ዛሬ በተከናወነው የሁለተኛ ሳምንት የማልታ ሴቶች ሊግ ቢርኪርካራ ተጋጣሚውን ሲያሸንፍ ሎዛ አበራ ሁለት ግቦች አስቆጥራለች። ለማልታው ቢርኪርካራ በመፈረም ባለፈው ሳምንት በመጀመርያ ጨዋታዋ ለክለቡ ሁለት ግቦች አስቆጥራ አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ በማመቻቸት ጥሩ አጀማመር ያደረገችው ሎዛ አበራ ዛሬ በተደረገ ጨዋታም ሁለት ግቦች አስቆጥራለች። ቢርኪርካራዎች ተጋጣሚያቸው ኪርኮፕ ዩናይትድን 7-1 ሲያሸንፉ ኢትዮጵያዊቷ አጥቂRead More →

ወላይታ ድቻ የአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ረዳት አሰልጣኝ በማድረግ የቀድሞ የክለቡ ተጫዋቾች ግዛቸው ጌታቸው እና ዘላለም ማቲዮስን ሾሟል፡፡ ክለቡ ዐምና የአሰልጣኝ ዘነበ ፍሰሀ እና አሸናፊ በቀለ ረዳት የነበረውን ደለለኝ ደቻታን አሁንም ባለበት እንዲቀጥል በማድረግ የአሰልጣኝ ቡድኑን ለማስፋት በማሰብ ነው ተጨማሪ አሰልጣኞችን የሾመው፡፡ ወላይታ ድቻ በ2005 ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድግ የቡድኑ አምበልRead More →

ሀይቆቹ በዛሬው ዕለት ካሜሩናዊው ግብ ጠባቂ ቢሊንጌ ኢኖህ እና የቀድሞው የክለቡ የተስፋ ቡድን ተጫዋች የነበረው ወጣቱ አማካይ አቤኔዘር ዮሐንስን አስፈርመዋል፡፡ ቢሊንጌ ኢኖሆየህ ለሀገሩ ክለቦቸ ሮምዴ አድጃ እና አቺሊ ለተባሉ ክለቦች የተጫወተ ሲሆን ከስምንት ዓመታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኃላ ረጅም ዓመታት በሀገራችን የተለያዩ ክለቦች በመጫወት አሳልፏል፡፡ በሐረር ቢራ፣ ውሀ ስራዎች፣Read More →

በወጣት ተጫዋቾች እየተገነባ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና ለወደፊት ተስፋኛ መሆኑን እያሳየ የሚገኘውን ወጣቱን አጥቂ አስፈርሟል። በ2008 በክለብ ደረጃ የአዲስ አበባ ከተማ ከ17 ዓመት በታች ቡድንን በመቀላቀል ከዛም በመቀጠል ከ20 ዓመት በታች ቡድን እና ዘንድሮ ዋናው ቡድን ማገልገል ችሏል። ያለፉትን አራት ዓመታት በጥሩ ብቃት ያገለገለ የሚገኘው የመስመር አጥቂው አላዛር ሽመልስ ለኢትዮጵያ ቡናRead More →

የ2011 የኢትዮጵያ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጥቅምት 23 እንደሚካሄድ ፌዴሬሽኑ ለክለቦቹ በላከው ደብዳቤ አስታውቋል፡፡ ከአዲሱ የውድድር ዘመን ጅማሮ በፊት የክለቦች የዋንጫ ዓይን መግለጫ ተደርጎ የሚቆጠረው ይህ ውድድር በ1977 ዓ.ም ጅማሮውን ሲያደርግ በተለያዩ ጊዜያት በወጣ ገባ መልኩ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ ባሳለፍነው ዓመት መጀመሪያ ላይ መከላከያን ከጅማ አባ ጅፋር ያገናኘው ጨዋታም በመከላከያ የበላይነት መጠናቀቁRead More →

