጉ ተሳታፊዎች በሚወሰኑት ሒደት ዙርያ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን መግለጫ አውጥቷል። ከፌዴሬሽኑ ድረገፅ ያገኘነው ማብራርያ ይህንን ይመስላል:-ዝርዝር

በ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ላይ ተካፋይ ያልነበሩት መቐለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ስሑል ሽረ በቀጣይ ዓመት ወደ ውድድር እንዲመለሱ በማሰብ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ከክለቦቹ ጋር ግንኙነት መጀመሩ ተገልጿል፡፡ በ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ላይ በትግራይ ክልል የሚገኙት ሦስቱ ክለቦች በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት በሊጉ ሳይሳተፉ በመቅረታቸውዝርዝር

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከ2010 በኋላ ያልተደረገውን ውድድር በሐምሌ ወር ዳግም እንደሚጀምር ገልጿል። በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የ16 ሳምንታት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድርን ግምገማ በኢንተር ኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል እያከናወነ ይገኛል። የሥነ-ስርዓቱ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ በሀምሌ ወር ፌዴሬሽናቸውዝርዝር

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማ ላይ በተደረገ ጨዋታ የአፈፃፀም ግድፈት አሳይተዋል የተባሉት ረዳት ዳኛ ለሁለት ወራት ታግደዋል። በዘጠነኛ ሳምንት የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሰበታ ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና ባደረጉት ጨዋታ 87ኛው ደቂቃ ላይ ዱላ ሙላቱ በቀኝ የሜዳው ክፍል ከሰበታው ተከላካይ መሳይ ጳውሎስ ቀድሞ ኳስ ለማግኘት በሚሮጥበት ወቅት መውደቁን ተከትሎ ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛውዝርዝር

በተለያዩ ችግሮች ውስጥ የሚገኘው ሀድያ ሆሳዕና የተወሰነበትን ውሳኔ ተግባራዊ ባለማድረጉ ምክንያት ፌዴሬሽኑ የዕግድ ውሳኔ አሳልፎበታል። ከባለፉት ዓመታት ደካማ የውድድር አፈፃፀም ዘንድሮ በሁሉም መልኩ ተሽሎ የመጣው ሀድያ ሆሳዕና ምንም እንኳን በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ለዋንጫ የሚገመት ቡድን ቢሆንም ከሜዳ ውጭ ያሉበት የተለያዩ ችግሮች በጉዞው ላይ ፈተና እየሆኑበት መምጣታቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ ያሳለፍነውዝርዝር

በካሜሮን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የቻን ውድድር እና ተዛማጅ ጉዳዮች የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ ለሳምንታት ቆይታ ወደ ካሜሩን አቅንተዋል። በሀገር ውስጥ ሊጎች ተጫዋቾች ብቻ የሚካሄደው የቻን ውድድር በኮሮና ሻይረስ ምክንያት በ2020 መካሄድ ሲገባው ተገፍቶ ከቀናት በኋላ በካሜሩን አስተናጋጅነት እንደሚካሄድ ይታወቃል። በዚህ ውድድር በክብር እንግድነት ተጋብዘው ፕሬዝደንት ኢሳያስ ጅራ በትናትናው ዕለት ወደዝርዝር

ከቀናት በፊት በጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች ተገቢነት ላይ ክስ ያቀረቡት ወልቂጤ ከተማዎች ክሳቸው ውድቅ መደረጉን ተከትሎ ይግባኝ ብለዋል። ወልቂጤ ከተማዎች በሁለተኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማ አባጅፋርን ገጥመው ያለጎል ነጥብ ተጋርተው እንደነበር ይታወሳል። ከጨዋታው በኋላ በተጋጣሚያቸው ተጫዋቾች ላይ የተገቢነት ክስ ያቀረቡት ወልቂጤዎች ለክሳቸው “ተገቢ ምላሽ አላገኘንም” በሚል በድጋሚ ይግባኝ ብለዋል።ዝርዝር

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙርያ የአቋም መግለጫ ሲያወጣ አላግባብ የስም ማጥፋት ዘመቻ በተቋሙ ላይ ስለመደረጉ ገልጿል። ፌዴሬሽኑ ያወጣው የአቋም መግለጫ ይህንን ይመስላል:- የአቋም መግለጫ ታህሳስ 19/2013ዓ.ም አዲስ አበባ፤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ህዳር 27/2013ዓ.ም 12ኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በተሳካ ሁኔታ ማካሄዱ ይታወሳል፤ ጠቅላላ ጉባዔው ከመካሄዱ በፊት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅትዝርዝር

ክለቦች ትርፋማ የባለቤትነት ድርጅታዊ መዋቅር እንዲኖራቸው ለማስቻል በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የተዘጋጀው የውይይትና አቅጣጫ የማስያዝ መርሐግብር በጁፒተር ሆቴል ተካሄደ። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባዘጋጀው በዚህ መድረክ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደን አቶ ኢሳይያስ ጅራ፣ ዋና ፀሐፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን እንዲሁም የሊግ ኩባንያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ ተገኝተዋል። በጉባዔው ላይም አስራ ሦስቱ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግዝርዝር

የዓለም አቀፋ እግርኳስ ማኅበር (ፊፋ) በ2021 የፊፋ ኢንተርናሽናል ዳኞች በመሆን የሚያገለግሉ ኢትዮጵያዊ ዋና እና ረዳት ዳኞችን ስም ዝርዝር ማሳወቁን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል። ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2021 በኢንተርናሽናል ዳኝነት የሚያገለግሉ 7 የወንድ እና 4 የሴት ዋና ዳኞች እንዲሁም 6 የወንድ እና 4 የሴት ረዳት ዳኞች መስፈርቱን በሟማላት ተቀባይነትዝርዝር