የጅማ እና ሀዋሳን ጨዋታ በዳሰሳችን እንዲህ ተመልክተነዋል። የጅማ አባ ጅፋር የውድድር ዓመት የሚቃናበት ጊዜ ቅርብ አይመስልም። ቡድኑ ከድሬዳዋው ጨዋታ በኋላ የተሟላ ልምምድ ሳይሰራ ለነገው ጨዋታ ደርሷል። ዛሬ ከሰዓትም በ10 ተጫዋቾች ብቻ ልምምድ ሰርቷል። በርከት ያሉ ተጫዋቾች ክለቡን ለመክሰስ ዛሬ ወደ ፌዴሬሽን አምርተው እንደነበርም ሰምተናል። በዚህ ዓይነት የቡድን መንፈስ ውስጥ ሆኖRead More →

ያጋሩ

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሐ የሚገኘው ጌዴኦ ዲላ አስራ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾች እና ዘጠኝ ነባሮችን አስፈርሟል፡፡ ክለቡ የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያን በማውጣት እዮብ ማለን ቀጥሮ ወደ ዝግጅት ከሳምንት በፊት የገባ ሲሆን አሰልጣኙም ውላቸው ተጠናቆ የነበሩ ነባር ዘጠኝ ተጫዋቾችን ኮንትራት በማደስ እንዲሁም አዳዲስ አስራ ሶስት ተጫዋቾችን በነበረበት ክፍት ቦታ ከተለያዩ ክለቦች በማስፈረም ዝግጅቱንRead More →

ያጋሩ

ነገ የሚጀምረው አምስተኛው ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ቀዳሚ ጨዋታን አስመልክተን ይህን ብለናል። ኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ ሽንፈቱን ካስተናገደ በኃላ ዳግም ወደ ድል ለመመለስ ከሰበታ ጋር ይፋለማል። በሀዋሳው ጨዋታ ተቀዛቅዘው የታዩት ቡናዎች ውደ ቀደመው የቡድን መንፈሳቸው ተመልሰው በጥሩ መነሳሳት ወደ ጨዋታው እንደሚገቡ ይጠበቃል። ከሀዋሳ ጋር የማጥቃት ጥይታቸውን ጨርሰው የታዩት ቡናዎች ነገ ከተጋጣሚያቸውRead More →

ያጋሩ

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት መርሐ ግብሩን ከሰኞ እስከ ረቡዕ ከአናውኖ የተለያዩ ውጤቶች ተመዝግበዋል። በዚህ ሳምንት በተከናወኑ ጨዋታዎች ዙርያ ያሉ ቁጥራዊ መረጃዎች እና ዕውነታዎችን እንደሚከተለው አዘጋጅተናል። – በአራተኛ ሳምንት በተደረጉ ስድስት ጨዋታዎች 15 ጎሎች ተቆጥረዋል። በአማካይ በጨዋታ 2.5 ጎሎች ያስተናገደው የዚህ ሳምንት መርሐ ግብር ካለፉት ሳምንታት ጨዋታዎች ጋር ሲነፃፀርRead More →

ያጋሩ

በትግራይ ክልል ክለቦች ለሚገኙ ተጫዋቾች የሚሆን ልዩ የዝውውር ጊዜ ማዘጋጀቱን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። የክለቦቹ ተጫዋቾች ውል ቢኖርባቸውም ወደ ሌሎች ክለቦች እንዲያመሩ ፈቃድ ተሰጥቷቸው ገሚሶቹ ወደ ልሎች ክለቦች ሲያመሩ አመዛኞቹ ያለ ክለብ መቀመጣቸው የሚታወስ ሲሆን ይህን ተከትሎ ዛሬ ፌዴሬሽኑ በነበረው ስብሰባ ውሳኔ ሊያሳልፍ እንደሚችል መዘገባችን የሚታወስ ነው። በዚህም መሰረት ፌዴሬሽኑ በጉዳዩ ዙርያRead More →

