የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ የሆኑት ንግድ ባንኮች የወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ውል ሲያድሱ አንድ ተጫዋቾችም ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል። በአሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመራው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2014 የሴቶች ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ከሆነ በኋላ በሴካፋ የቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ውድድር ላይ ከመካፈሉ በፊት ናርዶስ ጌትነት፣ ብርቄ አማረ፣ መሳይ ተመስገን እና አርየት ኦዶንግ ያስፈረመ ሲሆን በዛሬው ዕለትRead More →

ያጋሩ

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ያጠናቀቀው አርባምንጭ ከተማ የአሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ እና ረዳቶቹን ውል አራዝሟል፡፡ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ከሌሎች ዓመታት በተሻለ ተፎካካሪነቱ ዐይሎ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በደረጃ ሰንጠረዡ አምስተኛ ላይ ተቀምጦ ያገባደደው አርባምንጭ ከተማ የዋና አሰልጣኙ ዮሴፍ ገብረወልድን ኮንትራት ለተጨማሪ አንድ ዓመት አድሷል፡፡ የቀድሞው የሀዋሳ ከተማRead More →

ያጋሩ

አዲሷ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጫዋች መሳይ ተመስገን በሴካፋ የቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ውድድር እና ዝግጅት ዙሪያ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርጋለች። የአፍሪካ እግር ኳስ የበላይ አካል የሆነው ካፍ ከዓምና ጀምሮ የእንስቶች የቻምፒየንስ ሊግ ውድድርን ማዘጋጀት እንደጀመረ ይታወቃል። በአህጉሩ በሚገኙ ስድስት ቀጠናዎች የማጣሪያ ውድድሮች ተከናውነው አሸናፊዎቹን የሚያሳትፈው ትልቁ የሴት ክለቦች ውድድር ዘንድሮRead More →

ያጋሩ

የሴካፋ ዞን የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የማጣሪያ ውድድር ለማድረግ ከነገ በስትያ ወደ ዳሬ ሰላም የሚያቀናውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስብስብ ሶከር ኢትዮጵያ አግኝታለች። ለሁለተኛ ጊዜ በሚደረገው የአፍሪካ ሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የቀጠናውን የማጣሪያ ውድድር ለማድረግ እየተዘጋጀ የሚገኘው የወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከነገ በስትያ ሀሙስRead More →

ያጋሩ

ለተከታታይ ሁለተኛ በድምሩ ለስድስተኛ ጊዜ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን ያጠናቀቀችው እና ከንግድ ባንክ ጋር ተከታታይ የሊጉን ዋንጫ ያነሳችው አጥቂዋ ሎዛ አበራ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታን አድርጋለች፡፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ በ2004 ጅምሩን ቢያደርግም ከሊጉ ጋር ትውውቅ የጀመረችው 2005 ለሀዋሳ ከተማ በመጫወት ነበር፡፡ ቀስ በቀስ በምታሳየው አስደናቂ አቅምRead More →

ያጋሩ

👉”ተጫዋቾቼ ጀግኖች ናቸው ፤ ትክክለኛ ባለሙያን የሚሰሙ ክለባቸውን የሚያገለግሉ ፣ ለሀገራቸውም ሟች ናቸው።” 👉”ወንዱ ሸራተን ይሸለማል ፤ ሴቱ ላይ ግን ሜዳ ላይ እንኳን 34 ላገባችው ሎዛ አይነገርም።” 👉”እኔ 23 ዓመት የሰራሁ ባለሙያ ነኝ ፤ በማንም ማስፈራራት የምረበሽ ሰው አይደለሁም” 👉”በ11 ዓመታት ውስጥ 5 ዋንጫ ማሳካት የቻለ ጠንካራ ቡድን ነው ያለን”Read More →

ያጋሩ

በአሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው የሚመራው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2014 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ የሆነበትን ዋንጫ አንስቷል፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳሰ ፌድሬሽን ስር የሚደረገው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ2014 የውድድር ዘመን በአስራ ሦስት ክለቦች መካከል በየጊዜው ሲቆራረጥ ሰንብቶ በመጨረሻም በዛሬው ዕለት ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ በሀዋሳ ከተማ ጅምሩን ካደረገ በኋላ በባህርዳር እንዲሁም የሁለተኛው ዙርRead More →

ያጋሩ

ሊጠናቀቅ የአንድ ሳምንት ዕድሜ ብቻ በቀረው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የዛሬ ጨዋታዎች የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ ድሬዳዋ ከተማ ፣ ጌዲኦ ዲላ እና አዳማ ከተማ ሲያሸንፍ አርባምንጭ ከተማ ከ አዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነጥብ ተጋርተዋል፡፡ ድሬዳዋ ከተማ ቦሌን 1ለ0 ሲረታ አርባምንጭ ከተማ ከ አዲስRead More →

ያጋሩ

ሊጠናቀቅ የሁለት ሳምንት ጨዋታዎች የቀሩት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ24ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ሲደረጉበት የሊጉ ቻምፒዮን የሆነው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ሽንፈት ሲገጥመው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ዓመቱን ሁለተኛ ሆኖ መፈፀሙን አረጋግጧል፡፡ ድሬዳዋ ፣ ቦሌ እና መከላከያም ተጋጣሚዎቻቸውን ረተዋል፡፡ ሀዋሳ በጭማሪ ደቂቃ ጎል ከአርባምንጭ ጋር ነጥብ ሲጋራ ድሬዳዋ ከተማRead More →

ያጋሩ

23ኛ ሳምንቱ ላይ በደረሰው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ንግድ ባንክ የሊጉ ቻምፒዮን እንደሆነ ሲያውጅ በሌሎች ጨዋታዎች ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ድሬዳዋ ከተማ አሸንፈዋል። 3፡00 ላይ የተደረጉ ጨዋታዎች በኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊነት ተጠናቀዋል ረፋድ ላይ ዝናባማ በነበረው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ቦሌ ክፍለ ከተማ ጨዋታ በአበበ ቢቂላ ስታዲየምRead More →

ያጋሩ