የነገው ሁለተኛ ጨዋታ ቀጣዩ የዳሰሳችን ትኩረት ይሆናል። ወልቂጤ ከተማ በሰበታ ጨዋታ ሽንፈት አስተናግዶ ለነገው ጨዋታ ይደርሳል። ቡድኑ ጠንካራ አቋሙን ይዞ ባለመዝለቁም ወደ ላይ ከፍ ማለት የሚልባቸውን ዕድሎች በየጣልቃው በሚገጥሙት ሽንፈቶች እያጣ ለ13ኛው ሳምንት በቅቷል። ቅዱስ ጊዮርጊስ በበኩሉ ከሦስት ተከታታይ የአቻ ውጤቶች መልስ በአዳማ ላይ ድል አስመዝግቦ ነው የሚቀርበው። ቡድኑ ባስመዘገበውRead More →

ያጋሩ

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን የአስራ ሁለተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ሁለተኛ ጨዋታ በአዳማ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ መካከል ተደርጎ አዳማ 1ለ0 አሸንፎ ወጥቷል፡፡ በረዳት አሰልጣኟ የሺሃረግ ለገሰ መሪነት ወደ ሜዳ የገቡት አዲስ አበባ ከተማዎች ከዋና አሰልጣኟ ሙሉጎጃም እንዳለ እገዳ በኋላ ጨዋታ አድርጓል። በመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አዳማRead More →

ያጋሩ

ከደደቢት ተስፋ ቡድን የተገኘውና አሁን በሰበታ ከተማ ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ የእግርኳስ ህይወቱን አስመልክቶ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርጓል። አዲስ አበባ ከተማ ካሳንችስ 28 ሜዳ አካባቢ ተወልዶ አድጓል። ብዙ ባልተለመደ ሁኔታ ወላጅ አባቱ “ልጄ ትልቅ እግርኳስ ተጫዋች ይሆንልኝ ዘንድ ምኞቴ ነው።” በማለት ገና ከስምንት ዓመቱ ጀምሮ እግርኳስ ተጫዋችRead More →

ያጋሩ

የ13ኛውን ሳምንት ቀዳሚ ጨዋታ የተመለኩቱ ጉዳዮችን እንዲህ አንስተናል። ሀዋሳ ከተማ ላይ ባሳካው ድል ማንሰራራት የመጀመር ዕድል የነበረው አዳማ ከተማ በደረሱበት ተከታታይ ሽንፈቶች ወደ ሊጉ ግርጌ ወርዷል። ነገስ ‘ከአስከፊው ጉዞ ለማገገም ከጠንካራው ተጋጣሚ ነጥብ ያገኝ ይሆን ?’ የሚለው ጉዳይ ተጠባቂ ሆኗል። እንዳለው ስብስብ እና እንደሚገኝበት ሁኔታ ጥብቅ መከላከልን ምርጫው ሲያደርግ የማይታየውRead More →

ያጋሩ

በ12ኛው ሳምንት ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጥሩ የተንቀሳቀሱ ተጫዋቾችን እንደሚከተለው መርጠናል። አሰላለፍ : 4-3-3 ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑሪ – ጅማ አባጅፋር ለመጀመሪያ ጊዜ በሊጉ ሁለተኛ ተከታታይ ጨዋታውን ያከናወነው ወጣቱ የግብ ዘብ አቡበከር በአዲሱ የቡድኑ አሠልጣኝ የመጀመሪያ ጨዋታ ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል። በጥሩ ቅፅበታዊ ቅልጥፍናዎች የሲዳማ ቡናዎችን የግብ ሙከራ ሲያመከን የነበረው አቡበከር ቡድኑRead More →

ያጋሩ

በአስራ ሁለተኛ ሳምንት ላይ የተመረኮዙ ዕውነታዎች፣ ቁጥሮች እና የዲሲፕሊን መረጃዎች እንዲህ አጠናቅረናል። – በዚህ ሳምንት በተደረጉ ስድስት ጨዋታዎች 11 ጎሎች ብቻ ተቆጥረዋል። ይህም ባለፈው ሳምንት ከተቆጠረው በሦስት ያነሰ ሲሆን ከዘጠነኛው ሳምንት በመቀጠል ዝቅተኛ ጎል የተቆጠረበት የጨዋታ ሳምንት ሆኗል። – ከ11 ጎሎት መካከል አምስቱ በመጀመርያ አጋማሽ ሲቆጠሩ ስድስቱ ጎሎች ከዕረፍት በኋላRead More →

ያጋሩ

የሳምንቱን ዐበይት ጉዳዮችን የምናገባድደው እንደተለመደው ሌሎች የትኩረት ነጥቦችን በማንሳት ነው። 👉አስደናቂው የባህርዳር ዓለምአቀፍ ስታድየም መጫወቻ ሜዳ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ከ12ኛ ሳምንት አንስቶ የማስተናገድ ተራውን የወሰደው የባህርዳር ዓለምአቀፍ ስታድየም እስካሁን ውድድሩ ከተካሄደባቸው ብሎም በሀገሪቱ ከሚገኙ ስታድየሞች የምቹው የመጫወቻ ሳር ባለቤቱ ነው ቢባል ለስህተት የሚዳርግ አይመስልም። አረንጓዴማ መልኩ በጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭትRead More →

ያጋሩ

በወላይታ ድቻ ከታዳጊ ቡድን አንስቶ እስከ ዋናው ቡድን እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በተለያዩ የዕድሜ እርከኖች መጫወት የቻለው እዮብ ዓለማየሁ አሁን ስላለበት ሁኔታ ይናገራል። ከ17 ዓመት ታዳጊ ቡድን አንስቶ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ ለወላይታ ድቻ ከፍተኛ አገልግሎት ሰጥቷል። ወጣቱ ፈጣን አጥቂ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ከዋናው ብሔራዊ ቡድን ውጭ በሁሉም የዕድሜRead More →

ያጋሩ

አሰልጣኞችን የተመለከቱ የትኩረት ነጥቦች እና አንኳር አስተያየቶችን እነሆ! 👉 መተንፈሻ ጊዜ ያገኙት ማሒር ዴቪድስ ከጥቂት ሣምንታት በፊት በክለቡ አመራሮች የቡድኑን ውጤት እንዲያስተካክሉ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ደቡብ አፍሪካዊው ማሒር ዴቪድስ ከማስጠንቀቂያ በኃላ ቡድናቸውን ሀዲያ ሆሳዕናን ገጥሞ አቻ መለያየቱን ተከትሎ ጫና በርትቶባቸው ሰንብቷል። ይባስ ብሎ ክለቡ ሌላ አሰልጣኝ ለመቅጠር ዓይኑ ማማተር የመጀመሩRead More →

ያጋሩ

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን የ12ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ አርባምንጭ ከተማን አስተናግዶ 5 ለ 1 አሸንፏል፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊት የመኪና አደጋ ገጥሟቸው የነበሩት አርባምንጭ ከተማዎች ከኢትዮ ኤሌክትሪክ የነበራቸውን ጨዋታ በዚህ ምክንያት ማድረግ ሳይችሉ የአስራ ሁለተኛ ጨዋታ መርሐ ግብራቸውን ከአደጋው ነፃ ሆነው በተመለሱ ተጫዋቾች አማካኝነት አከናውኗል፡፡Read More →

ያጋሩ