የሴቶች እግርኳስ (Page 3)

በአንደኛ ዲቪዝዮን የሚሳተፈው አርባምንጭ ከተማ የአራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲያጠናቅቅ የስድስት ነባር ተጫዋቾችን ውልም አራዝሟል፡፡ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን የ2013 የውድድር ዘመን ተወዳዳሪ የነበረውና በዓመቱ መጨረሻ ለመውረድ ተገዶ የነበረው አርባምንጭ ከተማ በቅርቡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወረዱ ክለቦች በድጋሚ በአንደኛ ዲቪዚዮኑ ይቀጥሉ የሚል መመሪያን በማውጣቱ መነሻነት በፕሪምየር ሊጉዝርዝር

በኮስታሪካ አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የ2022 ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ጅቡቲ እና ኤርትራ አዲስ አበባ ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ የ2022 የዓለም ከ20 አመት በታች የሴቶች ዋንጫ በኮስታሪካ አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡ ለዚህም ውድድር ይረዳ ዘንድ በአፍሪካ የሚገኙ ሀገራት የቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ማድረግ የጀመሩ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በቅርቡ በአንደኛዝርዝር

በሀዋሳ እየተደረገ ያለውን የኢትዮጵያ ሴቶች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የፊታችን ቅዳሜ በሚደረጉ የደረጃ እና የፍጻሜ ጨዋታዎች ይጠናቀቃል፡፡ በሀዋሳ ከተማ ከሐምሌ 19 ጀምሮ በአስር ክለቦች መካከል በሁለት ምድቦች ተከፍሎ ሲደረግ የነበረው የኢትዮጵያ ሴቶች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና አስቀድሞ በተደረጉ ጨዋታዎች ስምንት ክለቦች ወደ 2014 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ማደጋቸውን ያረጋገጡ ሲሆንዝርዝር

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚሳተፍበት የሴቶች የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የምስራቅ አፍሪካ ዞን የማጣሪያ ውድድር ለሁለት ጊዜ ከተገፋ በኋላ የሚካሄድበት ቀን ታውቋል። በቀጣይ ዓመት በግብፅ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የመጀመሪያው የሴቶች የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የአህጉሩ የሊግ አሸናፊ ክለቦች በስድስት ዞን ተከፋፍለው የማጣሪያ ጨዋታዎችን እንደሚያደርጉ መገለፁ ይታወቃል። በሴካፋ ዞን የሚገኙ የቀጠናው የሊግዝርዝር

በ2022 የሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ አቻውን የሚገጥመው የሩዋንዳ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾች ጥሪ አቅርቧል። በ2022 በኮስታሪካ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የሴቶች የዓለም ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር ላይ የሚሳተፉ ሀገራት የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ማድረግ ጀምረዋል። በአህጉራችን አፍሪካም የመጀመሪያ ዙር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ተደርገው ሲገባደዱ የሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎች ደግሞዝርዝር

ባጣቸው በርካታ ተጫዋቾችን ምትክ ከሰሞኑ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ እየቀላቀለ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ትናንት አመሻሽ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡ ግብ ጠባቂዋ ብርሀን ባልቻ ወደ ድሬዳዋ አምርታለች፡፡ ከሻሸመኔ ከተማ ሀዋሳን ከተቀላቀለች በኋላ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በሀዋሳ በተጠባባቂ ግብ ጠባቂነት ያሳለፈችው ተጫዋቿ በሁለት ዓመት ውል ለድሬዳዋ ፊርማዋን አኑራለች፡፡ ፈጣኗ አጥቂ ቤተልሄም ታምሩዝርዝር

በሁለት ምድብ ተከፍሎ በአስር ክለቦች መካከል በሀዋሳ ሲደረግ የነበረው የክልል ክለቦች ሻምፒዮና የምድብ ጨዋታዎች ተጠናቀዋል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን የሚያድጉ ክለቦችን ለመለየት ለመጀመሪያ ጊዜ እየተደረገ ያለው ይህ ውድድር ከቀናቶች በፊት አላፊ ስድስት ቡድኖች ተለይተው የታወቁ ሲሆን የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ትላንት በሀዋሳ ግብርና ኮሌጅ ተከናውነው ቀሪዎቹ ሁለት ቡድኖቹምዝርዝር

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተሳታፊው ድሬዳዋ ከተማ የመስመር ተከላካይ አስፈርሟል፡፡ በርካታ ተጫዋቾች ወደተለያዩ ክለቦች ያመሩበት የአሰልጣኝ ብዙዓየሁ ጀምበሩ ቡድን ድሬዳዋ ከተማ እንደ አዲስ ክለቡን እየገነባ የሚገኝ ሲሆን ትዕግስት ዳዊትን ዘጠነኛ ፈራሚው አድርጓል፡፡በሀዋሳ ከተማ የክለብ የእግር ኳስ ህይወቷን በ2004 የጀመረችሁ የመስመር ተከላካይዋ ሀዋሳን ከለቀቀች በኋላ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታትዝርዝር

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተካፋዩ አዳማ ከተማ የሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲፈፅም አራት ነባር ተጫዋቾቹን ውል ደግሞ አድሷል። የዋና አሰልጣኙ ሳሙኤል አበራን ውል ያራዝማል ወይንስ አዲስ አሰልጣኝ ይሾማል የሚለው ጉዳይ ሳይጠናቀቅ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተወዳዳሪው አዳማ ከተማ በሌሎች የቡድኑ አሰልጣኞች መሪነት አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረም እናዝርዝር

የአሰልጣኝ ብዙአየው ጀምበሩን ውል ያደሰው እና አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ከአንድ ቀን በፊት ያስፈረመው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮኑ ድሬዳዋ ከተማ በዛሬው ዕለት ደግሞ ተጨማሪ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአንድ ነባር ተጫዋችን ውልም አድሷል፡፡ ተከላካይዋ ፀሐይ ኢፋሞ ወደ ቀድሞው ክለቧ ድሬዳዋ ከተማ ከአራት ዓመታት በኃላ በድጋሚ የሚመልሳትን ዝውውር አጠናቃለች፡፡ የቀድሞዋዝርዝር