የኮንጎ ብሔራዊ ቡድን ለኢትዮጵያው ጨዋታ ልምምዱን ጀምሯል

ፈረንሳዊው የኮንጎ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ክላውድ ሌሮይ በ2018ቱ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ለሚያደርጉት የደርሶ መልስ ጨዋታ 21 ተጫዋቾችን በመጥራት ልምምድ እያደረጉ ይገኛሉ። አሠልጣኙ በቡድኑ ካካተቷቸው ተጫዋቾች 9ኙ በአውሮፓ ክለቦች የሚጫወቱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በኮንጎ ሊግ ከሚሳተፉ ክለቦች የተጠሩ ናቸው።

ኮንጎ በ2017ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ጊኒ ቢሳውን 4-2 ባሸነፈችበት ጨዋታ አራቱንም ግቦች ያስቆጠረው ፍሬቦሪ ዶሬ በፈረንሳይ ሊግ 1 ለክለቡ አንጀርስ ሲጫወት ባጋጠመው የእግር ስብራት ምክንያት ቀዶ ጥገና ያደረገ በመሆኑ ሀገሩ ከዋሊያዎቹ ጋር ለምታደርገው ጨዋታ እንደማይደርስ ታውቋል። ይህም ለዋልያዎቹ መልካም ዜና ይመስላል፡፡ አሠልጣኝ ክላውድ ሌሮይም የዶሬ አለመኖር የሚፈጥረውን ክፍተት ለመድፈን ለ21 ዓመቱ የስታዴ ብሬስቶይ አጥቂ ኬቭን ኩቤምባ ጥሪ አድርገዋል።

በፈረንሳይ 4ኛ ዲቪዝዮን ከሚጫወተው ሌ ፖንቴት ከተቀነሰ በኋላ ክለብ አልባ ሆኖ የቆየው ግብ ጠባቂ ክሪስቶፈር ማፎውምቢ መጠራት እና የሊዮፓርድሱ ግብ ጠባቂ ቻንሴል ማሳ ከቡድኑ ውጪ መሆን እያነጋገረ ሲሆን ወጣቱ የጌታፌ አማካይ ፊልትዘርላንድ ምባካ ሌላው በቡድኑ ሳይካተት የቀረ ተጫዋች ሆኗል።

ኮንጎ ዋሊያዎቹን የፊታችን ቅዳሜ አዲስ አበባ ላይ የምትገጥም ሲሆን የመልሱን ጨዋታ ደግሞ ከ3 ቀን በኋላ በብራዛቪል ታስተናግዳለች።

Dore
በጉዳት በኢትዮጵያው ጨዋታ የማይሰለፈው ፍሬቦሪ ዶሬ

 

ኢትዮጵያን የሚገጥመው ጠየሪፑብሊክ ኦፍ ኮንጎ ስብስብ

ግብ ጠባቂዎች

ክሪስቶፈር ኦንሪ ማፎውምቢ (ክለብ የለውም)

ፓቬል ንድዚላ (ኤቶይል ዱ ኮንጎ)

 

ተከላካዮች

ባውድሪ ማርቪን ቶኒ (ዙልቴ ዌሬጌም – ቤልጂየም)

ዲሚትሪ ቢሲኪ (ኤሲ ሊዮፓርድስ – ኮንጎ)

ፍራንሲስ ንጋንጋ (ስፖርቲንግ ቻርሌሮይ – ቤልጂየም)

ሳጌሴ ባቤሌ (ኤሲ ሊዮፓርድስ – ኮንጎ)

ቦሪስ ንጉንጋ (ኤሲ ሊዮፓርድስ – ኮንጎ)

ኮስሜ አንቶኒ ማቮንጉ (ድያቢሌስ ኖይርስ – ኮንጎ)

ካሮፍ ባኩዋ (ኤሲ ሊዮፓርድስ – ኮንጎ)

አርኖልድ ቡካ ሞውቱ (ኤስሲኦ አንጀርስ – ፈረንሳይ)

 

አማካዮች

መርቬል ንዶክይት (ካራ – ኮንጎ)

ፕሪንስ ኦኒያንጉዌ (ሬሚስ – ፈረንሳይ)

ዴልቪን ንዲንጋ (ሎኮሞቲቭ ሞስኮ – ሩሲያ)

ቤል ዱሬል ኦቮውኑ (ኬን – ፈረንሳይ)

ሃርዲ አላይን ሳማራንጌ ቢንጉይላ (ኤጄ ኦክሴር – ፈረንሳይ)

ጀስታሌይን ንኮንኩ (ኤሲ ሊዮፓርድስ – ኮንጎ)

 

አጥቂዎች

ቤርሲል ንጋትሶንጎ (ኤቶይል ዱ ኮንጎ – ኮንጎ)

ቲዬቪ ቢፎውማ (ግራናዳ – ስፔን)

ጆርጅስ ካደር ቢዲምቡ (ኤሲ ሊዮፓርድስ – ኮንጎ)

ኬቨን ኮውቤምባ (ብሬስት – ፈረንሳይ)

ጁኒየር ማኪኤሴ ሞውዚታ (ኤሲ ሊዮፓርድስ – ኮንጎ)

 

© Soccerethiopia.net

ያጋሩ