Soccer Ethiopia

የሴቶች እግርኳስ

​ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | አዳማ ከተማ አዲስ. ተጫዋች ሲያስፈርም የአማካይዋን ውል አራዘመ

አዳማ ከተማ ሁለገቧን ተጫዋች ሄለን ሰይፉን ሲያስፈርም የአማካይዋ ፋሲካ መስፍንን ውልም አድሷል፡፡ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተወዳዳሪው አዳማ ከተማ ከወራት በፊት የአሰልጣኝ ሳሙኤል አበራን ውል ካራዘመ በኃላ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ የቀላቀለ ሲሆን አሁን ደግሞ አንጋፋዋን የአማካይ እና የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቿን ሄለን ሰይፉን አስፈርሟል፡፡ በአዲስ አበባ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና መከላከያ ስትጫወት የነበረችው […]

​ሎዛ አበራ የቢቢሲ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካታለች

ኢትዮጵያዊቷ የፊት መስመር ተሰላፊ ሎዛ አበራ በተፅዕኖ ፈጣሪነቷ ዓለምአቀፍ ትኩረት አግኝታለች። የእንግሊዙ የሚዲያ ተቋም ቢቢሲ እንደአውሮፓዊያኑ የዘመን አቆጣጠር ከ 2013 ጀምሮ ዓለም ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሚላቸውን 100 እንስቶች በየዓመቱ ይፋ ያደርጋል። እንስቶቹ በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ ተሰማርተው በማህበረሰባቸው ውስጥ ቢፈጥሩት ከፍ ያለ ተፅዕኖ መነሻነት ነው በተቋሙ ዝርዝር ውስጥ የሚካተቱት። በዚህ መሰረት ቢቢሲ የ2020 ተፅዕኖ ፈጣሪ […]

ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ንግድ ባንክ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርሟል

ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች አንድ ተጫዋች ሲያስፈርሙ ለ2013 ውድድር ዝግጅታቸውን የሚጀምሩበትም ቀን ታውቋል። የሦስት ጊዜ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሳምንታት በፊት የ10 ነባር ተጫዋቾችን ውል ማደሱ ይታወሳል። ክለቡ የነባር ተጫዋቾችን ውል ከማደሱ በተጨማሪ ሎዛ አበራ፣ አረጋሽ ካልሳ፣ ሰናይት ቦጋለ እና አያንቱ ቶሎሳን ወደ ስብስቡ በመቀላቀል ታህሳስ 10 ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀውን ውድድር በመጠባበቅ […]

ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | አዲስ አበባ ከተማ የአሰልጣኞቹን ውል ሲያድስ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

አዲስ አበባ ከተማ የዋና እና ረዳት አሰልጣኙን ውል ሲያድስ አስራ ዘጠኝ አዳዲስ እና አምስት ነባር ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተወዳዳሪ የሆነው አዲስ አበባ ከተማ ካለፈው አመት በተሻለ ተፎካካሪ ለመሆን በማሰብ ጠንካራ ሥራዎችን መሥራት ጀምሯል፡፡ የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ነፃነት ታከለ በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት ከዓምናው የተሻለ እና ጠንካራ ቡድን ለመገንባት በማሰብ […]

ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | አቃቂ ቃሊቲ ተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቾች አስፈረመ

አቃቂ ቃሊቲ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ ሁለት ታዳጊዎቸችን አሳድጓል፡፡ አሰልጣኝ ብዙዓየው ዋዳን ከቀጠሩ በኃላ አዳዲስ ተጫዋቾችን ከቀናት በፊት አስፈርመው ከነባሮቹ ጋር አዋህደው ወደ ቅድመ ውድድር ዝግጅት የገቡት የአቃቂ ቃሊቲዎች ተጨማሪ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡ ሔለን ሙሉጌታ (ግብ ጠባቂ ከፋሲል ከነማ)፣ ያብስራ ይታይህ (አጥቂ ከፋሲል ከነማ)፣ የትምወርቅ አሸናፊ (አጥቂ ከአርባምንጭ) አዳዲስ ፈራሚዎቹ ሲሆኑ ሩት ሚልዮን (ተከላካይ) […]

ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ጌዲኦ ዲላ የአሰልጣኙን ውል ሲያራዝም በርካታ ተጫዋቾችንም አስፈርሟል

