Soccer Ethiopia

ሉሲ

ጊዜው እየሄደ ቢሆንም ምላሽ ያላገኘው የብሔራዊ ቡድኑ ጉዳይ

ለ2021 የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታዎች ከተቋረጡበት ይቀጥላል በማለት ካፍ ቢያሳውቅም በኢትዮጵያ በኩል እስካሁን ምላሽ አላገኘም። በ2020 ሊደረግ ታስቦ የነበረው የዓለም ዋንጫው ጥር 2021 ላይ በኮስታሪካ እና ፓናማ አዘጋጅነት እንደሚካሄድ የሚጠበቅ ሲሆን በቅድመ ማጣርያ የቡሩንዲ አቻዋን 7-1 በሆነ ድምር ውጤት አሸንፎ ወደ አንደኛ ዙር ያለፈው ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ […]

የሴቶች ገፅ | የመጀመሪያው የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ አዝናኝ ክስተት…

ከዚህ ቀደም ከእግርኳስ ተጫዋችነት እስከ ህክምና ባለሙያነት የዘለቀውን የዶ/ር እንደገናዓለም አዋሶን አስገራሚ ህይወት አቅርበንላችሁ ነበር። ዛሬ ደግሞ የመጀመሪያው የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሲመሰረት ተጫዋቾቹ የሰሩትን አስቂኝ ድርጊት እንደገናዓለም ታጫውተናለች። ከአዳማ ከተማ 09 ቀበሌ ተነስታ ሃገሯን በብሄራዊ ቡድን ደረጃ መወከል የቻለችው እንደገናዓለም በተለይ በግራ እግሯ በምትሰራቸው ተዓምሮች የብዙዎችን ቀልብ ገዝታ ቆይታለች። ከምንም በላይ ደግሞ ከርቀት በግራ እግሮቿ […]

የሴቶች ገፅ | ወርቃማዋ እንስት ሽታዬ ሲሳይ

በቡድን ስኬት እና በግል ክብሮች ባንፀባረቀው የእግር ኳስ ህይወቷ ከትምህርት ቤት ተነስታ እስከ ብሔራዊ ቡድን የዘለቀችው ሽታዬ ሲሳይን የዛሬው የሴቶች ገፅ አምዳችን በስፋት ተመልክቷታል፡፡ ኳስን የጀመረችው ተወልዳ ባደገችበት አዲስ አበባ አዲሱ ገበያ አካባቢ ከወንድ ጓደኞቿ ጋር በመጫወት ነበር። ስኬታማዋ አጥቂ ሽታዬ ሲሳይ አባቷ ከኳሱ ይልቅ ትምህርቷ ላይ ብቻ እንድታተኩር በተደጋጋሚ ይገስጿት ስለነበር የልጅነት ዕድሜዋን በፕሮጀክት […]

የሴቶች ገፅ | 26 ዋንጫዎችን ያነሳችው ብዙሃን እንዳለ..

ለ13 ዓመታት ለኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ድንቅ ግልጋሎት የሰጠችው እና በ4 የተለያዩ ክለቦች 26 ዋንጫዎችን ያነሳችው ብዙሃን እንዳለ በዛሬው የሴቶች ገፅ አምዳችን ትዳሰሳለች። ጊንጪ በምትባል የኦሮሚያ ከተማ ተወልዳ ነገር ግን ገና አንድ ዓመት ሳይሞላት ወደ አዲስ አበባ የመጣችው ብዙሃን እንደ አብዛኞቹ የሴት ተጨዋቾች ኳስን ከልጅነቷ ጀምሮ እንደልቧ መጫወት አልቻለችም። በተለይ ከአንድ አመቷ ጀምሮ ያደገችበት ቶታል […]

የሴቶች ገፅ | ከእግርኳስ ተጫዋችነት እስከ ህክምና ባለሙያነት…

የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጎል ያስቆጠረችውና እና በአሁኑ ሰዓት የህክምና ባለሙያ በመሆን እያገለገለች ያለችው የዶ/ር እንደገናዓለም አዋሶ አስገራሚ የህይወት ጉዞ። ውልደት እና እድገቷ አዳማ ከተማ ልዩ ስሙ ቀበሌ 09 በሚባል ስፍራ ላይ ነው። ከልጅነቷ ጀምሮ እግርኳስ ለመጫወት ብዙ ፈተናዎችን አልፋ እንደነበረ የምትናገረው እንደገናዓለም በተለይ እንደማንኛውም ታዳጊ ልጅ በሰፈር ውስጥ ኳስ ለመጫወት ስትፈልግ በፆታዋ ምክንያት […]

