የወጣቶች እግርኳስ (Page 2)

በአሠልጣኝ እንድሪያስ ብርሃኑ የሚመራው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለአቋም መፈተሻ ጨዋታ ከነገ በስትያ ወደ እስራኤል ያቀናል። ባልተለመደ መልኩ የኢትዮጵያ ወንዶች ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የአቋም መፈተሻ ጨዋታ እንዲያደርግ እንደታሰበ እና ጨዋታውንም ከሀገር ውጪ ለማከናወን እንደታቀደ እና እግርኳስ ፌዴሬሽኑም የኢትዮጵያ እና የሌሎች ሀገሮችን እግርኳሳዊ ወዳጅነት ለማጠናከር ከበርካታ የአቻዝርዝር

በጌዲኦ ዲላ ስፖርት ክለብ አስተናጋጅነት በጌዲኦ በ8 ዞን ከአምስቱም ከተማ አስተዳደር በተወጣጡ 16 ክለቦች መካከል ሲካሄድ የሰነበተው ከ17 ዓመት በታች ውድድር በተስፋ ስንቅ አሸናፊነት ተጠናቋል። ዛሬ በተከናወነው የፍፃሜ ጨዋታ ላይ የጌዴኦ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዩሴፍ ማሩ (ዕጬ ዶ/ር) እንዲሁም የክለቡ የቦርድ አባልና የዞኑ ዋና አስተዳደር ተወካይ በክብርዝርዝር

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እየተካሄደ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከ17 ዓመት በታች የማጠቃለያ ውድድር ሦስተኛ የጨዋታ ቀን መድን፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አዳማ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል። ጠዋት ላይ የተገናኙት ኢትዮጵያ መድን እና መከላከያ ያደረጉት ጨዋታ በመድን አሸናፊነት ተጠናቋል። ጥሩ ፉክክር ባስተናገደው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ወደ ጎል በመድረስ እና ኳሱን ተቆጣጥረው በመጫወት የተሻሉ የነበሩትዝርዝር

ትልቅ ተጫዋች ለመሆን ከልጅነቱ ጀምሮ ያደረበት የእግርኳስ ፍቅር በፕሮጀክት ጀምሮ ዛሬ የሀድያ ሆሳዕና ዋናው ቡድን እስከመጫወት አድርሶታል። ተስፈኛው አጥቂ ደስታ ዋሚሾ ተወልዶ ያደገው በሀድያ ከተማ ልዩ ስሟ ጊቤ ወረዳ በምትባል ሠፈር ነው። በእግርኳስ ፍቅር የተለከፈው ደስታ በአሰልጣኝ አብነት ስር በሠፈር በፕሮጀክት ታቅፎ እግርኳስን በእውቀት መሠልጠን ጀመረ። ብዙም ሳይቆይ በ2011 በሀድያዝርዝር

ከቀናት በፊት በሁለት ምድቦች ተከፍሎ በሁለት ከተሞች ሲካሄድ በነበረውና በአዳማ ከተማ አሸናፊነት በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ዙርያ በተከታዩ ፅሁፍ የተወሰኑ ነጥቦችን ለማንሳት ወደናል። አስራ አራት ተሳታፊ ቡድኖች በአዳማ እና አሰላ ከተማ ላለፉት ወራት ሲያደርጉት የቆየው ውድድር በርከት ያሉ ሁነቶችን አስመልክቶን በሳምንቱ መጨረሻ ተጠናቋል። በየምድብ ውድድሮች ብሎም በማጠቃለያውዝርዝር

በሐምሌ ወር መጀመሪያ በሀዋሳ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ከ17 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ክለቦችን ለመለየት ይረዳ ዘንድ በተለያዩ ክልሎች የውስጥ ውድድሮች እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ከ2006 እስከ 2010 ድረስ ሲካሄድ ቆይቶ አብዛኛዎቹ የየክለቦቹ ተጫዋቾች ተማሪ በመሆናቸው በጉዞ ምክንያት ከትምህርታቸው እንዳይስተጓጎሉ በሚል ምክንያት በየክልሎቹ እንዲደረጉዝርዝር

በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ የሆነው የወላይታ ድቻ ቡድን ከውድድር ውጪ መሆኑ ታውቋል፡፡ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የምድብ ሀ ተሳታፊ በመሆን አሰላ ላይ በመጀመሪያው ዙር በሰበሰው 12 ነጥብ በመሪነት ያጠናቀቀው ይህ ቡድን በአዳማ ለሚደረገው የሁለተኛው ዙር የሊጉ ጨዋታዎች በበጀት ምክንያት እንዳይሄድ በክለቡ አመራሮች በመገለፁ መበተኑንዝርዝር

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከ2010 በኋላ ያልተደረገውን ውድድር በሐምሌ ወር ዳግም እንደሚጀምር ገልጿል። በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የ16 ሳምንታት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድርን ግምገማ በኢንተር ኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል እያከናወነ ይገኛል። የሥነ-ስርዓቱ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ በሀምሌ ወር ፌዴሬሽናቸውዝርዝር

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ከተማን ከመመራት ተነስቶ በመጨረሻዎቹ ስድስት ደቂቃዎች ባስቆጠሩት ጎል 2ለ1 በማሸነፍ አንድ ቀሪ ጨዋታ እየቀረው የሊጉ ቻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ክለቡ አሸናፊነቱን እንዲያረጋግጥ ተቀይራ ገብታ ሁለት ግብ ያስቆጠረችው ተስፈኛዋ አጥቂ ፎዚያ መሐመድ ከጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ ስሜቷን ለሶከር ኢትዮጵያ አጋርታለች፡፡ ትውልድ እና ዕድገቷ በምዕራብ ጎጃም ዞን ዱርቤቴ በምትባል አካባቢዝርዝር

በአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስር በሁለት ምድብ ተከፍሎ አስራ ሦስት ቡድኖችን የሚካፈሉበት ከ17 ዓመት በታች የታዳጊዎች ውድድር ዛሬ በይፋ ተጀምሯል። ረፋድ ሦስት ሰዓት ጎፋ ሜዳ ላይ መከላከያን ከ ሀሌታ ያገናኘው ጨዋታ በአንድ አቻ ውጤት ተጠናቋል። ሳቢ ያልነበረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ብዙም የግብ ማግባት አጋጣሚዎችን ሳያስመለክተን ቢቀጥልም የተሻለ ለመንቀሳቀስ ጥረት ሲያደርጉዝርዝር