ዘንድሮ በተለይም ደግሞ በቅርብ በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ላይ ደምቆ የወጣው እና ለመጀመሪያ ጊዜ በብሔራዊ ቡድን ጥሪ ውስጥ የተካተተው ወጣቱ የአዳማ ከተማ አጥቂ ዮሴፍ ታረቀኝ የዛሬ እንግዳችን ነው። ትውልድ እና ዕድገቱ መቂ ከተማ ነው። ከልጅነቱ አንስቶ ለእግርኳስ በነበረው ከፍተኛ ፍላጎት በሰፈር ውስጥ መጫወት የጀመረው ይህ ተስፈኛ ወጣት በ2012 በመቶዎች ከሚቆጠሩ ታዳጊዎችRead More →

👉”በፕሮጀክት እና በሰፈር ስጫወት የአጥቂ መስመር ተጫዋች ነበርኩ” 👉”ከልጅነቴ እንደ አርዐያ አድርጌ የወሰድኩት ተጫዋች…” 👉”አሠልጣኞቼ የሚነግሩኝን ነገር በመስማቴ እና በደንብ በመስራቴ ነው እዚህ የደረስኩት” 👉”ያሉብኝን ብዙ ክፍተቶች አስተካክዬ በብሔራዊ ቡድን ሀገሬን ማገልገል እሻለው” የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማሮውን ሀዋሳ ላይ በማድረግ በድሬዳዋ ዘልቆ በአሁኑ ሰዓት በአዳማ የሁለተኛ ዙር ውድድሩን እያከናወነRead More →

ትልቅ ተጫዋች ለመሆን ከልጅነቱ ጀምሮ ያደረበት የእግርኳስ ፍቅር በፕሮጀክት ጀምሮ ዛሬ የሀድያ ሆሳዕና ዋናው ቡድን እስከመጫወት አድርሶታል። ተስፈኛው አጥቂ ደስታ ዋሚሾ ተወልዶ ያደገው በሀድያ ከተማ ልዩ ስሟ ጊቤ ወረዳ በምትባል ሠፈር ነው። በእግርኳስ ፍቅር የተለከፈው ደስታ በአሰልጣኝ አብነት ስር በሠፈር በፕሮጀክት ታቅፎ እግርኳስን በእውቀት መሠልጠን ጀመረ። ብዙም ሳይቆይ በ2011 በሀድያRead More →

ያለፉትን ተከታታይ አምስት ጨዋታዎች በመጀመርያ አሰላለፍ በመግባት ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ እያስመለከተን ከሚገኘው ከግብ ጠባቂው አብዱልከሪም ኑሪ ጋር ቆይታ አድርገናል። በኢሉአባቡራ ገጠር ሱፔ በምትባል መንደር ተወልዷል። ይህች ገጠራማ መንደር ዕውቁ ደራሲ በዓሉ ግርማም የተወለደባት ከተማ ናት። ከልጅነቱ ጀምሮ የሆላንዳዊው ድንቅ ግብ ጠባቂ የቫንደርሳር አድናቂ በመሆን ግብ ጠባቂነትን እየወደደው እርሱን ለመሆን እየጣረRead More →

በአጭር በሆነው የአዳማ የታዳጊ ቡድን ቆይታው በአስደናቂ ሁኔታ ጎል የማስቆጠር አቅሙን እያሳየ የሚገኘው ፍራኦል ጫላ የዛሬው ተስፈኞች አምድ እንግዳችን ነው። ለበርካታ ተስፈኛ እግርኳስ ተጫዋቾች ዕድል በመስጠት በሚታወቀው አዳማ ከተማ ከ2011 ጀምሮ በሁለቱም የዕድሜ እርከኖች ማለትም ከ17 እና 20 ዓመት በታች ቡድን ውስጥ ተጫውቷል። በተለይ በ2011 በአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን አወዳዳሪነትRead More →

አጭር ከሆነ የፕሮጀክት ቆይታ በኃላ ቅዱስ ጊዮርጊስን ተቀላቅሎ በፍጥነት ወደ ዋናው ቡድን በማደግ ዘንድሮ በዝግጅት ላይ የሚገኘው እና ለወደፊት ጥሩ አማካይ እንደሚሆን የሚገመተው ፉአድ ሀቢብ የዛሬው የተስፈኞች አምዳችን ዕንግዳ ነው። በቀደመው ዘመን በተለይ ከሰማንያዎቹ መጀመርያ አንስቶ እስከ ሚሌኒየሙ አጋማሽ ድረስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊዎችን ከታችኛው ቡድን በሂደት አብቅቶ በዋናው ቡድን በማጫወትRead More →

የኢትዮጵያ የወጣቶች ፕሪምየር ሊግ በአዲስ መንገድ መካሄድ ከጀመረበት ከ2008 ጀምሮ ለተከታታይ ዓመታት ዕድገቱን ጠብቆ በመጫወት የቆየው እና ባለፈው አንድ ዓመት በኢትዮጵያ ቡና እየተጫወተ የሚገኘው ባለ ክህሎቱ ሁለገብ ተጫዋች የአብቃል ፈረጃ የዛሬው የተስፈኛ አምዳችን እንግዳ ነው። ከመስመር አጥቂነት እስከ ፊት አጥቂነት ወደ ኃላም ተመልሶ የመስመር ተከላካይ በመሆን ጭምር የአዲስ አበባ ከተማRead More →

በዛሬው የተስፈኞች አምዳችን ላይ ከፈጣኑ እና ሁለገቡ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ጋር ቆይታ አድርገናል። በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ተወልዶ ያደገው ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሮጀክት እግርኳስን የጀመረ ሲሆን በ2009 አማራ ክልልን ወክሎ ከተጫወተ በኋላ በዛው ዓመት ፋሲል ከነማ ተስፋ ተቀላቅሏል። ለሁለት ዓመት በተስፋ በቡድኑ ቆይታ ያደረገው ናትናኤል በውበቱ አባተRead More →

የኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ ፍሬ የሆነው እና በቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን መልካም ነገሮችን እያሳየ የሚገኘው ግብጠባቂ ዳዊት በኃይሉ የዛሬው ተስፈኛ ገፅ ተረኛ እንግዳ ነው። ተወልዶ ያደገው ካዛንቺስ ከፍተኛ ስድስት አካባቢ ነው። ወላጅ አባቱን አይመልከታቸው እንጂ ቀድሞ በተለያዩ ክለቦች በግብጠባቂነት ያገለግሉ እንደነበረ ከአባቱ ጓደኞች ሲሰማ እና በፎቶ ሲመለከት አድጓል። የአጋጣሚ ሆኖ በምንRead More →

በመከላከያ ከታዳጊ ቡድን አንስቶ በየዓመቱ በሚያሳየው ተከታታይ እድገት አቅሙን በማሳየት ወደ ዋናው ቡድን ማደግ የቻለው ተስፋኛው አጥቂ አቤል ነጋሽ የዛሬው ተስፈኞች አምዳችን እንግዳ ነው። በ2009 በኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ውድድር ወቅት በኢትዮጵያ ቡናው ተመስገን ዘውዴ በጥቂት ጎሎች ተቀድሞ ሁለተኛ የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን አጠናቋል። ከ17 እና 20 ዓመትRead More →