የዐምናው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን አሸናፊ አዳማ ከተማ የአሰልጣኝ ሳሙኤል አበራን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዘመ፡፡ የቀድሞው የአዳማ ከተማ፣ ሙገር ሲሚንቶ እንዲሁም የደብረብርሃን ከተማ ተጫዋች ሳሙኤል የአሰልጣኝነት ህይወቱን ጅማሮ ያደረገው በአዳማ ከተማ የተስፋ ቡድን ሲሆን ላለፉት አራት ዓመታት በአዳማ የሴቶች ቡድን አሰልጣኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡ በተስፈኛው አሰልጣኝ የሚመሩት አዳማዎች በወጣቶችRead More →

ከዲሜጥሮስ ወልደሥላሴ እና ብሩክ ተሾመ ጋር በስምምነት የተለያዩት ሽረዎች የአምስት ነባር ተጫዋቾቻቸውን ቆይታ አራዝመዋል። ቀደም ብለው የአሰልጣኝ ሳምሶን አየለን ውል በማራዘም በርካታ ተጫዋቾችን ያስፈረሙት ስሑል ሽረዎች በአንፃሩ ከሌሎች ተጫዋቾቻቸው ጋር ደግሞ ተለያይተዋል። ከቡድኑ ጋር በስምምነት የተለያዩት ሁለቱ ተጫዋቾች ባለፈው ዓመት መጀመርያ አዲስ አበባ ከተማን ለቆ ስሑል ሽረን በመቀላቀል ቡድኑን በአምበልነትRead More →

መከላከያ ከሦስት ተጫዋቾች መለያየቱ ሲረጋገጥ በቀጣይ ቀናትም ከሌሎች ተጫዋቾች ይለያያል ተብሎ ይጠበቃል። የፕሪምየር ሊጉ ፎርማት ወደ 24 ቡድኖች ማደጉ ተከትሎ በርካታ ተጫዋቾች ያስፈረሙት መከላከያዎች ቀጣይ ዓመት በከፍተኛ ሊግ እንደሚሳተፉ ከተረጋገጠ በኃላ በክረምቱ ካስፈረማቸው በርካታ ተጫዋቾች መለያየት ጀምረዋል። ቀድመው ከክለቡ ጋር የተለያዩት በዚ ዝውውር መስኮት ከድሬዳዋ ቡድኑን የተቀላቀለው አንተነህ ተስፋዬ፣ ከሃዋሳRead More →

በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ሀገር ተጫዋቾችን በሙከራ እየተመለከተ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ስኬታማ ጊዜ ያሳለፉት ሦስት ተጫዋቾችን አስፈርመዋል፡፡ በቢሾፍቱ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ላይ ባሳለፉት ሙከራ ጊዜ አሰልጣኝ ስምዖን ዓባይ ማሳመን የቻሉት ሦስት የድሬዳዋ ፖሊስ ተጫዋቾች ናቸው ክለቡን መቀላቀል የቻሉት። የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ከድር አዩብ፣ የመስመር አጥቂው ፈርዓንRead More →

በፕሪምየር ሊጉ ተሳታፊ እንደሆነ በፌዴሬሽኑ በመገለፁ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የነበረው ደቡብ ፖሊስ ውሳኔው ተሽሮ በከፍተኛ ሊጉ እንዲወዳደር በመወሰኑ ከአዲስ ፈራሚዎቹ ጋር እየተለያየ ነው፡፡ ክለቡ በውሳኔ ለውጡ መነሻነት ተጫዋቾቹን ለመልቀቅ የተገደደ ሲሆን በቀጣይም በርካታ ተጫዋቾችን እንደሚለቅ ተሰምቷል። በዚህም መሠረት ከአርባምንጭ ከተማ ክለቡን ተቀላቅለው የነበሩት አማካዩቹ ቴዲ ታደሰ እና አስጨናቂ ፀጋዬ፣ ከወላይታ ድቻRead More →