በቀጣይ ዓመት በካሜሩን የሚዘጋጀው የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ተሳታፊዎች ዛሬ ሙሉ ለሙሉ ሲታወቁ በርካታ ትላላቅ ሃገራት ወደ ውድድሩ አያመሩም። በውድድሩ በአህጉሪቱ ላይ ጥሩ ስም ያላቸው ጋና፣ ሴኔጋል፣ ደቡብ አፍሪካ እና ግብፅ የመሳሰሉ ሀገራት የማይካፈሉ ሲሆን በተቃራኒው በርካታ ያልተገመቱ ቡድኖችን ያሳትፋል። አዘጋጇ ካሜሩን፣ ታንዛንያ፣ ሩዋንዳ፣ ዩጋንዳ፣ ዛምቢያ፣ ናሚቢያ፣ ቶጎ፣ ሞሮኮ፣ ዚምባብዌ፣Read More →

ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር በፋሲል ከነማ ሲሰራ የነበረው ይታገሱ እንዳለ የሰበታ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ ሆኖ ሲሾም የግብ ጠባቂ አሰልጣኙ አዳሙ ኑሞሮ ውልም ተራዝሞለታል፡፡ የቀድሞው የአዳማ ከተማ ተጫዋች ይታገሱ በአዳማ ከተማ የታዳጊ ቡድኖችን በማሰልጠን የአሰልጣኝነት ህይወትን የጀመረ ሲሆን በ2011 ደግሞ ውበቱ አባተ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ በመሆን ሲሾሙ አሰልጣኙ በረዳትነት አብረው መስራትRead More →

በአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አስተናጋጅነት ከጥቅምት 22 ጀምሮ የአዳማ ከተማ ዋንጫ የቅድመ ዝግጅት የአቋም መፈተሻ ውድድር በከተማዋ ይካሄዳል፡፡ ውድድሩን የሚያስተናግደው ክለቡ ሲሆን ከረጅም አመት በኃላም ይህ ውድድር እንደተሰናዳ ለማወቅ ችለናል፡፡ ከ2005 በፊት በነበሩ አመታት ሲዘጋጅ እንደቆየ የተነገረው ይህ ውድድር ዳግም ከስምንት ዓመት በኃላ በደመቀ መልኩ ለማሰናዳት መዘጋጀቱን ሶከር ኢትዮጵያRead More →

ሲዳማ ቡናዎች ከወር በፊት ለመከላከያ ለመጫወት ተስማምቶ የነበረው የመስመር እና የፊት አጥቂው ሀብታሙ ገዛኸኝን በድጋሚ ማስፈረም ችለዋል፡፡ የቀድሞው የደቡብ ፖሊስ ተጫዋች ከ2010 እስከ ዐምና ድረስ በሲዳማ ቡና ሲጫወት የቆየ ሲሆን ውሉ በመጠናቀቁም በዛው በሲዳማ ቡና ይቀጥላል ሲባል የቆየ ቢሆንም ኋላ ላይ ወደ መከላከያ ማምራቱ ይታወሳል፡፡ መከላከያም በፕሪምየር ሊጉ መሳተፍ እንደማይችልRead More →

ሰበታ ከተማ ወደ መከላከያ አምርቶ የነበረው የመሀል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ አንተነህ ተስፋዬን በእጁ አስገብቷል፡፡ ከወራት በፊት ለመከላከያ ለመጫወት ፈርሞ የነበረው ተጫዋቹ ቡድኑ በከፍተኛ ሊጉ እንዲጫወት በመወሰኑ ክለቡን በስምምነት ከለቀቀ በኋላ ነው ወደ ሰበታ ሊያመራ የቻለው። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ ተካቶ የሚገኘው የቀድሞው የአርባምንጭ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ተጫዋች አንተነህRead More →

በሀዋሳ የቅድመ ውድድር ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኘው ወልቂጤ ከተማ ሳዲቅ ሴቾን ሲያስፈርም አምስት ወጣቶችንም ከተስፋ ቡድኑ አሳድጓል፡፡ በመስመር እና በፊት አጥቂነት መጫወት የሚችለው ሳዲቅ ሴቾ ከዚህ ቀደም ወዳሳለፈበት ወልቂጤ በድጋሚ ተመልሶ ፊርማውን አኑሯል፡፡ ሼር ኢትዮጵያን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ተጉዞ ከፕሪምየር ሊግ ጋር የተዋወቀው አጥቂው ቡናማዎቹን ከለቀቀ በኋላ በሀዋሳ ከተማRead More →

ጋናዊው ኦሴይ ማዊሊ ለፋሲል ከነማ ፊርማውን አኑሯል። ባለፈው ዓመት ሃፖል ናዝሬት ሊሊትን ለቆ ወደ መቐለ 70 እንደርታ በመፈረም ከምዓም አናብስት ጋር ጥሩ ዓመት ያሳለፈው የሰላሳ ዓመቱ ጋናዊ አጥቂ አብዛኛው የእግር ኳስ ህይወቱን በእስራኤሎቹ ሃፖል አሽካሎን እና ሃፖል ኢራኒ ኬርያት ሻሞና ያሳለፈ ሲሆን በኢትዮጵያ ቆይታው መቐለ የሊጉን ዋንጫ ሲያነሳ ትልቅ ሚናRead More →