ያጋሩ

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አራተኛ ሳምንት በተደረጉት ጨዋታዎች ላይ ጥሩ ብቃት አሳይተዋል ያልናቸውን ተጫዋቾች እና ዋና አሰልጣኝ በማካተት ተከታዩን ምርጥ ቡድን መርጠናል። አሰላለፍ 3-2-3-2 ግብ ጠባቂ ፍሬው ጌታሁን – ድሬዳዋ ከተማ በሦስተኛው የጨዋታ ሳምንት በተጠባባቂነት ይዘነው የነበረው ፍሬው በዚህ ሳምንት ደግሞ ባሳየው ብቃት ወደ መጀመሪያ ተመራጭ አድርገን አምጥተነዋል። በሳምንቱ ግብRead More →

ያጋሩ

የአራተኛ ሳምንት ዐበይት ጉዳዮችን የምናገባድደው በዚህ ሳምንት ትኩረት የሳቡ ሌሎች ጉዳዮችን በማንሳት ነው። 👉በሀዘን ውስጥ ሆነው ከክለባቸው ያልተለዩት አብነት ገ/መስቀል ከጥቂት ቀናት በፊት እህታቸውን በሞት የተነጠቁትና ሀዘን ላይ የነበሩት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ሊቀመንበር አቶ አብነት ገ/መስቀል ክለባቸው በዕለተ ሰኞ ሰበታ ከተማን 4-2 በረታበት ጨዋታ ግን ሀዘናቸውን ገታ አድርገው የክለባቸውRead More →

ያጋሩ

በአራተኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ትኩረት ሳቢ አሰልጣኝ ነክ ጉዳዮች እና ዐበይት አስተያየቶችን እነሆ ብለናል። 👉”በማሸነፍ ውስጥም ስለመሻሻል ማሰብ” የአሰልጣኞቻችን በጎ ጅምር በሀገራችን እግርኳስ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በስፋት እየተለመደ በመጣው የአሰልጣኞች ድህረ ጨዋታ አስተያየቶች ውስጥ የተሸነፈው ቡድን አሰልጣኝ በዳኝነት፣ በተጫዋቾች ጉዳት፣ በሜዳውና መሰል ጉዳዮች ላይ ሽንፈቱን ማሳበብ በተቃራኒው የአሸናፊውRead More →

ያጋሩ

የ4ኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መጠናቀቅን ተከትሎ በጨዋታ ሳምንቱ የተመለከትናቸውን ዓበይት ተጫዋች ላይ ያተኮሩ ጉዳዮች በቀጣዩ ፅሁፍ ተዳሷል። 👉የውጪ ግብ ጠባቂዎች ዋጋ የሚያስከፍሉ ጥፋቶች መበራከት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውጭ ግብጠባቂዎች በዘንድሮው የውድድር ዘመን ከቀደሙት ዓመታት አንፃር በቁጥር ረገድ መቀነስ ቢያሳይም የተቀሩት ግብጠባቂዎች እስከዚህኛው ሳምንት ድረስ በየቡድኖቻቸው የነበራቸው ተፅዕኖ ይህRead More →

ያጋሩ

4ኛ ሳምንቱ ላይ በደረሰው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በዚህኛው ሳምንት የታዘብናቸውን ዓበይት ክለብ ነክ ጉዳዮች በተከታዩ ፅሁፍ ለመዳሰስ ሞክረናል። 👉 መልክ እየያዘ የመጣው ቅዱስ ጊዮርጊስ በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በመጀመሪያው ሳምንት በፋሲል ከነማ ከተረታበት ጨዋታ ወዲህ መሻሻሎችን እያሳየ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሦስተኛ ተከታታይ ድሉን በዚህኛው ሳምንት ሰበታ ከተማ ላይ ተቀዳጅቷል።Read More →

ያጋሩ