ጌዲኦ ዲላ የአሰልጣኝ እንዳልካቸው ጫካን ውል ሲያራዝም ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችን ጨምሮ አስራ አራት ነባሮችንም ለተጨማሪ አመት አስፈርሟል፡፡ የክለቡ አዲስ ፈራሚዎች:- መስከረም መንግሥቱ (ግብ ጠባቂ ከአዳማ ከተማ)፣ ገሊላ አበራ (ግራ ተከላካይ ሀዋሳ ከተማ)፣ ደመቀች ዳልጋ (ተከላካይ ከንግድ ባንክ)፣ በላይነሽ ልንገርህ (ተከላካይ ከቂርቆስ)፣ ይታገሱ ተገኝወርቅ (አጥቂ ሀዋሳ ከተማ)፣ ወርቅነሽ መሰለ (አማካይ ሀዋሳ ከተማ)፣ ቱሪስት ለማ (አጥቂ ከአርባምንጭ […]

ካፍ ለሴቶች እግርኳስ ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ጀምሯል

በካፍ እየተሰጠ የሚገኘው እና ኢትዮጵያዊያን የሴቶች እግርኳስ ባለሙያዎች እየተሳተፉበት ያለው ስልጠና ትናንት ተጀመረ፡፡ የአፍሪካ እግርኳስ ማኅበር (ካፍ) በስሩ ላሉ አባል ሀገራት ውስጥ ለሚገኙ የሴት እግር ኳስ አሰልጣኞች ባለሙያዎች እና በፊዚዮቴራፒስነት በሴት እግር ኳስ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ለሦስት ቀን የሚቆይ የኦንላይን ስልጠና ጀምሯል፡፡ትናንት ረፋድ በጀመረው ስልጠና ላይ ከዚህ ቀደም በአካል ባለሙያዎቹ በአንድ ሀገር በሚሰጥ ስልጠናን ሲወስዱ […]

የሴቶች ሊግ ውድድር የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ዛሬ ተከናውኗል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሴቶች አንደኛ እና ሁለተኛ ዲቪዚዮን የውድድር መመሪያ ደንብን በዛሬው ዕለት ለክለቦች ሲያቀርብ የዕጣ ማውጣት መርሐ-ግብርም አከናውኗል። በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስር የሚከወኑት የኢትዮጵያ አንደኛ እና ሁለተኛ ዲቪዚዮን የሊግ ውድድሮችን በተመለከተ ዛሬ ከረፋድ ጀምሮ የደንብ ውይይት እና የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ሲከናወን ውሏል። ይጀመራል ተብሎ ከተነገረበት ጊዜ አንድ ሰዓት አርፍዶ በተጀመረው በዚህ መርሐ-ግብር ላይ የፌዴሬሽኑ […]

ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | አቃቂ ቃሊቲ ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ@

በቅርቡ አዲስ አሰልጣኝ የቀጠረው አቃቂ ቃሊቲ ወደ ዝውውሩን በመቀላቀል ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የሦስት ነባሮችን ውልም አራዝሟል፡፡ በቅርቡ የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያን አውጥቶ በርካታ አሰልጣኞችን ካወዳደረ በኃላ ለረጅም አመታት በሴቶች እግር ኳስ ላይ በመስራት የሚታወቀውን አሰልጣኝ ብዙአየው ዋዳን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረው አቃቂ ቃሊቲ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ላይ ጠንክሮ ለመቅረብ ይረዳው ዘንድ በኢትዮጵያ ንግድ […]

ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | መከላከያ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

የበርካታ ወሳኝ ተጫዋቾችን ዝውውር ቀደም ብሎ የፈፀመው መከላከያ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ በ2013 ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን አዲስ አሰልጣኝ ከሾመ በኋላ ወሳኝ ተጫዋቾችን በማስፈረም ተጠምዶ የነበረው መከላከያ ሁለት ወጣት ጫዋቾችን ወደ ክለቡ ስብስብ ካካተተ በኃላ ዝውውሩን ፈፅሞ ወደ ቅደመ ውድድር ዝግጅት ገብቷል፡፡ ተስፈኛዋ አጥቂ ህዳት ካሡ ክለቡን የተቀላቀለች ተጫዋች ነች። በሁለተኛ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top