በሐምሌ ወር መጀመሪያ በሀዋሳ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ከ17 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ክለቦችን ለመለየት ይረዳ ዘንድ በተለያዩ ክልሎች የውስጥ ውድድሮች እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ከ2006 እስከ 2010 ድረስ ሲካሄድ ቆይቶ አብዛኛዎቹ የየክለቦቹ ተጫዋቾች ተማሪ በመሆናቸው በጉዞ ምክንያት ከትምህርታቸው እንዳይስተጓጎሉ በሚል ምክንያት በየክልሎቹ እንዲደረጉRead More →

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከ2010 በኋላ ያልተደረገውን ውድድር በሐምሌ ወር ዳግም እንደሚጀምር ገልጿል። በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የ16 ሳምንታት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድርን ግምገማ በኢንተር ኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል እያከናወነ ይገኛል። የሥነ-ስርዓቱ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ በሀምሌ ወር ፌዴሬሽናቸውRead More →

ከዓምናው የተሳታፊ ቁጥሩ የጨመረው የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው ከ17 ዓመት በታች የታዳጊዎች ውድድር የምድብ ድልድል ሥነ ሥርዓት ትናንት ተካሄደ። ከ2011 ጀምሮ በአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሥር መካሄድ የጀመረው ከ17 ዓመት በታች የታዳጊዎች ውድድር ዘንድሮ ቁጥሩ ከ10 ወደ 15 ቡድኖች ከፍ በማለት ይካሄዳል። ትናንት በአራት ኪሎ በወጣቶች ትምህርትና ሥልጠና ማዕከልRead More →

በአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው ከ17 ዓመት በታች ውድድር ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ሲካሄዱ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሐሌታ እና ኢትዮ ኤሌትሪክ አሸንፈዋል። በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ሜዳ ከተደረጉ ሦስት ጨዋታዎች መካከል 03:00 ላይ ሐሌታን ከሠላም ያገናኘው ጨዋታ በሐሌታ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። ብዙም ሳቢ ባልሆነ እንቅስቃሴ እና መሐል ሜዳ ላይ ተገድቦ በተጠናቀቀውRead More →

ዛሬ በኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል በተደረገ ሥነ ስርዓት የ2010 የውድድር ዓመት በኮከብነት የተመረጡ ተጫዋቾች ፣ አሰልጣኞች እና ዳኞች ሽልማታቸውን ተቀብለዋል። በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር በሚደረጉት ውድድሮች ጥሩ ብቃት ላሳዩ ስፖርተኞች ከ1977 ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው ሽልማት አምና በተለየ መልኩ በአንድ መድረክ ላይ መከናወን የጀመረ ሲሆን ዛሬም የ2010 ኮከቦችን ተሸላሚ አድርጓል። 03፡00 ላይRead More →

በባቱ ከተማ ያለፉትን 10 ቀናት ሲከናወን የቆየው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር በዛሬው እለት ሲጠናቀቅ ሀዋሳ ከተማ ለ3ኛ ተከታታይ የውድድር ዓመት ቻምፒዮን የሆነበትን ድል አስመዝግቧል። 03:00 ላይ ከፍፃሜው ጨዋታ በፊት ለደረጃ የተጫወቱት አፍሮ ፅዮን እና ወላይታ ድቻ መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1-1 በሆነ ውጤት በማጠናቀቃቸው በቀጥታ ወደRead More →

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የማጠቃለያ ውድድር ዛሬ ረፋድ በባቱ ከተማ ተጀምሯል። አራት ጨዋታዎች ዛሬ ሲከናወኑ አፍሮ ጽዮን፣ ወጣቶች አካዳሚ፣ ማራቶን እና አዳማ ከተማ አሸንፈዋል። በምድብ ሀ 03:00 ላይ በባቱ ስታድየም በተደረገው የአፍሮ ጽዮን እና ወላይታ ድቻ ጨዋታ በአፍሮ ጽዮን የበላይነት እና 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። ግብ ባልተቀጠረበት የመጀመርያ አጋማሽ አፍሮ ጽዮኖችRead More →

የኢትዮጵያ ከ17 እና 20 ዓመት በታች የማጠቃለያ ውድድሮች የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ዛሬ በባቱ ከተማ ተከናውኗል።  የእጣ ድልድሉ እና የመጀመርያ ጨዋታዎች የሚከተሉት ናቸው፡- ከ20 ዓመት በታች ውድድር ምድብ ሀ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ መከላከያ፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ፣ ደደቢት ሀሙስ ሐምሌ 5 ቀን 2010 08:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ጥሩነሽ ዲባባ (ባቱ ስታድየም)Read More →

2010 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች እና 20 ዓመት በታች ሊጎች የማጠቃለያ ውድድሮች በባቱ ከተማ እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ከሐምሌ 5 እስከ 15 ጨዋታዎቹ የሚካሄዱበት ቀናት ናቸው። ሁለቱም ውድድሮች በሁለት ምድቦች ተከፍለው እየተካሄዱ የሚገኙ ሲሆን የ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ባለፈው ሳምንት ተጠናቋል። ከ17 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግRead More →

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትላንት እና ዛሬ ተደርገው የየምድቦቹ መሪዎች ሀዋሳ ከተማ እና አፍሮ ፅዮን አሸንፈዋል። በምድብ ሀ መሪው ሀዋሳ ከተማ በሜዳው ሲዳማ ቡናን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የመጀመሪያ አጋማሽ በሁለቱም በኩል አመርቂ እንቅስቃሴ የታየበት ሲሆን ገና በ3ኛው ደቂቃ የውድድሩRead More →