ዳኞች

የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ እየተካፈለ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካ ጋር ላለበት ጨዋታ የሊቢያ ዜግነት ያላቸው ዳኞች ተመድበዋል፡፡ በኳታር አስተናጋጅነት ለሚደረገው የ2022 የዓለም ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከምድቡ ከተደለደሉት ጋና እና ዚምባብዌ ጋር ከሜዳው ውጪ እና በሜዳው ያከናወነ ሲሆን በሦስተኛው የማጣርያ መርሀግብር መስከረምዝርዝር

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ልማት እና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በ2022 የኢንተርናሽናል ዳኝነት ባጅ የሚወስዱ ዳኞችን ዝርዝር ለፊፋ ልኳል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ልማት እና አስተዳደር ኮሚቴ ከቀናቶች በፊት በ2022 ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን  ሊመሩ ለሚችሉ ዳኞችን ለፊፋ ለማሳወቅ ለነባር ዳኞች የአካል ብቃት ፈተና እንዲሁም ደግሞ ከነባሮቹ በሚወድቁት ምትክ ለአዳዲስ ዳኞች የአካል ብቃትዝርዝር

ኮስታሪካ ለምታስተናግደው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል አንዱ የሆነውን መርሐ-ግብር ለመዳኘት አራት እንስት የሀገራችን ዳኞች ወደ ናይሮቢ ሊያመሩ ነው። በቀጣይ ዓመት በኮስታሪካ አስተናጋጅነት በሚካሄደው ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የአህጉራችን ብሔራዊ ቡድኖች የሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታቸውን ካለንበት ሳምንት አንስቶ ማድረግ ይጀምራሉ። ካሉት መርሐ-ግብሮች መካከል ደግሞዝርዝር

ነገ በባህር ዳር ዓለምአቀፍ ስታድየም የሚደረገውን ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ባህር ዳር ደርሰዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2022 በኳታር አስተናጋጅነት ለሚደረገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታውን በማድረግ ላይ ይገኛል። የማጣሪያው አካል የሆነውን የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታም ነገ ባህርዳር ላይ የዚምባብዌ አቻውን በመግጠም እንደሚከውን ይጠበቃል። ይህንን ተጠባቂ ጨዋታም ለመዳኘት የተመደቡት ዳኞች ታውቀዋል። በመሀል እናዝርዝር

አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምኅረትን በዋና አሰልጣኝ መንበር የሾመው ሀድያ ሆሳዕና የ2014 የቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚጀምርበት ቀን ተገልጿል፡፡ ለሁለት ዓመታት በሚቆይ የውል ዕድሜ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምኅረትን ከቀጠረ በኋላ የተለያዩ ተጫዋቾችን ከፕሪምየር ሊግ ክለቦች ሲያስፈርም የቆየው ክለቡ በቀጣዮቹ ቀናትም ተጨማሪ ተጫዋቾችን እንደሚቀላቅል እና ከ20 ዓመት ቡድኑም ወጣቶች እንደሚያሳድግ የሚጠበቅ ሲሆን ለ2014 የቤትኪንግ ፕሪምየርዝርዝር

በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጋና ኢትዮጵያን የምታስተናግድበት ጨዋታ በሞሮኮ ዳኞች ይመራል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ2022 የካታር ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከዚምባብዌ ፣ ጋና እና ደቡብ አፍሪካ ጋር መደልደሏ ይታወሳል፡፡ በያዝነው ወር መጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታዎቹ የሚጀመሩ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም ከጋና ጋር ለምታደርገው መርሀግብር በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ መሪነት በአዳማ ከተማ ዝግጅት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡የመጀመሪያውንዝርዝር

👉 “…ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በፓርላማ ሲናገሩ…” 👉 “…እኔ ከለመደብኝ ነገር አኳያ ተጫዋቾች መሐል ዘሎ የመግባት ነገር አለኝ” 👉”በአንፃራዊነት ካጫወትኳቸው ጨዋታዎች የመጀመሪያው ጨዋታ ላይ … ኪሎ ሜትር ሸፍኜ ነበር”  👉 “ፈጣሪ ከፈቀደ በቀጣዩ የኳታር ዓለም ዋንጫ ላይ በመሐል ዳኝነት ማገልገል ህልሜ ነው” የዓለም ዋንጫ፣ የአፍሪካ ዋንጫ እንዲሁም የአህጉሪቱዝርዝር

ነገ ከሰዓት በሜክሲኮ እና ጃፓን መካከል የሚደረገውን የቶኪዮ ኦሊምፒክ የደረጃ ጨዋታ ኢትዮጵያዊው የመሐል ዳኛ ይመራዋል። በቶኪዮ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የ2020 የኦሊምፒክ ውድድር በደማቅ ሁኔታ የብዙዎችን ቀልብ በመያዝ ቀጥሏል። በኦሊምፒኩ ከሚደረጉት የተለያዩ የስፖርት አይነቶች መካከል ደግሞ እግርኳስ ይገኝበታል። ቀደም ብሎ ተጀምሮ የነበረው ይህ የስፖርት አይነትም ቅዳሜ ፍፃሜውን እንዲያገኝ መርሐ-ግብር ተይዞለታል። ቅዳሜዝርዝር

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ በቶኪዮ ኦሊምፒክ የአውስትራሊያ እና የስፔን ጨዋታን በዋና ዳኝነት ዕሁድ አመሻሽ ይመራል፡፡ በኮቪድ 19 ምክንያት በአንድ ዓመት ተራዝሞ በይፋ በትናንትናው ዕለት በመክፈቻ መርሐግብር የተጀመረው የ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ የእግር ውድድሮች በሁለቱም ፆታ ቀደም ብሎ ከቀናት በፊት የተጀመረ ሲሆን የምድብ ማጣሪያዎችም ቀጥለዋል፡፡ ከቀናት በፊት ሜክሲኮ ከ ፈረንሳይ ያደረጉትዝርዝር

ቅዳሜ በሚጀምረው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ አስራ ሰባት ዳኞች ከተለያዩ ሀገራት ጥሪ ሲቀርብላቸው ሁለቱ ከኢትዮጵያ ሆነዋል፡፡ የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ ሐምሌ 10 በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በሚደረጉ ሁለት መርሀግብሮች በይፋ ይጀመራል፡፡ በሶስት ምድቦች ተከፍሎ በዘጠኝ ሀገራት መካከል የሚደረገውን ይህን ጨዋታ ከተለያዩ ሀገራት በተመረጡ ዘጠኝ ዋና እና ስምንትዝርዝር