ቅድመ ዳሰሳ | ጅማ አባ ጅፋር ከ ወልቂጤ ከተማ
ቀጣዩ የዳሰሳችን ትኩረት ነገ ከሰዓት የሚከናወነው ጨዋታ ይሆናል። የዓመቱ ሁለተኛ ድሉን በአዳማ ላይ ያሳካው ጅማ አባ ጅፋር ወደ ባለሁለት ቁጥር የነጥብ ስብስብ ቢያድግም አሁንም ከስጋት ለመላቀቅ ብዙ ርቀት መጓዝ ይጠበቅበታል። ጅማ ነገ ማሸነፍ ከቻለ ከቀጠናው ባይወጣም በዚህ ሳምንት አራፊ የሆነው ሲዳማን ቦታ መውሰድ ይችላል። ከሰንጠረዡ አጋማሽም መንሸራተት የጀመረው ወልቂጤ ከተማRead More →