የሴቶች ገፅ | በወጥነት የዘለቀው የረሂማ ዘርጋ ውጤታማ ጉዞ

በኢትዮጵያ የሴቶች እግርኳስ ውስጥ ጎልተው ከወጡ ተጫዋቾች መካከል የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ አጥቂ ረሂማ ዘርጋ አንዷ ነች። እኛም ስኬታማዋን ግብ አዳኝ በዛሬው የሴቶች አምዳችን ቃኝተናታል፡፡ ትውልድ እና ዕድገቷ በመዲናችን አዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አካባቢ ነው፡፡ ኳስንም የጀመረችው እዛው ሽሮ ሜዳ ቀበሌ 03 ከሠፈር ጓደኞቿ ጋር ነበር። ከቆይታ በኋላም በወቅቱ ተክለኃይማኖት ፔፕሲ የሚሰሩ የሰፈር ጓደኞቿ እጇን ይዘው […]

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኖች ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚውል ድጋፍ አድርገዋል

በዓለም ደረጃ ከፍተኛ ስጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ በሃገራችን እንዳይስፋፋ የሚደረገው ድጋፍ ቀጥሎ ዋሊያዎቹ እና ሉሲዎቹ በጋራ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል። ከሳምንቱ መጀመሪያ ቀናት ጀምሮ በተናጥል ገንዘብ ሲያሰባስቡ የነበሩት ሁለቱ ብሄራዊ ቡድኖች የሰበሰቡትን ገንዘብ በአንድ በማድረግ ዛሬ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) አስረክበዋል። በሁለቱም ቡድኖች የሚገኙ የአሰልጣኝ ቡድን አባላት፣ የተለያዩ ማህበራት፣ ደጋፊዎች፣ የቀድሞ […]

ሉሲዎቹ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከያ የሚረዳ ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምረዋል

የተለያዩ ግለሰቦች እና ተቋማት ይህንን ወረርሽኝ ለመከላከል የሚረዳ ድጋፍ ማድረጋቸውን ሲቀጥሉ የሉሲዎቹ ተጨዋቾች እና አሰልጣኞች የበኩላቸውን ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምረዋል። በብሔራዊ ቡድኑ በዋና አሰልጣኙ ብርሃኑ ግዛው አስተባባሪነት ድጋፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ እና መጠኑ ለጊዜው ያልተገለፀ ገንዘብ እንደሰበሰበ ለማወቅ ተችሏል። ትላንት በጀመረው የብሔራዊ ቡድኑ ንቅናቄም ከ20 እና ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን የአሰልጣኞች ቡድን አባላት እና […]

ፌዴሬሽኑ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝን ውል አራዝሟል

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለተጨማሪ ወራት ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የሚያቆየውን ውል ፌዴሬሽኑ አራዝሞለታል። የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ቡሩንዲን በደርሶ መልስ ውጤት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር እንዲያልፍ ያስቻሉት የቀድሞ የደደቢት እና የሲዳማ ቡና የሴቶች ቡድን አሰልጣኝ ፍሬው ኃ/ገብርኤል ለተጨማሪ ሦስት ወራት ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የሚቆዩበትን አዲስ ኮንትራት ፈርመዋል። ለውሉ መራዘም […]

ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ጀምሯል

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከዚምባብዌ ጋር ለሚያደርገው የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ባልተሟላ ስብስብ ዝግጅቱን ማምሻውን በአዲስ አበባ ስታዲየም ጀምሯል። ከታሰበበት ቀን ዘግይቶ ዝግጅቱን የጀመረው ብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ከተደረገላቸው 23 ተጫዋቾች መካከል 13 ተጫዋቾች በመያዝ ነው ማምሻውን ከወልቂጤ ከተማ እና ከአዳማ ከተማ ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ ቀለል ያለ ልምምዱን በአዲስ አበባ ስታዲየም ያከናወነው። ባለፉት […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top