የሴቶች እግርኳስ (Page 70)

አልጄርያ 1-0 ኢትዮጵያ  የአፍሪካ ዋንጫ 1ኛ ዙር ማጣርያ ሀማዲ ስታድየም ተጠናቀቀ! ጨዋታው በአልጄርያ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ የመልሱ ጨዋታ ከ15 ቀናት በኀላ አአ ላይ ይደረጋል፡፡ 81′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ብርቱካን ገብረክርስቶስ ወጥታ ረሂማ ዘርጋ ገብታለች፡፡ 74′ ህይወት በግምት ከ40 ሜትር የመታችውን ቅጣት ምት ታክኒት ይዛባታለች፡፡ ታክኒት የሚመቱባትን ኳሶች በአግባቡ መቆጣጠርዝርዝር

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ትላንት አልጄርያ ገብቷል፡፡ ቡድኑ አልጄርያ ሲደርስ በአልጄርያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አቀባበል የተደረገለት ሲሆን በዛሬው እለት በሚጫወቱበት ሜዳ ልምምዳቸውን አከናውነዋል፡፡ ቡድኑ ዴር ዲአፍ በተባለ ሆቴል ያረፈ ሲሆን በሆቴሉ ደረጃ እና በሚደረግላቸው መስተንግዶ ደስተኛ መሆናቸውን አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ አሰልጣኝ ብርሃኑ አክለውምዝርዝር

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከአልጄርያ ጋር ለሚያደርገው የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ ትላንት ምሽት ወደ አልጀርስ አቅንቷል፡፡ ሉሲዎቹ ትላንት ጠዋት በአዲስ አበባ ስታድየም የመጨረሻ ልምምዳቸውን በሰሩበት ወቅት በስፍራው የተገኘችው ሶከር ኢትዮጵያ ከቡድኑ ወሳኝ ተጫዋቾች መካከል ዋንኛ ከሆኑት ብርቱካን ገብረክርስቶስ እና ሽታዬ ሲሳይ ጋር አጭር ቆይታ አድርጋለች፡፡ በብሄራዊ ቡድኑ ከፍተኛዝርዝር

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ወደ አልጄርያ ከማቅናቱ በፊት የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ ስታድየም አድርጓል፡፡ በሉሲዎቹ የመጨረሻ ልምምድ ላይ የተገኘችው ሶከር ኢትዮጵያ ከዋና አሰልጣኙ ብርሃኑ ግዛው ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡ እኛም ለእናንተ ለአንባቢያን በሚመች መልኩ እንዲህ አሰናድተነዋል፡- ዝግጅት ‹‹ ያለፉትን 20 ቀናት ዝግጅትዝርዝር

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለ2016 የካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከአልጄርያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ዛሬ ምሽት ወደ ስፍራው ያቀናል፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ በመጀመርያው ምርጫ 30 ተጫዋቾችን በመያዝ በሱሉልታ ልምምድ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ካለፈው ሳምንት ጀምሮ 25 ተጫዋቾችን በመያዝ በአዲስ አበባ ስታድየም ዝግጅቱን ቀጥሏል፡፡ ዛሬ ጠዋት ደግሞ ወደ አልጀርስ የሚያቀኑ 20ዝርዝር

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለ2016 የካሜሩን የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ የሚያደርገውን ዝግጅት ቀጥሏል፡፡ አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ከ2 ሳምንት በፊት ከመረጧቸው 30 ተጫዋቾች መካከል 5 ተጫዋቾችን በመቀነስ 25 ተጫዋቾችን የያዙ ሲሆን የኤሌክትሪኳ ፅዮን ፈየራ ፣ የዳሽን ቢራዋ ሰርካዲስ ጉታ ፣ የደደቢቷ ፍሬወይኒ ገብረመስቀል እና የአዳማ ከተማዋ ገነት ፍርዴ ተቀንሰዋል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊሷዝርዝር

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በሴፕቴምበር 2016 በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የመጀመርያውን የማጣርያ ጨዋታ ከአልጄርያ ብሄራዊ ቡድን ጋር በዚህ ወር መጨረሻ ያደርጋል፡፡  በአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመሩት ሉሲዎቹ መቀመጫቸውን በአፋረንሲስ ሆቴል ያደረጉ ሲሆን በዛሬው እለት ዝግጅታቸውን ጀምረዋል፡፡ የመጀመርያ ልምምዳቸውንም ዛሬ ጠዋት ሱሉልታ በሚገኘ ሜዳ አከናውነዋል፡፡ በዛሬው የልምምድ ፕሮግራም ቡድኑዝርዝር

  የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የካቲት 27 ከአልጄርያ ጋር ለሚያደርገው የ2016 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ በመጪው የካቲት 10 ዝግጅት ይጀምራል፡፡ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣን ሆነው የተመረጡት አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ለዝግጅታቸው 30 ተጫዋቾችን የጠሩ ሲሆን የአምናው የፕሪሚየር ሊግ እና የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ቻምፒዮን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 11 ተጫዋቾችን አስመርጧል፡፡ ከ17 አመት በታችዝርዝር