የሴቶች እግርኳስ (Page 71)

የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ እና የጥሎ ማለፍ አሸናፊ የሚገናኙበት የኢትዮጵያ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ መስከረም 19 ይካሄዳል ቢባልም በእለቱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከቦትስዋና አቻው ጋር በጋቦሮኒ የወዳጅነት ጨዋታ የሚያደርግ በመሆኑ ጨዋታው በተያዘለት ቀን የመደረጉ ሁኔታ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የውድድር እና ስነስርአት ኮሚቴ ጨዋታው መስከረም 19 ቀን 2008 ዓ.ም እንደሚካሄድ መረጃዝርዝር

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከቡርኪና ፋሶ ጋር በኦጋዱጉ በቀጣይ ቅዳሜ የሚያደርገው የጠአለም ከ20 አመት በታች ሴቶች ማጣርያ ጨዋታ በሃገሪቱ ባለው አለመረጋጋት ምክንያት በቡርኪና ፋሶ የመካሄዱ ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ ለ27 አመት ስልጣን ላይ ቆይተው ባለፈው አመት ከስልጣን የተወገዱት ብሌስ ኮምፓሬ ታማኝ እንደሆነ የሚነገርለት በጄኔራል ጂልበርት ዴንዴሬ የሚመራ የቡርኪናፋሶዝርዝር

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከቡርኪና ፋሶ አቻቸው ጋር ለዓለም ከ20 አመት በታች ዋንጫ 2ኛ ዙር ማጣርያ የሚያደርጉትን ዝግጅት በባህርዳር ማድረጋቸውን ቀጥለዋል፡፡ ቡድኑ ከአነጋጋሪው የበረራ ችግር በኋላ ባህርዳር ላይ ካሜሩንን 2-1 በማሸነፍ በድምር የ2-1 ውጤት ወደ ተከታዩ የማጣርያ ዙር ካለፈ በኋላ የአንድ ወር እረፍት ተሰጥቶት የቆየ ሲሆን ከእረፍት መልስዝርዝር

ሶከር ኢትዮጵያ በ2007 አመት በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ ተፅእኖ ያሳረፉ ግለሰቦች እና ተቋማትን መርጣለች፡፡ በምርጫው ሂደት ላይ የሶከር ኢትዮጵያ ኤዲተሮች እና የድረ-ገፁ አንባብያን ተሳትፈዋል፡፡ በምርጫው መሰረትም ድሬዳዋ ከነማን ወደ ፕሪሚር ሊግ የመራው አሰልጣኝ መሰረት ማኒ ‹‹ የሶከር ኢትዮጵያ የአመቱ ሰው›› በሚል ተመርጣለች፡፡ በዚህም መሰረት ሶከር ኢትዮጵያ የእውቅና የምስክር ወረቀት ለአሰልጣኝ መሰረትዝርዝር

2007 ተገባዶ 2008ን ልንቀበል የቀሩን 5 ቀናት ብቻ ናቸው፡፡ እየተገባደደ ባለው 2007 በእግርኳሳችን ውስጥ በርካታ ክንውኖች ተከናውነዋል ፣ አነጋጋሪ ክስተቶች ተከስተዋል ፣ አስደሳች እና አሳዛኝ አጋጣሚዎች ተከስተዋል ፣ በርካታ ግለሰቦች እና ተቋማትም በ2007 በእግርኳሳችን መነጋገርያ ሆነዋል፡፡ በሃገር ውስጥ የእግርኳስ ጉዳዮች ላይ የምትሰራው ሶከር ኢትዮጵያም የ2007 አመት መገባደድን አስመልክቶ የአመቱ ሰውዝርዝር

ዛሬ ባህር ዳር ላይ በተካሄደው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ የካሜሮን አቻውን አስተናግዶ የነበረው የአኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 2ለ1 በሆነ ውጤትአሸንፏል፡፡ ያውንዴ ላይ 0ለ0 የተለያየው ብሄራዊ ቡድኑ በባህር ዳሩ ግጥሚያ በሎዛ አበራ ሁለት ግቦች ታግዞ ወደ ቀጣዮ ዙር አልፏል፡፡ ሎዛ ግቦቹን በመጀመሪያው እና ሁለተኛው አጋማሽ አስቆጥራለች፡፡ዝርዝር

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የሰሞኑ መነጋገርያ ከሆነው የበረራ ችግር እና እንግልት በኋላ ባለፈው ረቡእ ማታ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል፡፡ ፌዴሬሽኑም ከተከሰተው ችግር እና አጠቃላይ የቡድኑ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ዛሬ በኢትዮጵያ ሆቴል መግለጫ ሰጥቷል፡፡ እኛም የመግለቻውን ዋና ዋና ሃሳቦች እንዲህ አቅርበናቸዋል፡፡   ‹‹ ለተከሰተው ችግር ተጠያቂዎቹ ካሜሩኖች ናቸውዝርዝር

  ብሄራዊ ሊግ የብሄራዊ ሊግ የምድብ ድልድል ከ20 ቀናት በኋላ እንደሚወጣ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለመግባት በ24 ክለቦች መካከል የሚደረገውን ፉክክር ድሬዳዋ እንድታስተናግድ መመረጧ የሚታወስ ሲሆን ከየዞናቸው (ብሄራዊ ሊጉ በ8 ዞኖች ተከፋፍሎ እየተካሄደ ይገኛል) ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁ በአጠቃላይ 24 ቡድኖች በ6 ምድብ ተከፍለው የማጠቃለያ ውድድራቸውን ያደርጋሉ፡፡ዝርዝር

-የኢትዮጵያ ዋንጫ (ጥሎ ማለፍ) ግማሽ ፍፃሜ እና ፍፃሜ ጨዋታዎች ወደ ቀጣዩ አመት ተዘዋውረዋል፡፡ ፌዴሬሽኑ የክለቦች የበጀት አመት ሰኔ 30 በመጠናቀቁ ጨዋታዎችን ማከናወን እንዳልቻለ ተነግሯል፡፡ የዘንድሮው ውድድር በህዳር ወር ቢጀመርም የጨዋታዎች ቀን በተደጋጋሚ ተቀይረዋል፡፡ በግንቦት ወር ሊካሄዱ የነበሩት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ወደ ሰኔ ፤ ሰኔ 23 ሊካሄዱ የነበሩት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋዎችዝርዝር

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ወንጂ ላይ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ 10 ብድኖችን በሁለት ምድብ ከፍሎ ሲያፋጥጥ የነበረው ፕሪምየር ሊጉ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ተሸጋግሯል፡፡ ከምድብ 1 የአምና አሸናፊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ዳሽን ቢራ አልፈዋል፡፡ ከምድብ ሁለት ደደቢት እና ሲዳማ ቡና ወደ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል፡፡ በግማሽ ፍፃሜው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡናዝርዝር