የጨዋታ ሳምንቱ የመጨረሻ ቀን ሦስት መርሐ-ግብሮች ላይ የሚያጠነጥነው ዳሰሳችን እንደሚከተለው ተሰናድቷል። አርባምንጭ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና ካለፉት አምስት ጨዋታዎች አንዱንም ያልተረቱት አርባምንጮች በጥሩ ወቅታዊ ብቃት ላይ ይገኛሉ። በተለይ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች በድምሩ አምስት ግቦችን አስቆጥረው ያሸነፉበት ጨዋታ ምን ያህል ጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ያመላክታል። ከወትሮ በተለየ የኳስ ቁጥጥር ላይ በመጠኑRead More →

አዲስ አበባን ባለ ድል ካደረገው እና ሰበታ ከተማ ከጅማ አባ ጅፋር ጋር ተያይዞ መውረዱን ካረጋገጠበት ጨዋታ ፍፃሜ በኋላ አሰልጣኞች አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው – አዲስ አበባ ከተማ ስለድሉ “ከዕረፍት በፊት በጥሩ መንገድ ሄደናል፡፡ ከዕረፍት በኋላ ግን ትንሽ ያው ዝናቡ ጨዋታ አበላሽቶብኛል ብዬ እገምታለው፡፡ ምክንያቱም እንደተመለከታችሁት ሜዳው ከዕረፍት በፊት ለመጫወትRead More →

ሰባት ግቦችን ያስተናገደው የዕለቱ የመጨረሻ ጨዋታ የ4-3 ድል ያሳካው አዲስ አበባ ከተማን ከአደጋ ዞኑ ሲያሸሽ ሰበታ ከተማ እና ጅማ አባ ጅፋርን ከሊጉ አሰናብቷል። አዲስ አበባ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ነጥብ የተጋራበትን የመጀመሪያ አሰላለፍ ሳይለውጥ የዛሬውን ጨዋታ ጀምሯል። ሰበታ ከታማ ደግሞ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ያለግብ ከተለያየው ስብስብ በኃይሉ ግርማ እና ዴሪን ንስባምቢንRead More →

ተጠባቂው ጨዋታ በአቻ ውጤት ከተጠነቀቀ በኋላ አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል። አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት – ሀዲያ ሆሳዕና ስለጨዋታው “ጨዋታው ከሞላ ጎደል እንደሚከብድ መጀመሪያም ገልጬ ነበር። እንደጠበቅነው ነው ፤ እኛ ግን የምንፈልገው አንድ ነጥብ ነበር። ከባድ ሁኔታ ላይ ስለነበርን ውጤት አሳክተናል። እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጥንካሬ መሪም ስለሆነ አንድ ነጥብ ከእነሱ ማግኘት ለእኛRead More →

በደረጃ ሰንጠረዡ አጋማሽ የሚገኘው ሀዲያ ሆሳዕና የሊጉን መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ አስጥሎ የዋንጫውን ፉክክር አጓጊ አድርጓል። ባሳለፍነው ሳምንት ከሰበታ ከተማ ጋር ነጥብ የተጋሩት ሀዲያ ሆሳዕናዎች ዛሬ ሁለት ተጫዋቾችን ቀይረው ወደ ሜዳ ገብተዋል። በዚህም ፍሬዘር ካሣን በቃለአብ ውብሸት እንዲሁም አበባየሁ ዩሐንስን በሚካኤል ጆርጅ ተክተዋል። ቅዱስ ጊዮርጊሶች በበኩላቸው ወልቂጤ ከተማን ከረታው ስብስባቸውRead More →

በ86ኛው ደቂቃ ቢኒያም ፍቅሬ ባስቆጠራት ግብ ወላይታ ድቻዎች የጅማ አባ ጅፋርን በሊጉ የመቆየት ተስፋን አጣብቂኝ ከከተቱበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል። አሰልጣኝ የሱፍ ዓሊ – ጅማ አባ ጅፋር ስለጨዋታው “በመጀመሪያው አጋማሽ ጨዋታው በፈለግነው መልኩ የሄደ ነበር ነገርግን በሁለተኛው አጋማሽ ግን በየ3(4) ቀናት ልዮነት እንደመጫወታችን በምንፈልገው መንገድRead More →

በሁለተኛ ቀን የመጀመሪያ ጨዋታ ወላይታ ድቻዎች ከመመራት ተነስተው ጅማ አባ ጅፋርን ሲረቱ የጅማ በሊጉ የመቆየት ነገር ወደ መጨረሻው ተጠግቷል። ጅማ አባ ጅፋሮች ባለፈው የጨዋታ ሳምንት በሲዳማ ቡና ከተረታው ስብስብ ላይ ባደረጓቸው ሦስት ለውጦች አካሉ አታሞ ፣ በላይ አባይነህ እና ዳዊት እስጢፋኖስን አስወጥተው በምትካቸው የዓብስራ ሙሉጌታ ፣ ሱራፌል ዓወል እና ቦናRead More →